4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
95K subscribers
13.8K photos
363 videos
35 files
1.12K links
እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ

እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው።

ለማስታወቂያ ስራ - @Marketing_team433
Download Telegram
Spider-Man በለው፣ ጉብ ይልባቸውና "የቅቅሌን"

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
🤣266😁31❤11
✅ታላቁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን በአንድ ወቅት ስለ ራሱ ፊቱ ሻካራነትና አስቀያሚነት ሁሉም ከጀርባውም በፊቱም ይወራ ነበር። ታድያ እሱ እየቀለደ እንዲህ የሚል ታሪክ አወራ።
...
"አንድ ቀን ጫካ ውስጥ ብቻዬን ስጓዝ አንድ ፈረሰኛ አገኘሁ። ሰውየው ፈረሱን አቁሞ ወረደና ትልቅ ቢላዋ አውጥቶ ወደ እኔ ዘረጋው። ደንግጬ 'ምንድነው?' ስለው... 'ይህንን ቢላዋ ያዝ፤ ከአንተ የበለጠ አስቀያሚ ፊት ያለው ሰው ስታገኝ ስጠው ተብዬ ነበር። ካየሁህ ጀምሮ ግን ይህ ቢላዋ ያንተ መሆን እንዳለበት አምኛለሁ!' አለኝ።"
...
✅ይኸን ሲያወራ እሱን ጨምሮ ሁሉም በሳቅ ፈነዱ፤ ከዚያ በኋላ በመልኩ ያሾፈ ሰው የለም።
...
በራሳችን ላይ መሳቅ የምንችለው የውስጥ በራስ መተማመን ሲኖረንና ማንነታችንን ሙሉ በሙሉ ስንቀበለው ብቻ ነው። የሰዎች አስተያየትና ትችት የማይበግረው ጠንካራ ማንነት የሚገነባው ከውስጥ ነው።
...
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤174🔥18🥰6🫡4👍2👏1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤4
አንዳንድ የኛ ሀገር ሌባ ባለስልጣናት ዱባይ ፡ አሜሪካና አውሮፓ የገዙት ቤት አረፍ ለማለት ሲሄዱ ፡ በቢዝነስ ክላስ ፈልሰስ ብለው ነው ።
የልጆቻቸው ደግሞ ከዛም ይብሳል ። አለችልህ ደግሞ የሜክሲኮ ፕሬዝደንት ፡
....
ሜክሲኮን ላለፉት ሁለት አመታት እየመራች የምትገኘው የሜክሲኮዋ ፕሬዝደንት ክላውዲያ ሺንባውም፡ ሰሞኑን ፡ በAPEC ጉባኤ ላይ ለመካፈል ወደ ቻይና ሼንዜን የሄደችው በተራ የመንገደኞች አውሮፕላን ፡ ለዛውም በኢኮኖሚ ክላስ ከፍላ ነው ።
.....
ፕሬዝደንት ክላውዲያ 21 ሰአታት የሚፈጀውን በረራ በኤኮኖሚ ክላስ ተጉዛ ሼንዜን መግባቷ ከታወቀ በኋላ በቻይና ታዋቂ በሆነው ዌይቦ በተባለው ሶሻል ሚዲያ ላይ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰወች የተቀባበሉት ሲሆን ፡ CNN , ብሉምበርግ እና በርካታ ታላላቅ ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ ።


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
❤129👍10🥰3🔥2
😡እስከመቼ እየበሉህ? ❓
🎉እድል ቤት ና አስመልስ💰

🔼እኛ አንናገርም እንከፍላለን💵🤑

ለመጫወት ይሄን ይጫኑ
👉 https://bilbet.s.gy/Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁18❤4💔4🔥2🥰1
Forwarded from 
የኢንተርኔት እና የኔትወርክ ልዩነት ምንድን ነው? መልዕክት ሲዘገይና ሲቆራረጥስ ችግሩ የየትኛው ነው?

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን «ኔትወርክ ጠፋ» ወይም «ኢንተርኔት ቀዘቀዘ» የሚሉ አባባሎችን በተደጋጋሚ ብንጠቀምም፣ ሁለቱ ቃላት በመሠረታዊ አሠራራቸውና በሽፋን ወሰናቸው የተለያዩ መሆናቸውን የቴክኖሎጂ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በመረጃዎቹ መሠረት ኔትወርክ (Network) ማለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ እንደ ኮምፒውተር፣ ስልክ እና ፕሪንተር ያሉ መሣሪያዎች መረጃንና ሀብትን ለመለዋወጥ እርስ በርስ ሲገናኙ የሚፈጠር ሥርዓት ነው።

