ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.4K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
ባጢልን በመተው ወደ ሓቅ መመለስ
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ
✔️ አዲስ እና ወሳኝ ሙሓዶራ

ርዕስ:- «ባጢልን በመተው ወደ ሓቅ መመለስ »

🎤ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ -ሐፊዞሁ'ሏህ-

🫱 "በሓራ ሰለፍዮች የዳዕዋና ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ላይ የተደረገ"

⌚ 41 ደቂቃ ከ 35 ሴኮንድ ብቻ !

📆 ጁሙዓ ምሽት ነሐሴ / 𝟐𝟐 / 𝟐𝟎𝟏𝟖

✈️https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አብራር አወል ( Abu ubeyda) (Abu Ubeyda)
ሱናን አጥብቆ መያዝ እና ግዜን በአግባቡ መጠቀም
🎤ዶ/ር ሸይኽ ሁሰይን ቢን ሙሀመድ ሀፊዘሁላህ
ልዩ አዲስ ሙሃዶራ

ሱናን አጥብቆ መያዝ እና ግዜን በአግባቡ መጠቀም በሚል ሪእስ የተደረገ

ነሓሴ 27/12/2018

🕌 በአል-ወሰጢያህ መድረሳ እና መርከዝ

🎤በዶ/ር ሸይኽ ሁሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ስልጢይ


https://t.me/AbraribnAwal
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል ሶስት

— የሶሓቦች ደረጃ በነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – ምስክርነት !

አላህ ከሰዎች ነብያቶችን መርጦ ወደ ሰው ልጆች በቃሉ ላካቸው ። በዚህም ነብያቶች በአላህና በሰው ልጆች መካከል አገናኝ ሆኑ ። ከተቀሩት ሰዎች መርጦ ደግሞ ለነብያቶች ሀዋሪያት አደረገ ። የነብዩ ሙሐመድ ባልደረቦች (ሶሓቦች) አላህ ለነብዩ ረዳትነት የመረጣቸው ምርጥ ትውልዶች ነበሩ ። የነብዩን መልእክት ባለበት ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ውድ ሕይወታቸውን ፣ ክብራቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ቤዛ አድርገዋል ። ለዚህ ዲን ሲሉ አንገታቸው ተቀልቷል ፣ ገላቸው ተከታትፏል ። አጥታቸው ተሰብሯል ። በደማቸው የነብዩ ሸሪዓ ለምልሞ ለዓለም ደርሷል ። የአላህ መልእክተኛ ስለነዚህ ባልደረቦቻቸው ከተናገሯቸውና የሰደባቸውንና ክብራቸውን የነካን ምን እንዳሉ በሚቀጥሉት ሐዲሶች እንመልከት : –

عن أبي سعيد رضي الله عنه قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم –:

«لَا تَسُبُّوا أَحَدًا مِنْ أَصْحَابِي، فَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَوْ أَنْفَقَ مِثْلَ أُحُدٍ ذَهَبًا، مَا أَدْرَكَ مُدَّ أَحَدِهِمْ وَلَا نَصِيفَهُ»

أخرجه البخاري ومسلم .
" ከሶሓቦቼ አንዱንም አትሳደቡ ከናንተ ውስጥ አንዳችሁ የኡሑድ ተራራን የሚያክል ወርቅ በአላህ መንገድ ላይ ወጪ ቢያደርግ (የሶሓቦቼን) የአንዳቸውን እፍኝ ወይም ግማሹ አይደርስም " ።
عن عائشة أم المؤمنين قالت: قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم –:

«مَنْ سَبَّ أَصْحَابِي فَعَلَيْهِ لَعْنَةُ اللهِ وَالْمَلَائِكَةِ، وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ» .
وقد رواه الإمام أحمد في "مسنده"، والإمام الترمذي وقال: حسن غريب،

" ሶሓቦቼን የተሳደበ በሱ ላይ የአላህ የመላኢካዎችና የሰዎችም ባጠቃላይ እርግማን ይውረድ "።

عن عبد الله بن مغفل – رضي الله عنه– قال :
قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم–:

«اللهَ اللهَ فِى أَصْحَابِي، اللهَ اللهَ فِى أَصْحَابِي، لَا تَتَّخِذُوهُمْ غَرَضًا بَعْدِي، فَمَنْ أَحَبَّهُمْ فَبِحُبِّي أَحَبَّهُمْ، وَمَنْ أَبْغَضَهُمْ فَبِبُغْضِي أَبْغَضَهُمْ، وَمَنْ آذَاهُمْ فَقَدْ آذَانِي، وَمَنْ آذَانِي فَقَدْ آذَى اللهَ، وَمَنْ آذَى اللهَ فَيُوشِكُ أَنْ يَأْخُذَهُ».

