Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል።
የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላት #ማረጋገጥ ችሏል።
በዚህ መሰረት ፦
1ኛ. በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት #በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ኘሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደትም እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስመቅጧል።
2ኛ. በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 /2015 እስከ ሐምሌ 13 /2015 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።
3ኛ. የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።
በተጨማሪም እንደ አገር ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር ከ2016 ጀምሮ ለማስተካከል ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚሁ ማዕቀፍ አንዲያስተካክሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል።
ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የተለያዩ #ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እየሰሙ አለመረጋጋት ውስጥ መግባታቸውን ሲገልፁልን ነበር ፤ በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር / የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሚሰጡት ትክክለኛ መረጃ #ብቻ እንድትከታተሉ ፤ በቀረው አጭር ጊዜም ዝግጅታችሁን ታጠናክሩ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።
(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል #ትክክለኝነቱን ያረጋገጠው ነው።)
@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT

#MoE #ይፋዊ
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ #በይፋ አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ይሰጣል ብሏል።
የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱም ገልጿል።
በ2014 ዓ.ም የህግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱ አስታውሷል።
@tikvahethiopia

👍3
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጄና አማካኝነት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች መረጃ በአስቸኳይ እንዲላክለት ጠይቋል።
ሚኒስቴሩ ፤ ተቋማት መረጃው እጅግ ቢዘገይ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲልኩ ያሳሰበ ሲሆን የማያሳውቅ ዩኒቨርሲቲ " ተፈታኝ ተማሪ የለውም " በሚል ተይዞ የሚታቀድ መሆኑን በጥብቅ አስገንዝቧል።
በ2015 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 77,981 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፉት 48,632 ተማሪዎች ወይም 62.37 በመቶ መሆናቸው አይዘነጋም።
በግል ተቋማት ደግሞ ለፈተና ከተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ነበሩ።
በድምሩ ከአጠቃላይ 150,184 የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉት 61,054 ብቻ ወይም 40.65 በመቶ ናቸው።
የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና አስተዳደር መመሪያ እንደሚያሳየው ከሆነ ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰጣል። የመጀመሪያው በአመቱ መጨረሻ ሲሆን ሁለተኛ በአመቱ አጋማሽ ነው።
የመጀመሪያውን የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚዘጋጀው ሌላ ፈተና መፈተን የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ስርዓት እንደሚዘረጋ መግለፁ አይዘነጋም (በዚህ ጉዳይ ወደፊት የሚወጣ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን)።
#TikvahEthiopia

👍4❤2😱2
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።
1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤
2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤
ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።
ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።
ሚኒስቴሩ ፦
➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።
➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።
➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር➡️ 1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ seneexit2016@gmail.com ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።
1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤
2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤
ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።
ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።
ሚኒስቴሩ ፦
➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።
➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።
➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11❤5