ይህ ግንኙነት በአንድ ቤት ወይም በቢሮ ውስጥ ብቻ ተወስኖ (LAN) የኢንተርኔት አገልግሎት ሳይኖር ሊሠራ የሚችልና በተወሰነ አካል ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ነው።

በአንጻሩ ኢንተርኔት (Internet) ማለት በመላው ዓለም የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ ኔትወርኮችን እርስ በርስ የሚያገናኝ «የኔትወርኮች ኔትወርክ» ነው።

ኢንተርኔት በአንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ብቻ የሚተዳደር ሳይሆን፣ የጋራ የመገናኛ ሕጎችን (Protocols) በመጠቀም በዓለም ዙሪያ ያሉ ተጠቃሚዎችን የሚያስተሳስር ክፍት ዓለም አቀፍ መረብ ነው።

የዘርፉ ባለሙያዎች ልዩነቱን በቀላሉ ሲያስረዱ «እያንዳንዱ ኢንተርኔት ኔትወርክ ቢሆንም፣ እያንዳንዱ ኔትወርክ ግን ኢንተርኔት አይደለም» ይላሉ።

ይህንን ልዩነት በዕለት ተዕለት ገጠመኞቻችን ስንመለከተው፣ መደበኛ የስልክ ጥሪ ስናደርግ ድምፅ የሚቆራረጠው ወይም የስልክ ምልክቱ (Signal) የሚጠፋው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪው የኔትወርክ መሠረተ ልማት ሲጨናነቅ ወይም ካለንበት ቦታ አንጻር የሲግናል ሽፋኑ ሲዳከም ነው። ይህ ያለ ኢንተርኔት የሚከሰት የኔትወርክ ችግር ነው።

በሌላ በኩል ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን መልዕክት አልክም ብሎ እየተሽከረከረ ሲያዘገይ ሁኔታው በሁለቱም ምክንያት ሊከሰት ይችላል። መሣሪያችን ከቤት ወይም ከቢሮ ዋይፋይ (Wi-Fi) ራውተር ጋር በአግባቡ ካልተገናኘ ችግሩ የኔትወርክ ሲሆን፤ ከዋይፋይ ጋር ተገናኝቶ ነገር ግን ከአገልግሎት ሰጪው ወደ ዓለም አቀፉ መረብ የሚወስደው መስመር ሲዘጋ ወይም ሲዳከም ደግሞ ችግሩ የኢንተርኔት ይሆናል።

በመሆኑም በአንድ ቤት ውስጥ ያሉ መሣሪያዎች በራውተር (Router) አማካኝነት እርስ በርስ ሲገናኙ ኔትወርክ የሚፈጥሩ ሲሆን፣ ያ ራውተር ከቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ጋር ተያይዞ ከዓለም ጋር ሲያገናኛቸው ደግሞ ወደ ኢንተርኔት ይሸጋገራሉ።(መናኸሪያ ሬዲዮ)

@Tech_433et @Tech_433et
❤88🙏8🤝3👍1
የምር ሁላችንም ይሄን ቪዲዮ መስራት አለብን😃😃


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
😁316❤16👍9👏4😢3
ይህ የምትመለከቱት ፎቶ 1920 ካናዳ የተነሳ ፎቶ ነው! ዘመኑ ቀልድ አያውቅም ነበር! አንድ ሰው የሆነ አዲስ ነገር ፈጠርኩ ካለ ለህዝብ ከመቅረቡ በፊት ራሱ ላይ ይሞከራል!

የፈጠረው ብቻ ሳይሆን ማስታወቂያ የሚሰራውም በዚች ፈተና ያልፋል!  ፎቶው ላይ እንደምታዩት የውሃ ማስተላለፊያ የሸክላ ቱቦ ሰርቶ ነው አንዱ .."ብዙ ቶን ክብደት ቢያርፍበትም አይሰበርም ጠንካራ ነው" በማለቱ የፈጠራው  ባለቤት  ቱቦው ውስጥ ተቀምጦ ሙከራ እየተደረገ ነው! ከተሰበረም ደሙ በራሱ ላይ ነው!
😁119😭21❤16🤝8😨3🤯1
የቀብር ስነስርዓት ላይ እርቃን መደነስ⁉️

በቻይና በቀብር ስነስርዓት ላይ  ሀዘን ላይ ያሉ ዘመዶችን ለማበረታታት እና ብዙ ሰዎች ቀብር ስነስርዓት ላይ እንዲገኙ ስትሪፐር ይቀጥራሉ ።

