ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.3K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
‏صورة من حسين عبد الله
✅ ሱናን መኻለፍ ያስቀጣል !

🔹 ሰዒድ ኢብኑ መሰይብ አንድ ሰው ሰሀይ
ከወጣ በኋላ ስጁዱና ሩኩዑ እያበዛ ከሁለት ረካዓ በላይ ሲሰግድ አየው, እንደዚህ አታድርግ ብሎ ከለከለው, ሰውየውም አንተ የሙሐመድ አባት ሆይ አላህ ሶላት በመስገዴ ይቀጣኛል እንዴ ? ሲል ጠየቀው ! ሰዒድም (ሶላት በመስገድህ) አይቀጣህም, ነገር ግን ሱናን በመቃረንህ ይቀጣሃል አለው "! ።

http://t.me/bahruteka
Audio
መውሊድ ማክበርን ማን ጀመረው

መውሊድ ማክበር እውን ነብዩን የሚወዱ ሰዎች ተግባር ነውን ? መውሊድ ማክበርስ የሳቸው መውደድ መገለጫ ነውን ?
ለማንኛውም መውሊድ ማክበርን አስመልክቶ ልናውቃቸው የሚገቡ ነጥቦች በጥያቄና መልስ መልኩ ቀርበዋል ። ጥያቄዎቹ አራት ናቸው እነርሱም : –
1ኛ – ማን ጀመረው ?
2ኛ – መቼ ነው የጀመረው ?
3ኛ – የት ነው የጀመረው ?
4ኛ – ለምድነው የጀመረው ? የሚሉ ናቸው ከነመልሶቻቸው ቀርበዋል ።
እነዚህ መሰረታዊ ነጥቦችን ማወቅ መውሊድ ማክበር ከእስልምና ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር እንደሌለና የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሞችን ለመሸንገል ያመጡት ፈጠራ መሆኑ በግልፅ እንዲገባን ያደርጋል ።
መውሊድን ማክበር ወደ አላህ የሚያቃርብና ምንዳ የሚያስገኝ ቢሆን ኖሮ እነዚያ ለነብዩ የህይወት ዋጋ የከፈሉ ብርቅዬ የኢስላም የበኩር ልጆች ያከብሩት ነበር ። አቡ በክር ፣ ዑመር ፣ ዑስማንና ዐልይ ማንም ባልቀደማቸው ነበር ። የአላህ መልእክተኛ ከናንተ ውስጥ እኔ አንዳችሁ ዘንድ ከወላጆቹ ከልጆቹና ካጠቃላይ ሰዎች በላይ ተወዳጅ እስከምሆን ድረስ አላመነም ሲሉ እንዴት መውሊዴን አክብሩ አላሉም ?
አላህ ሆይ ሐቅን አውቀን የምንከተለው ባጢልን አውቀን የምንርቀው አድርገን ።

http://t.me/bahruteka
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ወድ ወንድምና እህቶች ቴሌግራም የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እያስከፈለ ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ይለቃል። አሁን የተለቀቀው ማስታወቂያ እኔን አይወክልም።  ማስታወቂያውን ሪፖርት አድርጋችሁ ለማስጠፋት ከጎን ያለውን ሶስት ነጥብ ነክታችሁ ምጫዎች ሲመጡ spam ብላች ላኩ።

https://t.me/bahruteka
🚫 ተጠንቀቅ !

አንዳንዴ አሳካሁት ከምትለው አላማ በስተጀርባ ያለው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ብታውቅ ኖሮ ሂደትህ የስኬት ሳይሆን የክስረት እንደነበር ታውቅ ነበር ። እውነተኛ ስኬት ላይ ለመድረስ የልብ ንስህና ለአላህ ብሎ መንቀሳቀስና አላህን መፍራት የግድ ነው ! ። ስኬት ላይ ደርሻለሁ ብሎ እያሰቡ ከመክሰር አላህ ይጠብቀን ።