" በሶሓቦቼ ጉዳይ አላህን ፍሩ, (እኔ ከሞትኩ በኋላ) ክብራቸውን በመንካትና በመስደብ አዛ በማድረግ ኢላማ አድርጋችሁ አትያዟቸው ( በመጥፎ ነገር ወደነርሱ አታነጣጥሩ) እነርሱን የወደደ እኔን ለመውደዱ ነው የወደዳቸው ። እነርሱን የጠላቸው እኔን ለመጥላቱ ነው የጠላቸው ። እነርሱን አዛ ያደረገ እኔን አዛ አደረገ ! እኔን አዛ ያደረገ አላህን አዛ አደረገ ! አላህን አዛ ያደረገ ሊዘው ይቀርባል " ።

ጮሌ በምልክት ይገባዋል እንደሚሉት የነብዩና የሶሓቦች ወዳጆች ሶሓቦችን ለመውደድና ለማክበር አንድ የቁርኣን አንቀፅ ወይም የነብዩ ሐዲስ ይበቃቸዋል ። እነዚህ ስለሶሓቦች ክብርና እነርሱን መስደብ ወይም አዛ ማድረግ አደጋው ምን እንደሆነና ባለቤቱ ለአላህ እርግማንና ለሱ ቅጣት ራሱን የዳረገ መሆኑን የሚያሳዩ የነብዩ ንግግሮች ናቸው ። ሁሉንም እንዘርዝር ብንል መፅሐፍ ማሳተም ግድ ይለናል ። አላህ ካለ በሚቀጥለው ክፍል የሰለፍ ዑለሞች የሶሓቦችን ክብር የሚነካና የሚተች ሰውን አስመልክተው የሰጧቸውን ብይኖች እናያለን ።

https://t.me/bahruteka
Audio
የዱኻን ምእራፍ ክፍል 02

" ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
✅ታላቅ የምስራች ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته


በመጀመሪያ ለዐለማቱ ጌታ አላህ ምስጋና ይገባው!
በመቀጠልም ከዚህ በፊት በተለያዩ መድረሳዎች ሲቀሩ የነበሩት ደርሶችና ተጨማሪ አዳዲስ ኪታቦች በአድስ መልኩ ቅዳሜ(ነሀሴ-30) ጀምሮ የሚሰጡ ይሆናል። ጊዜያችንን አመቻችተን በሚቀርበን ቦታ በመገኘት ድናችንን እንገንዘብ!

የአላህ መልዕክተኛ ሲናገሩ፦
من يريد الله به خيرا يفقهه في الدين
"አሏህ መልካም የሻለት ሰው ድኑን ያስገነዝበዋል"

الجهل عار عار
لا يرضى به إلا حمار
ማሳሰቢያ
✅ደርሶቹ የሚሰጡበት ጊዜ👉 ከመጝሪብ-ዒሻ
✅ የሚሰጡበት ቦታ 👉 ዳቶ ፣ ቲቲሲና ተማሪዎች መድረሳ
✅ደርሱን የሚሰጡት፦
↪️ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ደሴ
↪️ኡስታዝ ዐብዱልሀሚድ

👉👉👉ዝርዝር ፕሮግራሙን በፎቶው ላይ ተመልከቱ!

ከሱብሂ በኋላ እንድሁም በቀኑ ክፍል የሚወጡ ፕሮግራሞችን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ለሌሎች ሰዎች በማድረስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!


🔈🔈🔈🔈🔈🔈🔈🔈🔈🔈
https://t.me/hutemariwochchannel
✅ ልብህ እንዲርስ ከፈለግህ የየቲምን ራስ አብስ !