ስትሪፐር ማለት  አንዲት ሴት ልብሷን አውልቃ የተለያዩ የዳንስ ትርኢቶችን ሳቢ በሆነ መንገድ የምታሳይ ሴት ማለት ነው። በእንደዚ ዓይነት የቀብር ስነስርዓት ላይ ወንድ የተባለ አይቀርም ነው ሚባለው።

የዚ አይነት ትርኢት የሚደረገው ለአዋቂዎች መዝናኛ በሚሆኑ ቦታዎች እንደ ክለቦች ወይም ፓርቲዎች ላይ ነው።


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
😁113🙉17😭14❤8🤯4
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
⛔️ የ GTA ሀክ ያረከው የ 17 አመቱ ታዳጊ  ፖሊስ ላፕቶፑን ቀምቶ በሆቴል ጥበቃ ስር አደረገው... እሱ ግን በሆቴሉ ቴሌቪዥን ብቻ የGTA 6ን ሚስጥር አሾለከ! ይህ ታሪክ የሚመስለው የሆሊውድ ፊልም ቢሆንም፣ በመስከረም 2022 በእንግሊዝ ውስጥ በእውነት የተፈጸመ ነው። 🌟 የታሪኩ ባለቤት አሪዮን ኩርታጅ (Arion Kurtaj) የተባለ የኦክስፎርድሻየር ወጣት ሲሆን፣ ጥቃቱን ሲፈጽም ገና 17 ዓመቱ…
ሰበር ዜና

✅GTA 6ን ሀክ ያደረገው ግለሰብ ከእስር ተለቀቀ!

በ2022 የGTA 6 ያልተጠናቀቀ የጨዋታ ቪዲዮዎችን በኢንተርኔት ያወጣው ሀከር Arion Kurtaj የ7 ዓመት እስር ተፈርዶበት በዚያው ቀን ከእስር ተለቋል።

የ21 ዓመቱ ሀከር Rockstar Gamesን በመጥለፍ ወደ 90 የሚጠጉ የGTA 6 የጨዋታ ቪዲዮዎችን ሰርቆ በኢንተርኔት ላይ ለቋቸዉ ነበር።

የሚያስገርመው ጥቃቱን የፈጸመው ኮምፒውተሩ በፖሊስ ከተወሰደበት በኋላ ሲሆን፣ በሆቴል ውስጥ እያለ የAmazon Fire TV Stick፣ ሞባይል ስልክና የሆቴሉን ኢንተርኔት በመጠቀም ነዉ።

ሀከሩ ከእስር የተለቀቀው ከ4 ዓመት በላይ በቁጥጥር ሥር ካሳለፈ በኋላ ቀሪውን ቅጣት በሕግ ቁጥጥር ሥር እንዲያሳልፍ በመወሰኑ ነው


ተጨማሪም Netflix ,Prime Video እና ሌሎችም Documentary ለመስራት ሀይለኛ ግብግብ እያደረጉ ነው


🌐@Amazing_fact_433
🌐@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤89😁22👍3👏2😱1
ጄሰን ሁአንግ ይባላል የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቺፕ አምራች ኩባንያ ኒቪዲያ (Nvidia) መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነው ከተወሰኑ ቀናት በፊት ከስራ መልቀቃቸው ይታወሳል

ሁዋንግ ለ33 ዓመታት የመሩትን ኩባንያ ለመልቀቅ የተገደዱት፣ ከጋብቻ ውጭ ከፈጸሟቸው ሁለት የፍቅር ግንኙነቶች ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰ ውዝግብ ምክንያት ነው። ከእነዚህም መካከል አንደኛው ግንኙነት ለቻይና ትሰልላለች ተብላ በአሜሪካ የደኅንነት ተቋማት ከተጠረጠረች ሴት ጋር የነበራቸው ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ በኩባንያው ውስጥ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ከምትሠራ ባልደረባቸው ጋር መሆኑ ተገልጿል።

ታድያ አሁን በዶናልድ ትራምፕ ውትወታ ወደ መስራያ ቤቱ ከተመለሰ በኃላ ሰራተኞቹ በዚ ልክ በደስታ ጮቤ እየረገጡ ተቀብለውታል።

ይበል የሚያሰኝ ነው Cheat አድርጎ በዚ ልክ የሞቀቀ አቀባበል የተቀበሉት የመጀመሪያ ሰው ሳይሆን አይቀርም ።

The Irreplaceable Man የሚል ቅፅም ስም ተሰጦታል 👏👏

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
❤77🤣16👏10🔥5👍1
Forwarded from 
ሰዎች ለመሳም በሚቀርቧቸው ወቅት ጨቅላ ህፃናት የሚያዩት ምስል እና የሚያለቅሱበት ሳይንሳዊ ምክንያት
 
አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት የእይታ ብቃት (Visual Acuity) ገና ሙሉ በሙሉ ያላደገ በመሆኑ ሰዎችንና አካባቢያቸውን የሚመለከቱበት መንገድ ከአዋቂዎች የተለየ መሆኑን የህፃናት ህክምና ጥናቶች ያመላክታሉ።
 
ህፃናት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ጥራት ባለው መልኩ ማየት የሚችሉት ከ20 እስከ 30 ሴንቲ ሜትር (ከ8 እስከ 12 ኢንች) ባለው አጭር ርቀት ላይ የሚገኙ አካላትን ብቻ ነው። ይህም ጡት በሚጠቡበት ወቅት ከእናታቸው ፊት ጋር ያለውን ርቀት የሚያክል ነው።
 
ሰዎች ለመሳም ወይም ለማጫወት ከ20 ሴንቲ ሜትር በታች ወደ ህፃናቱ ፊት እጅግ በሚቀርቡበት ጊዜ፣ የሰው ፊት ቅርጽ ተዛብቶና አጉልቶ የሚታያቸው ሳይሆን በከፍተኛ ሁኔታ የደበዘዘ (Blurry) ሆኖ ያዩታል። ህፃናቱ በዚህ ወቅት የተለየና ጥራት ያለው የፊት ቅርጽ የማየት አቅም የላቸውም።
 
በተጨማሪም የሰው ልጅ ፊት ህፃናት ትኩረት ከሚሰጧቸው የመጀመሪያ ነገሮች አንዱ በመሆኑ፣ የአንጎላቸው የነርቭ ስብስብ የሰዎችን የፊት ገጽታና ስሜት በፍጥነት ለመለየት እድገት በማድረግ ላይ ይገኛል።
 
በዚህ ሂደት ሰዎች ወደ ህፃናት ፊት በድንገት እጅግ በሚቀርቡበት ወቅት ህፃናቱ የሚያለቅሱት ፊታቸው ተዛብቶ ስለሚታያቸው ሳይሆን፣ በድንገተኛ እንቅስቃሴ፣ በድምጽ እና በቅርበት በሚፈጠርባቸው የነርቭ እና የባህሪ መደናገጥ (Sensory Overload) ምክንያት እንደሆነ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ።(መናኸሪያ ሬዲዮ)
 
@Ethionews433
@Ethionews433
😁158❤34🤣14💔3👏1
ጥንቃቄ ‼️
ሰዎች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ጥሪ እየደረሳቸው ይገኛል፦
•  +947
•  +371
•  +563
•  +370
•  +255
ወይም በእነዚህ መነሻዎች የሚጀምሩ ማንኛውም ቁጥሮች፦ +371፣ +375፣ +381
እነዚህ አካላት አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ይዘጋሉ። ተመልሰው ከደወሉላቸው በ3 ሰከንድ ውስጥ በስልክዎ ላይ ያለውን የሰው ዝርዝር (Contact list) መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም በስልክዎ ላይ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃዎች ካሉ በቀላሉ ያገኟቸዋል።

የሀገራት መለያ ኮዶች፦
•  +375 - ቤላሩስ (Belarus)
•  +371 - ላቲቪያ (Latvia)
•  +381 - ሰርቢያ (Serbia)
•  +563 - ቫልፓራይሶ (Valparaiso)
•  +370 - ቪልኒየስ (Vilnius)
•  +255 - ታንዛኒያ (Tanzania)       
                                                                                                                    መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦

1.ለእነዚህ ቁጥሮች አይመልሱ ወይም ተመልሰው አይደውሉ።

2.ማንኛውም ደዋይ በስልክዎ ላይ #90 ወይም #09 እንዲጫኑ ቢጠይቅዎት በፍጹም እንዳያደርጉት።

ይህ ዘዴ የእርስዎን ሲም ካርድ (SIM card) ለመቆጣጠር፣ በእርስዎ ወጪ ስልክ ለመደወል እና እርስዎን ለወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙበት አዲስ ሴራ ነው።
                                                               ይህንን የጥሰት ሙከራ ለመከላከል ይህንን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ለብዙ ጓደኞችዎ ያጋሩ (Forward ያድርጉ)!!!


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
🤝147❤35👍17😁2🥰1
✅ይሄንን ያውቃሉ?

ሴቶች "Baby " ተብለው ሲጠሩ በአእምሯቸው 🧠ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዲያድርባቸው ያደርጋል ይህም ፈጣን የሆነ emotional ጭንቀትን ያስወግድላቸዋል::

✔️@amazing_fact_433
✔️@amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁141🤣30❤11👍6💔1
ከ ሺ በላይ የአማርኛ እና English መጽሐፎች(በpdf) በነፃ የሚገኙባቸውን

📚ሳይኮሎጂ ,
📚ልብወለድ ,
📚ታሪክ እና
ሌሎችም

«እንደምርጫዎ» ቻናላችንን  ይቀላቀሉ!