https://t.me/bahruteka
👉  የመውሊድ ታሪክ

   መውሊድ የሚለው ቃል የትውልድ ቦታና ጊዜን የሚያመለክት ሲሆን ሰዎች ዘንድ የተለመደው የነብዩ ሙሐመድ የልደት ( እሷቸው የተወለዱበት ) ቀን መሆኑን ነው ። ስለሆነም ይህ ቀን በዐለም ላይ አብዛኛው ሙስሊም ዒድ አድርጎ ያከብረዋል ። ይህ ተግባር በሸሪዓ እይታ እንዴት ይታያል የሚለውን ለማወቅ መጀመሪያ የሚከተለውን ነጥብ ማወቅ ያስፈልጋል ። አንድ ነገር በሸሪዓ የተፈቀደ ነው የሚባለው አላህ ያዘዘው ወይም ነብዩ ሙሐመድ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ያዘዙት ወይም ፈለጋቸውን እንድንከተል ያዘዙን ሶሓባዎች የሰሩት ሲሆን ነው ።
ከዚህ አንፃር መውሊድ ማክበር አላህ አላዘዘውም ። ነብዩም አላዘዙበትም ። ሶሐባዎችም አልሰሩትም ።  ከዛ በኀላም የመጡት አራቱም አኢማዎች አልሰሩትም አያውቁትምም ። ታዲያ እንዴት ተጀመረ ከተባለ በ461ኛው አመተ ሂጅሪያ ግብፅ ውስጥ ዑበይዲዎች የተባሉ የሺዓ አንጃዎች ስልጣን ላይ በወጡበት ጊዜ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ለማድረግ ነብዩንና ቤተሰቦቻቸውን እንወዳለን ለማለት የጀመሩት ነው ። የነብዩን መውሊድ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ 6 መውሊድ ነበር የጀመሩት እነርሱም :–
--- የነብዩ መውሊድ
--- የዓልይ   "  "
--- የፋጡማ   "  "
--- የሐሰን      "   "
--- የሑሰይን   "  "
--- የመሪያቸው   "  "   ነበሩ ። እነዚህ ሰዎች ማን ናቸው ካላችሁ አብረን ማንነታቸውን እንይ : –
    ዑበይዲዎች የሚባሉ ሺዓዎች ሲሆኑ ፋጢሚዮች ፣ ቀራሚጣዎች ፣ ኢስማኢሊዮች በመባል ይታወቃሉ ። መሰረታዊ የሆኑ የእስልምናን መርሆች የሚንዱ በዐልይና ኢማሞች በሚሏቸው መሪዎቻቸው ድበር የሚያልፉ አምልኮትን ከአላህ ውጪ ለተለያዩ አካላት አሳልፈው የሚሰጡ እስልምና ግልፅና ድብቅ ሚስጥር አለው እኛ ድብቁን ነው የምናውቀው ነብያቶች ግልፁን ነው የሚያውቁት እሱን መከተል ኩፍር ነው የሚሉ ናቸው ።
በዚህም የመጣ ነብዩ ያስተማሩትን ሸሪዓ ተግባራዊ የሚያደርግን እንደ ካፊር በማየት መግደል ይበቃል ንብረቱም መዝረፍ ይቻላል ይላሉ ። ከዚህ በመነሳት በ300ኛው አመተ ሂጅሪያ አካባቢና ከዛ በኀላ ከዐለም ወደ መካ ለሐጅ የሚመጡትን ሱንይ ሙስሊሞችን በመግደልና በመዝረፍ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የነበሩ ሑጃጆች ከሐጅ እንዲቀሩ ያደርጉ ነበር ። 
በ317ኛው አመተ ሂጅሪያ ተውበት አድርገን ተመልሰናል በሚል ወደ መካ እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው በመግባት የሐጅ ስራ በሚጀመርበት የ8ተኛው የዙልሒጃ ቀን መሪያቸው አቡ ጣሂር የሚባለው ለተከታዮቹ መካ ውስጥ ያገኙትን ሁሉ እንዲያርዱ ትእዛዝ ሰጠ ። ተከታዮቹም የኢሕራም ልብሳቸውን ለብሰው ከተለያየ የዐለም ክፍል የተሰበሰቡ ሑጃጆችን ከነ ኢሕራማቸው አጋድመው እያረዱ ወደ 30000 ( ሰላሳ ሺህ ) የሚሆን ሙስሊም ጨርሱ ።  ጀናዛቸውንም በዘምዘም ጉድጓድና በየቦዩ በመጣል የተከበረውን ካዕባ በሐጅ አድራጊዎች ደም እንዲጨቀይ አደረጉ ። ቀጥሎም መሪያቸው የካዕባን በር ገንጥሎ አውጥቶ ካዕባ ላይ ወጥቶ ቆሞ ዝሆንን ያጠፋው ጌታችሁ የት አለ እኔን ለምን አያጠፋኝም ብሎ በመፎከር ለተከታዮቹ ሐጀረል አስወድን ነቅለው እንዲያወጡ አዘዘ ። ሐጀረል አስወድን ነቅለው ይዘውት ሄደው ለ20 አመት ያክል ቦታውን ባዶ አድርገውት ያቆዩ ናቸው ። እነዚህ ሶዎች ናቸው እንግዲ ታሪካቸውን ከሙስሊሙ አእምሮ ለመፋቅ ነብዩንና ቤተሰቦቻቸውን እንወዳለን በማለት መውሊድን የጀመሩት ።‼
   ታዲያ እነዚህ አካላት የነብዩ ወዳጆች ወይስ ጠላቶች የሚባሉት ?
     ይህ ተግባር የነብዩ ወዳጅ ኹለፋ የኡማው ፈርጥ የሆኑት አቡበከር ፣ ዑመር ፣ ዑስማን ፣ ዐልይ – ረዲየላሁ ዐንሁም – አያውቁትም ።
በመሆኑም አላህን ያመፁ ሶዎች ያመጡት ቢዳዓ ነው የነብዩን ጠላት ትተን ወዳጆቻቸውን በመከተል ሱናቸውን እንተግብር ።