عن أبي هريرة – رشي الله عنه قال : قال رسول الله - صلى الله عليه وسلم –

" إنْ أردْتَ تَلْيِينَ قلبِكَ، فَأَطْعِمْ المِسْكِينَ، و امْسَحْ رَأْسَ اليَتِيمِ "

أخرجه إمام أحمد كما في سلسلة الصحيحة

— አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢማሙ አሕመድ በዘገቡ, ሸይኽ አልባኒ ሶሒሕ ባሉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ : –

" ቀልብህ እንዲርስልህ ከፈለግህ ምስኪናችን አብላ, የየቲምንም ራስ አብስ " ።

https://t.me/bahruteka
✅ ከአላህ ውጪ ያለን ነገር ከሚያመልክ ሰው ህይወት የእንሰሳ ህይወት ይሻላል !

يقول ابن القيم – رحمه الله –

" لا حياة لمن أعرض عن الله واشتغل بغيره ، بل حياة البهائم خير من حياته " .

الداء والدواء ص (84)

ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" አላህን ( ከመገዛት) አፈንግጦ ከአላህ ውጪ ያለን በመገዛት የተጠመደ ህይወት የለውም ። ይልቁንም የእንሰሳዎች ህይወት ከሱ ህይወት ይሻላል "።

https://t.me/bahruteka
Audio
የጃሲያ ምእራፍ ክፍል 01

" የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል አራት

ሙሐመድ ሓሚድን ጥብቅና የቆመው ሰይድ ቁጥብ አላህ መርጦ ያላቃቸውን ነብዩላሂ ሙሳን ላንቋሸሸበት የነብዩን ባልደረቦች ላዋረደበት የሙስሊሙን ኡማ በግልፅ ላከፈረበት የአላህን ብቸኛ ተመላኪነት ለናደበትን ተራራ ለማይሸከመው ወንጀል ነው ። አላህ ካለ ይህን በሙዋዘና በማጣፋት ጥብቅና የቆመበትን ስራው በመረጃ ድባቅ እንመታለን ። ከመምታታችን በፊት ስለ ነብያቶችና ስለነብዩ ባልደረቦች አላህ በቁርኣኑ ከተናገራቸው የአላህ መልእክተኛ ሶሓቦቻቸውን የሚሳደብንና ክብራቸውን የሚነካን በተመለከተ የተናገሩትን ባለፉት ክፍሎች አይተናል ።
አላህ ካለ በዛሬው ክፍል የኢስላም ሊቃውንቶች የነብዩን ባልደረቦች ክብር የሚነካን አስመልክተው ከተናገሯቸው ንግግሮች የተወሰኑት ካየን በኋላ የሰይድ ቁጥብ ንግግሮችን በሙሉ ከራሱ ኪታቦች በሙጀለድና ገፅ መረጃ እያቀረብን ውድቅ እናደርጋለን ።

قال الجَلالُ البلقينيُّ : أن سب الصحابة داخِلٌ تحتَ مُفارَقةِ الجَماعةِ، وهو الابتِداعُ المَدلُولُ عليه بتَركِ السُّنَّةِ، فمَن سَبَّ الصَّحابةَ رضي الله عنهم أَتى كَبِيرةً بلا نِزاعٍ] اهـ
.
الزواجر 3810/2

ኢብኑ ሀጀር አል ሀይሰሚይ የተባለ ዓሊም አልጀላል አልበልቂኒ ከተባለ ዓሊም ይዞ እንዲህ ይላል : –

" ሶሓቦችን መሳደብ ( ከሱና ) ጀማዓ መውጣት ውስጥ ይገባል ። ያ እሱ ሱናን በመተው ቢዳዓ ማምጣት መሆኑ መረጃ የመጣበት ነው ። ሶሓቦችን የሰደበ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ መግባቱ በዑለሞች መካከል ልዩነት የለበትም " ።
قال الإمام أبو زُرعة الرازي - رحمه الله –

" إذا رأيتَ الرجلَ ينتقص أحدًا من أصحاب رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم فاعلم أنه زِنديق؛ وذلك أن الرسولَ صلى الله عليه وآله وسلم عندنا حق، والقرآنَ حق، وإنما أدى إلينا هذا القرآنَ والسننَ أصحابُ رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم. وإنما يريدون أن يجرحوا شهودَنا ليبطلوا الكتابَ والسنةَ، والجرحُ بهم أولى، وهم زنادقة " اهـ .