📱https://t.me/Enmare1988/10303
📱https://t.me/Enmare1988/10303
📱https://t.me/Enmare1988/10303
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤9🤣3👌2
ከ12 ሚስቶቹ 102 ልጆችን የወለደው የ67 ዓመቱ ኡጋንዳዊ የልጆቹን ስም ለማስታወስ በማስታወሻ መፃፍ ነበረብኝ ይላል።  

ከዚህ በኋላ የወሊድ መቆጣጠሪያ ተጠቀሙ፣ኑሮው ከብዶኛል  ያለው አዛዉንቱ 568 የልጅ ልጆችም አሉት።
🤣251❤23😨19😁10👍4🔥2🤯1😭1
የሚሰራ ሰው በመጥፋቱ ምክንያት እስረኞች እየተከፈላቸው ስራ መስራት ጀምረዋል - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)

@amazing_fact_433
😁278🤣22👍11❤7😱2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ - " ሠራተኛ አጥተን፣ እስረኞች አውጥተን በቀን 500፣ 600፣ 700 ብር እየከፈልን በአንድ ቀን ነው የምናሠራው” ብለዋል።


@amazing_fact_433
@amazing_fact_433
🤣379😁32❤14😢11🤝2😎2🥰1👏1😭1
ከአፈና (እገታ) ጋር በመላው አለም ዛሬም ድረስ መነጋገሪያ የሆነ ታሪክ አለ። ...
.
እኤአ 1973 ላይ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም 4 ሰዎች ባንክ ለመዝረፍ ወደ ከተማዋ ባንክ ይገባሉ። ከዛ በባንኩ ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ሶስቱን እዛው አግተው አስቀርተው ሌሎቹን በሙሉ ያስወጣሉ።

ከዛ ፖሊስ ባንኩን ይከባል። አጋቾቹ "የፈለጋችሁትን እንሰጣችኋለን ውጡ፣ ያገታችኋቸውን ልቀቁ" ሲባሉ "በፍፁም አይሆንም" ብለው አራት፣ አምስት ቀን እዛው በባንኩ ውስጥ ካፈኗቸው ሰዎች ጋር ይከርማሉ።

በመላው ስዊድንም ጉዳዩ በየሬዲዮኖች በቀጥታ መተላለፍ ጀመረ። ... ታዲያ የሚገርመው በነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ አንዱ አጋችና ከታገቱት መሃል የባንክ ሰራተኛ በነበረችው መሃል ከባድ ፍቅር ይፈጠራል።...እሷ ባለትዳርና የልጆች እናት ናት። ... ግን በቃ ልክ እንደ አፍላ ወጣት ሁለቱ በሚገርም ፍቅር ተሳሰሩ።

በመጨረሻው ቀን አጋቾቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ እሷም ይዘኸኝ ካልሄድክ ሞቼ እገኛለሁ አለች። መጨረሻ ከባንኩ አምልጠው ሲጓዙ ተያዙ። ... ፍርድ ቤት ቀርበውም መስክሩባቸው ሲባሉ አጋቿን ያፈቀረችው ሴትና ጓደኞቿ እንኳን ሊመሰክሩባቸው "አንድም ቀን አላገቱንም" ብለው ያልተጠበቀ መልስ ሰጥተዋል።

ከዛ በኋላ ነው Stockholm Syndrom የሚባለው ነገር የመጣው። Stockholm Syndrom ማለት ባጭሩ አፋኝ ከታፋኝ ወይም ታጋች ከአጋች ጋር በፍቅር ሲወድቁ ማለት ነው።

@amazing_fact_433
@amazing_fact_433
🤣56❤19🔥2🌚1
የሰው ልጅ በቴሌስኮፕ ሊያየው የሚችለው የጠፈር ወሰን እስከ 46.5 ቢሊዮን የብርሃን ዓመታት ርቀት ብቻ ነው።

ከዚህ ወሰን ባሻገር ያለው ጠፈር መጨረሻ የለውም ተብሎ ይታመናል። ለምን ከተባለ ጠፈር (ዩኒቨርስ) በየሴኮንዱ በሁሉም አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየሰፋ በመሄድ ላይ ስለሆነ ቋሚ “መጨረሻ” ወይም “ዳርቻ” የለውም።

@amazing_fact_433
@amazing_fact_433
❤13👍3