አላህ ሐቅን አውቆ ከሚከተል ባጢልን አውቆ ከሚርቅ ያድርገን ።

በድጋሚ የተለቀቀ !

http://t.me/bahruteka
👉 ሽቶ ተቀብታ የምትወጣ ሴት ዝሙተኛ ናት !

عن أبي موسى الأشعري – رضي الله عنه – قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم –

" أيُّما امرأةٍ استعطَرَت فمرَّت علَى قومٍ ليجِدوا من ريحِها ؛ فَهيَ زانيةٌ ".

أخرجه النسائي بسند حسن

አቡ ሙሳ አልአሽዓርይ ባወሩትና ኢማሙ ነሳኢ በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ : –

" የትኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ ሽታዋን እንዲያገኙ በሰዎች መሀል ካለፈች እሷ ዝሙተኛ ናት " ·

http://t.me/bahruteka
✅ ወንጀል ልብን ያሳምማል ካልሆነም ይገላል !

يقول ابن القيم – رحمه الله –

" الذنب إما أن يميت القلب أو يمرضه مرضا مخيفا أو يضعف قوته "

الداء والدواء (1/178)

ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሉ – እንዲህ ይላል : –

" ወንጀል ልብን ይገላል ወይም የሚፈራ አይነት ህመምተኛ ያደርገዋል ። ወይም ሀይሉን ያደከመዋል "።

http://t.me/bahruteka
جمعية أهل السنة الاتيوبية.
بيان عن اجتماع علماء السنة في أديس أبابا
عُقد اجتماع لعدد من علماء السنة في أديس أبابا خلال يومي ٢ و٣ من شهر ربيع الأول ١٤٤٨هـ، وتناول اللقاء عددًا من القضايا المهمة
وقد أكد العلماء المجتمعون على جملة من القضايا المهمة من أبرزها:
_وجوب الاعتصام بكتاب الله وسنة رسوله ﷺ، بفهم السلف الصالح، والرجوع إلى ما كان عليه الصحابة والتابعون ومن تبعهم بإحسان.
_الحرص على طلب العلم الشرعي ، لا سيما مذاكرة العلم بين المشايخ والعلماء والأساتذة، وبحث المسائل العلمية ومناقشتها فيما بينهم .
التآخي في الله، وتعزيز المحبة والمودة والتعاون بين علماء السنة والسلفيين ، ونبذ كل ما يؤدي إلى التباغض والتنازع.
_البعد عن أسباب الخلاف والفرقة، ومعالجة ما يقع من الاختلاف بالرجوع إلى الكتاب والسنة مع التحلي بالعدل والإنصاف
_وحذر العلماء من التدخل في شؤون المراكز السلفية والمدارس والسعي إلى التفريق بين صفوف السلفيين. ،
_الحذر من التسرع في التحذير ممن عرفوا بالسنة والبعد عن تصنيفهم، وإصدار الأحكام عليهم أو وصف أحد منهم بأنه «ليس بسلفيً» أو نحوه من غير حجة ولا برهان ولا رجوع إلى كبار مشايخ السنة ، لما قد يترتب على ذلك من الفرقة والفتنة.
_الحذر من ممارسة الضغوط وإرهاب السلفيين بطلب حذف المقاطع والصوتيات أو منع نشرها بدعوى أن صاحبها ليس سلفيًا، أو أنه مع فلان لحصول خلافات شخصية أو تصفية حسابات لا صلة لها بالعقيدة والمنهج.
_ وجوب المحافظة على التميز عن أهل الأهوء والبدع وعدم الاحتكاك بهم
وبخصوص الأخ علي حسين، فقد أكد العلماء أن ما ظهر لهم من حاله أنه قد حسنت توبته هكذا نحسبه والله حسيبه ولا نزكي على الله أحدا ، وأنه من إخوانهم السلفيين.
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
جمعية أهل السنة الاتيوبية. بيان عن اجتماع علماء السنة في أديس أبابا عُقد اجتماع لعدد من علماء السنة في أديس أبابا خلال يومي ٢ و٣ من شهر ربيع الأول ١٤٤٨هـ، وتناول اللقاء عددًا من القضايا المهمة وقد أكد العلماء المجتمعون على جملة من القضايا المهمة من أبرزها:…
🔷ከሱና ኡለሞች የተሰጠ መግለጫ