الكفاية ص (49)

ኸጢቡል በጝዳድይ የተባለ ዓሊም ከአቡ ዙርዓ አርራዚ የተባለ ታላቅ የሐዲስ ሊቅ ይዞ እንዲህ ይላል : –

" አንድ ሰው የነብዩን ባልደረቦች ክብር በሚያጎድል መልኩ ሲናገር ካየህ እወቅ እሱ ሙናፊቅነቱ ግልፅ የወጣ ነው ። ምክንያቱም እኛ ዘንድ የአላህ መልእክተኛ ሐቅ ናቸው ። ( ይዘውት የመጡት ዲን ሐቅ ነው) ይዘውት የመጡት ቁርኣንና ሐዲስ ወደኛ ያደረሱት ሶሓቦች ናቸው ። ( የእነርሱን ክብር የሚነኩት ፍላጎታቸው ) ሶሓቦችን ተችተው ቁርኣንና ሐዲስን ውድቅ ማድረግ ነው ። ለመተቸት የተገቡት እነርሱ ናቸው ። እነርሱ ዚንዲቆች ( ሙናፊቅነታቸው ግልፅ የወጣ) ናቸው"።

وقال الإمام أحمد رحمه الله –:

" إذا رأيت رجلا يذكر أحدا من الصحابة بسوء فاتهمه على الإسلام "
.
البداية والنهاية 8 / 142

ኢማሙ አሕመድ ሶሓቦች የሚሳደብን አስመልክቶ እንዲህ ይላል : –

" አንድ ሰው ሶሓቦችን በመጥፎ ሲያነሳ ( ሲያወሳ) ካየኸው በሙስሊምነቱ ጠርጥረው "

و قال بشر بن الحارث –رحمه الله – :

« من شتم أصحاب رسول الله فهو كافرٌ، و إن صام و صلّى و زعم أنه من المسلمين»

الشرح والإبانة ص (162).

ቢሽር ኢብኑ አል ሓሪስ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል :–

" የነብዩን ሶሓቦች የተሳደበ ቢፆምም ቢሰግድም እኔ ሙስሊም ነኝ ቢልም እሱ ካፊር ነው "።


قال الإمام السّرَخْسي – رحمه الله –

«فمن طعن فيهم فهو ملحد منابذ للإسلام دواؤه السيف إن لم يتب »
أصول السرخسي ( 134/2)

ኢማሙ ሰርኸስይ እንዲህ ይላል : –

"ሶሓቦችን የተቸ እሱ እስልምናን የሚዋጋ ሙልሒድ ነው ። መድሀኒቱ ተውበት አድርጎ ካልተመለሰ ሰይፍ ነው " ።

وقال شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله – :

" وذلك أن أول هذه الأمة هم الذين قاموا بالدين تصديقا، وعلما، وعملا، وتبليغا، فالطعن فيهم طعن في الدين، موجب للإعراض عما بعث الله به النبين، وهذا كان مقصود أول من أظهر بدعة التشيع، فإنما كان قصده الصد عن سبيل الله، وإبطال ما جاءت به الرسل عن الله، ولهذا كانوا يظهرون ذلك بحسب ضعف الملة، فظهر في الملاحدة حقيقة هذه البدع المضلة..."

منهاج السنة (1 /18)

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ –ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" የዚህ እማ የመጀመሪያዎቹ ( ሶሓቦች) እነርሱ ናቸው ( የነብዩን) ዲን እውነት ነው በማለት ፣ በማመን ፣ በመስራትና በማድረስ ከፊት የሆኑት ። እነርሱን መተቸት ዲኑን መተቸት ነው ። አላህ ነብያቶችን የላከበትን አልቀበልም ማለትን ግድ ይላል ። ይህ ነበር ተሸዩዕንን ( የሺዓ ዐቂዳን) ግልፅ ያደረጉ ሰዎች አላማ ። አላማቸው ነብያቶች ይዘውት የመጡትን ውድቅ ማድረግና ሰዎች ወደ አላህ ዲን እንዳይገቡ ማገድ ነበር ።… "

قال الإمام الذهبي – رحمه الله – مبيناً حكم الطاعن في الصحابة والساب لهم :

