Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.62K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ በ2019 በጀት የ1ኛው ሩብ አመት በቅንጅት የተከናወኑ የፀጥታና የህግ ማስከበር ስራዎችን ገመገሙ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የሁለቱም ከተማ የፖሊስ አዛዦች እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በያዝነው 2019 በጀት በ1ኛው ሩብ አመት በቅንጅት የተሰሩ የፀጥታ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን ገምግመዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት የፀጥታ ስራ አስቀድሞ ማቀድ እና ቁጥጥር ማድረግ የሚጠይቅ ስለሆነ ከሸገር ከተማ ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ በትብብር በመሰራቱ ወንጀልን መቀነስ እና የፀጥታ ስጋቶችን መቆጣጠር መቻሉን ገልፀዋል። በቀጣይ በሁለቱም ከተሞች በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ፣ በሰው ላይ የሚፈፀሙ ከባድ ወንጀሎችን፣ የምርት መደበቅ ፣ እንዲሁም ለወንጀል መፈፀም መንስኤ የሚሆኑ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመከላከል የጋራ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ጀነራሉ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት በመጀመሪያው ሩብ አመት በሁለቱ ከተሞች የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠርና ህብረተሰቡን በማሳተፍ ወንጀልና ሕገ-ወጥ ተግባራትን ከመካከል አኳያ፣ የወንጀል ስጋቶችን ማስወገድ ፣ የኑሮ ውድነት እንዲከሰት ምርት የሚያከማቹ አካላትን ከመቆጣጠር አኳያ የተሻለ ውጤት የተመዘገበ መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀዋል። ለዚህ ትልቅ ውጤት መገኘት ደግሞ በጥምረት መስራት በመቻሉ ነው ብለዋል። በሁለቱም ከተሞች ያሉ የወንጀልና የፀጥታ ስጋቶችን በመቅረፍ አስተማማኝ ሁኔታን በመፍጠር የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተጠናከረ መንገድ ይሰራል ብለዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የሸገር ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ እንደገለፁት ሁለቱ ከተሞች የማይነጣጠሉ ስለሆኑ የፀጥታ ሁኔታን አስተማማኝ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፣ ሠላምን በማስፈን ሂደት የአስተዳደር አካላት እና የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በ2019 በጀት በ1ኛው ሩብ አመት በጋራ የተሰሩ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል። በሁለቱ ከተሞች ዘላቂ ሠላም እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ፣ በሠላም ጉዳይ ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዲፈጠር ተደርጓል። ልዩ ልዩ ሕዝባዊ መድረክ በማዘጋጀት በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ በፀጥታው ዙሪያ እንዲወያይ፣ የጋራ የሠላም እሴቶች የመገንባት ስራ ተሰርቷል።

በሩብ አመቱ በከተማችን አዲስ አበባ የተካሄዱ የአደባባይ በዓላት፣ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ፣ የመንግስት ምስረታ በሠላም ማከናወን የተቻለ ሲሆን ለዚህ ውጤት መገኘት ትልቁን ሚና የተወጡት የሁለቱ ከተሞች እና ሌሎች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በህዝብ ትብብር መሆኑ ተገልጿል።

በጋራ የፀጥታ ስምሪትና አሰሳ፣ በተደረገ በፍተሻ ለወንጀል፣ ለሕገ-ወጥ ድርጊቶች መፈፀሚያ የሚያገለግሉ ህገ-ወጥ ጦር መሳሪያ እና እኩይ ዓላማ አንግበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር በዋል ሴራቸውን ማክሸፍ ተችሏል። በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ንግድና ያለ ደረሰኝ ግብይት እንቅስቃሴን በመቆጣጠር መንግሥት ሊያጣ የነበረውን ከፍተኛ ገቢ ማዳን እንደተቻለ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ፍቃዱ አቶምሳ እና የሸገር ከተማ ሠላም ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አሰፋ እንዳሉት በሩብ አመቱ አመርቂ የህግ ማስከበር ስራ በጋራ መሰራቱን ገልፀው፤ ወደፊት የአዲስ አበባን እና የዙሪያዋን ሠላምና ፀጥታ ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናገረዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በአፈፃፀም ወቅት የነበሩ መልካም ጎኖችን ማስቀጠል፣ መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች እንዲስተካከሉ ሀሳብ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረኩ ተገቢ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
*
ዘገባ፦ ዋና ሳጅን አምሳሉ መብራቴ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤23🔥3👍2👎1
በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከል እድሳት ተደርጎ ተመረቀ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአትክልት ተራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በወረዳ 2 ቀጠና 7 ህብረተሰቡን በማስተባበር ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ያስገነባውን ደረጃውን የጠበቀ የማህበረሰብ አቀፍ  ፖሊስ  አገልግሎት መስጫ ማዕከል ስራ አስጀመረ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና መምሪያ የወንጀል መከላከል እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ም/ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ደገፋ እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከል መገንባት በህብረተሰቡ እና በፖሊስ መካከል ያለውን ግንኝነት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በጋራ የምንከላከልበት ነው በማለት በግንባታው ላይ አስተዋፅኦ የነበራቸው አካላትን በዋና መምሪያው ስም አመስግነዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአትክልት ተራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አብርሀም ገብረፃዲቅ በበኩላቸው ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል የተገነባው በህብረተሰቡ በጎ ፈቃደኝነት 3,500,000 (ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ) ብር ወጪ በማድረግ መሆኑንና ማዕከሉ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ  ድረስ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ገልጸው፤ የፖሊስ ስራ ያለ ህብረተሰቡ ተሳፎ ውጤታማ ስለማይሆን የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ገልፀዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ምክትል ስራ አስፈፃሚ የሰራተኛ እና ስራ እድል ፈጠራ ፅ/ቤት ኃላፊ የኋላሸት ተድላ እንደተናገሩት ለማህበረሰቡ ሠላም እና ደህንነት መረጋገጥ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ከገለፁ በኋላ በህብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ ለማቀራረብ ማዕከሉ ጠቀሜታው የጎላ  ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

የአካባቢ ነዋሪዎች የቀድሞው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከሉ ለአገልግሎት ምቹ እንዳልነበረ ገልፀው። የማህበረሰቡን ሠላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ ሳይሰለች ለሚሰራው ፖሊስ ከጎኑ በመሆን ማዕከሉ 24 ሰዓት ክፍት ሆኖ እንዲያገለግል የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

ማዕከሉ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ አስተዋጾኦ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ጻዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤13👍8👎1