በረቢዕ አል'አወል 2 እና 3 / 1448 ዓ.ሂ. የሱና ኡለሞች በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች በማካሄድ፣ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።

አጽንኦት ሰጥተው ከመከሩባቸውና ውሳኔ ካስተላለፉባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-

1.  በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ ላይ በመመስረት፣ የአላህን መጽሐፍና የመልእክተኛውን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ሱና አጥብቆ መያዝ፤ ለማንኛውም ጉዳይ ሶሃቦች፣ ታብእዮች፣ እነርሱንም በመልካም ወደ ተከተሉት ጎዳና መመለስ ግዴታ እንደሆነ፤

2.  ሸሪዓዊ እውቀትን ለመፈለግ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳደር፤ በተለይም ከመሻይኽ፣ ከኡለሞችና ከኡስታዞች ጋር በመሆን ኢስላማዊ እውቀቶችን መተዋወስ። በኢስላማዊ የሸሪዓ ጉዳዮች ላይ እርስ በርስ መወያየት እንደሚገባ፤

3.  ለአሏህ ብሎ በመዋደድ፤ በሱና አሊሞችና በሰለፊዮች መካከል ፍቅርና ትብብርን ማጠናከር ፤ ወደ ጥላቻና ጭቅጭቅ ከሚወስዱ ነገሮች መራቅ እንደሚገባ፤

4.  የልዩነትና የግጭት መንስኤዎችን መራቅ፤ ልዩነቶች ሲከሰቱ፣ ፍትህና ሐቅን ተላብሶ ወደ ቁርዓን እና ወደ ሐዲስ በመመለስ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ፤

5.  በመርከዞችና በመስጊዶች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት፤ በመርከዞችና በመስጊዶች የውስጥ ጉዳይ የማይመለከተው አካል ጣልቃ መግባት፣ የሰለፍያን አንድነት የመከፋፈል ሙከራ በመሆኑ፣ ከዚህ ተግባር መራቅ እንደሚገባ፤

6.  በሱና የሚታወቁ (ወንድምና እህቶችን) ፈጥኖ ከመፈረጅ መጠንቀቅ፤ ይህ ተግባር መከፋፈልንና ፊትናን ስለሚያስከትል፣ ጉዳዩን ወደ ታላላቅ ኡለሞች መመለስ እንደሚገባ፤

7.  ‘ባለቤቱ ሰለፊ አይደለም’፣ ‘እርሱ ከእገሌ ጋር ነው' በሚል ወይም በበቀል ቪዲዮዎችንና የድምጽ ቅጅዎችን ከቻናል ላይ እንዲያነሱ ከመጠየቅ መቆጠብ፤

8.  ከዝንባሌና ከፈጠራ ባለቤቶች ጋር ያለውን ልዩነት የመጠበቅ ግዴታን መወጣትና ከእነርሱ ጋር ከመለካለክ መቆጠብ ፤

9.  ወንድማችን ዓሊ ሁሴንን በተመለከተ፤ የሱና ኡለሞች ባደረጉት ክትትል መሰረት ተጸጽቶ መመለሱን፣ ጸጸቱም ያማረ መሆኑንና ከሰለፊ ወንድሞቻቸው አንዱ እንደሆነ አረጋግጠዋል።