"فمن طعن فيهم أو سبهم فقد خرج من الدين ومرق من ملة المسلمين لأن الطعن لا يكون إلا عن اعتقاد مساويهم وإضمار الحقد فيهم وإنكار ما ذكره الله تعالى في كتابه من ثنائه عليهم وما لرسول الله صلى الله عليه وسلم من ثنائه عليهم وفضائلهم ومناقبهم وحبهم ولأنهم أرضى الوسائل من المأثور والوسائط من المنقول والطعن في الوسائط طعن في الأصل والإزدراء بالناقل ازدراء بالمنقول وهذا ظاهر لمن تدبره وسلم من النفاق ومن الزندقة والألحاد في عقيدته "
الكبائر ص ( 235 )

ኢማሙ ዘሀብይ ሶሓቦችን የሚተችን ሰው ሸሪዓዊ ብይን አስመልክቶ እንዲህ ይላል : –

" ሶላቦችን የተቸው ወይ የሰደበ በርግጥ ከዲን አፈንግጧል ከእስልምና መንገድም ወጥቷል ። ምክንያቱም በሶሓቦች ላይ ምቀኝነትን በመቋጠርና መጥፎነታቸውን በማመን እንጂ ትችት ስለማይመጣ ነው ። …… " እያለ ይቀጥላል ።
ይህ ከዑለሞች ንግግሮች ውስጥ ከባሕር ጠብታ ነው ። ባየናቸው የዑለሞች ንግግሮች ሶሓቦችን መተቸት ፣ ክብራቸውን መንካት ፣ ደረጃቸውን ዝቅ ማድረግ ከእስልምና ሊያወጣ የሚችል መሆኑን አውቀናል ። በጣም የሚያሳፍረው ኢኽዋኖች የነብያትና ሶሓቦችን ክብር በመንካት የሚያዋርድና የአላህና የነብዩ ጠላት የሆኑትን ሺዓዎችን የሚያስደስተውን ሰይድ ቁጥብን ኢማም ( የዲን መሪ ) እያሉ ለትውልድ ማስተዋወቃቸው ነው ።

አላህ ካለ ከዚህ በኋላ የሰይድ ቁጥብ ጥመቶችን ከራሱ ኪታቦች አንድ ባንድ ማየት እንጀምራለን ።

https://t.me/bahruteka
ሰለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?1706372650618
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ለኢብኑ ሙነወር የተሰጠ ምላሽ

ርእስ:- ሠለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
ጥር 17/2016 የተደረገ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ቅድሚያ የአላህን ቃል ቁርኣን ለመማር!!!
ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ አልለተሚይ
አዲሰ ወሳኝ ሙሐደራ

ርዕስ « የዒልም (እውቀት) መጀመሪያው ቁርኣን ነው»

🎙ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ያሲን አልለተሚይ ሐፊዘሁላህ

🕌
ጉንችሬ ከዕብ መስጂድ (ዳሩል ሂጅራ መርከዝ)

🗓 ቅዳሜ ነሐሴ /30/2018 ምሽት ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/medresetulislah
وقد سبقني بالرد عليه الشيخ محمد حياة فجزاه الله خيرا . وكذلك اطلعت على مقالات الشيخ بحر وهي لا تزال متتالية باللغة المحلية وألفيتها مليئة بالأدلة النقلية من الكتاب والسنة وأقوال سلف الأمة . فرفع الله قدره وعافاه وثبته على الكتاب والسنة حتى الممات.
🚫 ተጠንቀቅ/ቂ

— አሮጌ ልብስ ለድሃ
— አሮጌ ጫማ ለድሃ
— አሮጌ ጅልባብ ለድሃ
— አሮጌ ኒቃብ ለድሃ
— ትራፊ ምግብ ለድሃ
— አንተ/ቺ የማትፈልጉት ለድሃ !
ድሃ ማለት ቆሻሻ መጣያ ሳይሆን በሱ ምክንያት የአላህ ውዴታ የምታገኝበት የክብር እንግዳ ነው ። ለዚህ ነው አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ የሚለው : –

{ لَن تَنَالُوا الْبِرَّ حَتَّىٰ تُنفِقُوا مِمَّا تُحِبُّونَ ۚ وَمَا تُنفِقُوا مِن شَيْءٍ فَإِنَّ اللَّهَ بِهِ عَلِيمٌ}
آل عمران ( 92)
" የምትወዱትን እስከምትለግሱ ድረስ በጎን ሥራ (ዋጋውን) አታገኙም ፡፡ ከምንም ነገር ብትለግሱ አላህ ያውቀዋል " ፡፡