እኛ  እርሱን  የምንመለከተው በዚህ መንገድ ነው ፤ ፈራጁ አሏህ ነው። በአሏህ ፊት ማንንም አናወድስም።

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷ከሱና ኡለሞች የተሰጠ መግለጫ በረቢዕ አል'አወል 2 እና 3 / 1448 ዓ.ሂ. የሱና ኡለሞች በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች በማካሄድ፣ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል። አጽንኦት ሰጥተው ከመከሩባቸውና ውሳኔ ካስተላለፉባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- 1.  በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ ላይ በመመስረት፣ የአላህን መጽሐፍና የመልእክተኛውን…
🔹 በአቋም መግለጫው ላይ የማነሳቸው ነጥቦች

በመጀመሪያ ደረጃ ከሀገራችን የሰለፍይ መሻኢኾች ውስጥ የተወሰኑት ለሰለፍያ ዳዕዋ ይጠቅማል ብለው በሚያስቡት ነጥብ ላይ ተነጋግረው ምክረ ሀሳብ ለመስጠት ጊዜያቸውን ገንዘባቸውን እውቀታቸውና ጉልበታቸውንም ጭምር መሰዋእት አድርገው ተሰባስበው ጠቃሚ ነው ያሉትን የአቋም መግለጫ በማውጣታቸው አላህ ስራቸውን በመልካም ስራ መዝገባቸው ላይ እንዲያሰፍራለቸው እለምነዋለሁ ።
በመቀጠል መግለጫው በዐረብኛና በአማርኛ የተለቀቀ ሲሆን ዋናው ዐረብኛው ሆኖ አማርኛው ትርጉም ይመስለኛል ። ይህ ከሆነ በዐረብኛውና በአማርኛው ትርጉም መካከል የተወሰኑ ልዩነቶች አሉ ። ከእነዚህ ውስጥ በዐረብኛ የተወሰኑ ዑለሞች የሚለውን በአማርኛ ዑለሞች ተብሎ ተተርጉሟል ። እንደሚታወቀው የሀገራችን ሰለፍይ ማህበረሰብ አብዛኛው አማርኛ ነው የሚያነበው ። በመሆኑም የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳይፈጠር በዚህና በተወሰኑ ነጥቦች ላይ ሀሳብ ለመስጠት ወደድኩ ። እነርሱም የሚከተሉት ናቸው :–
1 – " ከሱና ዑለሞች የተሰጠ መግለጫ " የሚለው አብዛኛው ሰው የሚረዳው የሀገራችን ሁሉም የሱና ዑለሞች እንደተገኙ አድርጎ ሊወስደው ይችላል ። ይሁን እንጂ የተገኙት እኔ በማውቀው ከሀገራችን የሱና ዑለሞች ውስጥ ግፋ ቢል 1/3 የሚሆኑት ናቸው ። ስብሰባው ተነግሯቸው በዑዝር ምክንያት የቀሩና ያልሰሙም በጣም ብዙ ናቸው ። የዐረብኛው ፅሑፍ ይህን ሊያስዳ በሚችል መልኩ የተፃፈ ነው ።
2 – የተገኙት መሻኢኾች የቋም መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ነው ብለው ካመኑ የአቋም መግለጫውን ላልተገኙት ልከው የሚጨመርም የሚቀነስም ካለ ሐሳብ እንዲሰጡበት አድርገው የተለቀቀው ከዛ በኋላ ቢሆን ኖሮ የተሻለ ነበር የሚል እምነት አለኝ ። ይህም የሰለፍዮችን ሶፍ ለመጠበቅ በጣም የቀረበ ነበር ብዬ ስለማምን ነው ።
3 – የዐሊ ሑሰይንን ጉዳይ በተመለከተ መስከረም15/2018 ላይ መሻኢኾች ተሰብስበው ያስተላለፉትን ውሳኔ ሸይኽ ዩሱፍ ለዐሊ ሑሰይን በቴሌግራም የላከለት ሲሆን በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ አንብቡት :–
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/7602

ከዛ በኋላም ቢሆን በዋነኝነት ከዛ በፊት ሲዘምተባቸው በነበሩ ሰዎች ላይ ውስጥ ለውስጥ ፊትናውን እስካሁንም እያሰራጨ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ያለ በመሆኑ አሁን የተሰጠው ምስክርነት ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጋጭ ነው እላለሁ ።
4 – በመግለጫው ላይ መግለጫውን የሰጡ ዑለሞች ስም ዝርዝርና ፊርማ ቢኖር ኖሮ ጥሩ ነበር ብዬም አምናለሁ ።
በተረፈ የመሻኢኾቹን መግለጫ ቀደም ብዬ ሼር ያላደረግሁት በሀጃ ላይ ስለነበርኩ ዘግይቶ ስለደረሰኝ ሲሆን ካነሳኋቸው ሀሳቦች ውጪ በጥቅሉ ጥሩ ነው እላለሁ ።
በተረፈ እነዚህን ሀሳቦች ያነሳሁት በስብሰባው ላይ በዑዝር ምክንያት ሳልገኝ ቀርቼ የነበር በመሆኑ ሲሆን ከዑለሞችም ስላልሆንኩኝ ዑዝር ባይኖረኝም መገኘቴ አስፈላጊ እንዳልነበር አምናለሁ ።

http://t.me/bahruteka
👉 ለፈገግታ !

ባልና ሚስት ቁጭ ብለው እየተጫወቱ ሳለ ሚስት ለባልዋ እስኪ እውነቱን ንገረኝ ያኔ እኔን ለትዳር ስተጠይቀኝ ማን ነበር የጠቆመህ ትለዋለች ።
ባልም ቀበል አድርጎ ማን እንደሆነ አላስታውስም ምክንያቱም ጠላቶቼ ብዙ ናቸውና ብሏት እርፍ ! ።

http://t.me/bahruteka
👉 ዱዓእ የነብያቶች መሸሸጊያ !

قال العلامة السعدي – رحمه الله –

" الدعاعاء سلاح الأقوياء والضعافاء ، وملاذ الأنبياء والأصفياء، وبه يستدفعون كل بلاء "

مجموع مؤلفات الشيخ (23//736)

ኢማሙ አስሰዕዲይ የተባሉ ታላቅ ዓሊም እንዲህ ይላሉ : –

" ዱዓእ የጠንካሮችና የደካሞችም መሳሪያ ነው ። የነብያቶችን የንፁሃን መሸሸጊያም ነው ። ሁሉንም በላእ የሚከላከሉትም በሱ ነው " ።

http://t.me/bahruteka
Audio
የፉሲለት ምእራፍ ክፍል 01

" አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው ፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
ሸይኽ ሙሐመድ አወል ባህር ዳር ከነሲሐወች ጋር በ እጅና ጓንትነት አብረው ይሰራሉ።

ከነሲሓወች ጋር አብረን አንሰራም የሚሉ እንቶኔወች ግን ሸይኻችን እያሉ ያሞኳሿቸዋል።

አንድ ወፍጮ ባለ ሁለት ቋት እንደማለት ነው ባንድ ጎኖ በርበሬ በልለኛው ጎኖ ሽሮ እንደሚፈጨው።

ለማንኛውም ስሌት እናስተካክል ወይ ነሲሐወችን አንወርፍ ወይም አጋሮቻቸውም ይወረፉ(ፍትሕ ላስተሳሰብ)

https://t.me/abumuazhusenedris
#መውሊድን_ከተለያዩ_ሸሪዓዊ
ምክንያቶች አንጻር አላከብርም!
   ከብዙው በጥቂቱ 20 (ሀያ)
     ምክንያቶችን ልጥቀስ።
      ➚➚➚➚➚➚➚

❶ኛ,
#መውሊድ በሸሪዓችን #መሠረት የሌሌለው ማለትም #ቁርኣንና_ሐዲሥ ላይ ያልተደነገገ አዲስ #መጤ ፈጠራ ስለሆነ፣

❷ኛ,
#መውሊድ መከበር ያለበት ጠቃሚ #ኢስላማዊ በዓል ሁኖ በነበር፤
ከእኛ
#በፊት ያሉ ደጋግ የነቢዩ ﷺ
➼ ባለቤቶች፣
➼ ባልደረቦች (ሶሐቦች)፤
➼ ታቢዒዮችና
➼ አትባዑ ታቢዒዮች
#ባከበሩት ነበር።
#ስለዚህ ያኔ ለነርሱ #ዲን ያልነበረው፤
ዛሬ ለእኛ
#ዲን አይሆንምና አላከብርም!