አላህ አውቀው ከሚሰሩት ባሮቹ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka
Forwarded from أبو سكينة(أمير)
👉ድንገታኛ ማስታወቂያ

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ

እነሆ ዛሬ ምሽት ከዒሻ ቡሀላ የምንነግራችሁ ትልቅ #ሰርፕራይዝ ስላለን ዒሻን እየሰገድን በሀራ ሰለፍዮች የቴሌግራም ግሩፕ ጎራ በማለት የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ ስንል በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የሀራ ሰለፍዮች የቴሌግራም ግሩፕ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/haraselefi
https://t.me/haraselefi
https://t.me/haraselefi
👆👆👆👆👆👆👆
#joine ይበሉ!!

ሸር
ሸር
ሸር
ሸር በማድረግ ለብዙዋች ተደራሽ እናድርግ
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል አምስት

የሰይድ ቁጥብ ኡማውን ማክፈር በመረጃ ሲረጋገጥ !

ሙሓመድ ሓሚዲን ስለ ሰይድ ቁጥብ ኡማውን ማክፍር ሲናገር በቀጥታ ተናግሮ ሳይሆን ሰዎች በራሳቸው መንገድ በተሳሳተ መልኩ እንደተረዱት በማስመሰል ነው የሚናገረው ። እንደሱ አባባል ሰይድ ቁጥብ ማህበረሰቡ ወደ ጃሂሊያ ተመልሷል ነው ያለው እንጂ በቀጥታ አላከፈረም ። ካለ በኋላ ይህ ንግግሩ ሙስሊሞች ከፍሯል ለማለት ሳይሆን የጃሂሊያ ባህሪ ተላብሷዋል ለማለት ነው ይላል ። ይህ ደግሞ በቁርኣንና ሐዲስ ላይም መጥቷል ብሎ ምሳሌ ሲያደርግ ነብዩ አንዱን ሶሓብይ አንተ የጃሂሊያ ባህሪ አለብህ ብለውታል ። አላህ በቁርኣኑ ሴቶችን የጃሂሊያ ( የመሀይማን) አይነት መገላለጥ አትገላለጡ ብሏቸዋል !!!። እያለ የማይገናኝን አገናኝቶ ስሌት ሰርቶ ሚዛን በሌለው ሚዛናዊነቱ አክፍሮቱን ሊያጣፋ ይፈልጋል ።
ለማንኛውም ስለሰይድ ቁጥብ በዓለም ላይ ያለን ማህበረሰብ በሙሉ ማክፈርና የሙሐመድ ሓሚዲንን ሚዛን የሌለው ሚዛናዊነትን ለማወቅ ሰይድ ቁጥብ በቀጣታ እንዴት እንደሚያከፍር ከራሱ መፅሐፎች እንይ : –

አንደኛ— በምድር ላይ እስልምናም ይሁን ሙስሊሞች እንደሌሉ ሲናገር እንዲህ ይላል: –

"إن المسلمين الآن لا يجاهدون، وذلك لأن المسلمين اليوم لا يوجدون، إن قضية وجود الإسلام ووجود المسلمين هي التي تحتاج اليوم إلى علاج"
الظلال : (3/ 1634)

" ሙስሊሞች ዛሬ ጂሃድ እያደረጉ አይደለም ። ምክንያቱም ሙስሊሞች የሉምና, ዛሬ መፍትሄ ለማምጥት መስራት የሚያስፈልገው የሙስሊሞችና የእስልምና መገኘት ጉዳይ ላይ ነው" ።
ሁለተኛ — ሰይድ ቁጥ የሚመራው ንቅናቄ ምን አላማ አድርጎ መንቀሳቀስ እንዳለበት ሲናገር እንዲህ ይላል : –
"وحركات البعث الإسلامي اليوم فى مفترق طرق ونقطة البدء الصحيحة فى الطريق الصحيح هي أن تتبين الشرط الأساسى لوجود الإسلام أو عدم وجوده، وأن تستيقن أن وجود الإسلام اليوم قد توقف... وأن تعلم أنها تستهدف إعادة إنشاء الإسلام من جديد، أو بتعبير أدق رده مرة أخرى إلى حالة الوجود بعد أن توقف هذا الوجود فترة... "
العدالة الاجتماعية : ص (216)
" በተለያየ መንገድ ዛሬ የሚደረገው እስልምናን የመመለስ እንቅስቃሴ ትክክለኛው አጀማመር በትክክለኛው መንገድ (እንዲሆን) እስልምና መኖሩና አለመኖሩን ማረጋገጥ የመጀመሪያው መስፈርት ነው ። ቀጥሎ ዛሬ እስልምና አለመኖሩ እርግጠኛ መሆን ነው ። ንቅናቄው አላማው ማድረግ ያለበት እስልምናን በአዲስ መልኩ ማስገኘት ነው ። በሌላ ረቀቅ ባለ አገላለፅ ካልነበረበት ለሁለተኛ ጊዜ ወደ መመለስ ነው ……" ።