❸ኛ, ከነዚህ
#ትውልዶች በኋላ የመጡ #ታላላቅ የኢስላም #ሊቃውንቶችና #ሙሐዲሦች ስላላከበሩት፣

❹ኛ,
#መውሊድን የጀመሩት ሶሐቦችን #በመሳደብ በግንባር ቀደምትነት የሚታወቁት #ሺዓዎች የሆኑት ፋጢሚዶች ስለሆኑ፣

❺ኛ,  አንድ ነገር በራሱ
#መልካም ከሆነና የተጀመረበት #አላማ ለመልካም ከሆነ፤ ምንም እንኳን #ጀማሪዎቹ መጥፎ ቢሆኑም ነገሩ #ያልተፈቀደ ላይሆን ይችላል። #መውሊድን እነዚህ የፋጢሚይያህ #ሺዓዎች የጀመሩበት ዐብይ ምክንያት ግን፤ #በዋናነት የራሳቸውን #ብልሹ እምነት በሌላው ላይ ለመጫን #መሸጋገሪያ ድልድይ ይሆናቸው ዘንድ እና ከሱንናው #ማኅበረሰብ ጋር ያለውን #ልዩነት አጥብበው በፖለቲካው ዘርፍም የስልጣን #አድማሳቸውን ለማስፋት ነበር። ስለዚህ ለዚህ እኩይ #የሺዓ አላማ የተጀመረን #መውሊድ አላከብርም!

❻ኛ,
#መውሊድ በሸሪዓችን #መሠረት የሌለው #በዓል ስለሆነ፤ ከፊሉ #ሙስሊም አከብራለሁ ሲል፣ ከፊሉ ደግሞ አላከብርም ሲል፤ #አንድ መሆን የሚገባውን #ሙስሊም በዚህ ክፍተት ብቻ #እንዲከፋፈል ጉልህ ሚና የተጫወተ #መጤ በዓል ነው።
#መልካም ነገር ቢሆን ኑሮ፤ #ሙስሊሙን አንድ ያደርጋል እንጅ አይከፋፍልም ነበር!

❼ኛ, 
#እስልምናዬ ሙሉ መሆኑ ተነግሮኛል። #ስለሆነም በውስጡ ያልተደነገገን ነገር በራሴ እሳቤ #አልጨምርም!

❽ኛ,
#መውሊድ ጠቃሚ በነበር #አላህና መልዕክተኛው ﷺ በነገሩን ነበር። እነርሱ ለእኛ ከእኛ ይልቅ #ይበልጥ ጠቃሚውን ያውቃሉና!

❾ኛ,
#ከመልዕክተኛው ሱንና ውጭ የሆነን #ነገር መፈጸም፤ እርሳቸው #ባላዘዙበት ነገር ወደ ርሳቸው #ለመቃረብ መሞከር፤ #እርሳቸውን መውደድ ሳይሆን #መቃረን  ስለሆነ፣

❿ኛ,
#በሸሪዓው ውስጥ የሌለን #መውሊድን ማክበር፤ #ሸሪዓውን ጉድለት #ያለበት ስለሚያስመስል፣

⓫ኛ,
#በእስልምናችን ውስጥ የተደነገጉ ሁላችንንም መላውን #ሙስሊም አንድ የሚያደርጉን ሁለት እውቅ #አመታዊ ዒዶች ስላሉን፣

⓬ኛ,
#መውሊድ በራሱ ቢድዓ ከመሆኑም #ባሻገር፤ በሚከበርበት እለት ደግሞ ከርሱ የባሱ #ቢድዓዎች ይፈጸማሉ።

⓭ኛ,
#በመውሊድ እለት ከራሱ ተጨማሪ ከሚታከሉ #ቢድዓዎች ባሻገር፤ #ከእስልምና ሊያስወጡ የሚችሉ #ሽርኮች መፈጸሚያ #ማዕከል በመሆኑ፣

⓮ኛ, መልዕክተኛውን ﷺ
#መውደድ ማለት ሱናቸውን #በቀንጣጤ አጥብቆ መያዝና ትዕዛዛቸውን #መፈጸም እንጅ፤ ልደታቸውን #ማክበር ባለመሆኑ፣

⓯ኛ, የርሳቸውን
#ልደት ማክበር፤ #አላዋቂዎች ደግሞ የሚወዱትን ሰው #ልደት እንዲያከብሩ በር #ከፋች በመሆኑ፣

⓰ኛ, እፁብ
#ድንቅ የሆኑ #በሸሪዓችን የተደነገጉ ብዙ ኢስላማዊ #እሴቶች እያሉን፤ ቅንጣት #መሠረት የሌለውን በዓል መሠረት ያለውን #አስመስለን ስናከብር፤ #ሙስሊም ላልሆኑ ወገኖች መተላለፍ ያለበትን #መልዕክት ወደ ጎን በመተው #መተላለፍ የሌለበትን መልዕክት #እያስተላለፍንላቸው በመሆኑ፣

⓱ኛ,
#መውሊድ የሚከበርበት ረቢዑል አወል 12፤ #ትክክለኛው የልደት ቀናቸው ባለመሆኑ #እንዳውም ይህ ቀን በትክክል #የሞቱበት ቀን ነበር። ስለዚህ #ልደታቸውን ነው ወይስ #ሞታቸውን እያከበርን ያለነው?! #የሚከበርበት ቀን ራሱ የተገደበና በውል #የታወቀ አለመሆኑ በራሱ፤ #መውሊድ በሸሪዓችን #መሠረት የሌለው አዲስ #መጤ ቢድዓ ለመሆኑ #አመላካች ነው። #ሁሉም ሸሪዓዊ ትዕዛዛት #የአፈጻጸም ህግና ደንብ አላቸው። እርሱ (መውሊድ)ግን የለውም፣ #ምክንያቱም ሰዋዊ ስለሆነ!!!

⓲ኛ, #በመውሊድ ምክንያት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ #ሲከፋፈል የሚያይ፤ በቂ #እውቀት የሌለው #ሙስሊም ማኅበረሰብ #በእስልምናው እንዲጠራጠር #ሰበብ ስለሚሆን።

⓳ኛ, #ሙስሊሞች በሸሪዓቸው ባልተደነገገው #የመውሊድ በዓል ሳቢያ ሲጨቃጨቁ፤ #አልፎም ለድብደባና ለሰፊ ልዩነት ሲዳረጉ የሚያይ፤ #እስልምናን ለመቀበል ጉጉት የነበረው #ሙስሊም ያልሆነ ወገን፤ #እስልምናን እንዲጠላና እንዲርቅ፣ እንዲሁም #ሙስሊሞችን በመጥፎ ምስል እንዲስል #ሰበብ ስለሚሆን፣

⓴ኛ, #እስልምና እንድንተገብራቸው ያዘዘን ብዙ በጎ #ተግባራት አሉ። እንኳን አዲስ #ተጨማሪ ነገር ልፈጥር ይቅርና፤ እነዚያን #መሠረት ያላቸውን የታዘዝኳቸውን ሰናይ #ተግባራት አሟልቼ የማልፈጽም ስለሆንኩ እንኳን ፈጽሜ #የማልጨርሳቸውን ብጨርሳቸው እንኳን፤ እነርሱኑ #በተደጋጋሚ እፈጽማለሁ እንጅ ሌላ አዲስ #ፈሊጥ አላመጣም። ይህን የማደርገው #መልዕክተኛውን ﷺ ስለምወድ #እንጅ ስለምጠላ አይደለም።

𝓬𝓸𝓹𝔂

<===/====/====/====/===>
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
<\\\>
📶 ሰበር

🫱 ዛሬ ከመጝሪብ በኋላ ቆይታ ከተከበሩ መሻኢኾቻችን ጋር በውቧ መስጂዳችን መስጅደ ሰላም ኢንሻ አሏህ

🎙️ ሸይኽ ሙሀመድ ሐያት📚

🎙️ ሸይኽ ሑሰይን ከረም 📚

▶️ በአካል መታደም ለማትችሉ ቀጥታ ስርጭታችን እንደተጠበቀ ነው❗️

https://t.me/kombolcha_selam_mesjd
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✅ ችኮላ ሰዎች ዘንድ ያለህን ቦታ ያሳጣል !

ሸይኽ ሙሐመድ አማን አል ጃሚ – አላህ ይዘንላቸውና – እንዲህ ይላሉ : –

ስርአት ፣ እርጋታና ለነገሮች አለመፍጠን አንድን ሰው ግርማ ሞገስና በአቋም መፅናትን ይጨምርለታል ። ችኮላ ግን አንድን ሰው ሰዎች ዘንድ ያለውን ክብር እንዲያጣ ሊያደርገው ይችላል " ።

http://t.me/bahruteka