ሶስተኛ— ሙስሊሞች ባጠቃላይ ወደ ኩፍር የተመለሱ መሆኑንና የሙአዚኖች በሚምበር ላይ ላ ኢላሃ ኢልለላህ ማለት ትርጉም እንደሌለው ሲናገር እንዲህ ይላል : –
  " لقد استدار الزمان كهيئته يوم جاء هذا الدين إلى البشرية بلا إله إلا اللّه. فقد ارتدت البشرية إلى عبادة العباد، وإلى جور الأديان ونكصت عن لا إله إلا اللّه، وإن ظل فريق منها يردد على المآذن: «لا إله إلا اللّه» دون أن يدرك مدلولها... إلا أن البشرية عادت إلى الجاهلية، وارتدت عن لا إله إلا اللّه. فأعطت لهؤلاء العباد خصائص الألوهية. ولم تعد توحد اللّه، وتخلص له الولاء.. البشرية بجملتها، بما فيها أولئك الذين يرددون على المآذن في مشارق الأرض ومغاربها كلمات: «لا إله إلا اللّه» بلا مدلول ولا واقع.. وهؤلاء أثقل إثما وأشد عذابا يوم القيامة، لأنهم ارتدوا إلى عبادة العباد -من بعد ما تبين لهم الهدى- ومن بعد أن كانوا في دين اللّه "
الظلال : 2/ 1057
" ዘመኑ መጀመሪያ በላኢላሃ ኢልለላህ ወደ ሰው ልጆች ወደ መጣበት ዘመን ተመልሷል ። የሰው ዘር ( አላህን ትቶ) ፍጡርን ወደ ማምለክ ተመልሷል ። ከላኢላሃ ኢልለላህ ወጣቷል ። ከሙስሊሞች ውስጥ በሚምበር ላይ ትርጉሙን ሳያውቁ ላ ኢላሃ ኢልለላህ የሚሉ ቢኖሩም ( ከእስልምና ወጥተዋል) ። በመሆኑም የሰው ዘር ወደ ጃሂሊያ ተመልሷል ። ከላ ኢላሃ ኢልለላህ ተመልሷል ። ለፉጡራኖች የላ ኢላሃኢልለላህን ( የአላህ ብቸኛ ተመላኪነትን) ለእነዚያ ፉጡራን ሰጥቷል ። …… " እያለ የህፃናት ፀጉር በሚያሸብት መልኩ ኡማውን እያከፈረ ይቀጥላል ።

አራተኛ — እሱና አምሳዩቹ የሚመሩትን እንቅስቃሴ ሰራዊቶች ወይም አባላት ከሃዲያኖች አዛን ከሚሉባቸው መስጂዶች መራቅ እንዳለባቸው ሲናገር እንዲህ ይላል : –
" اعتزال معابد الجاهلية واتخاذ بيوت العصبة المسلمة مساجد . تحس فيها بالانعزال عن المجتمع الجاهلي، وتزاول فيها عبادتها لربها على نهج صحيح وتزاول بالعبادة ذاتها نوعا من التنظيم في جو العبادة الطهور"
(الظلال (3/1816).
" ጃሂሊያዎች ( ወደ ኩፍር የተመለሱ ሰዎችን መስጂዶች) መራቅና ( ከአባሎቻችን) ቤቶች ውስጥ አንዱን ከከሀዲው ማህበረሰብ የመገንጠል ስሜት በሚሰማህ ልክ መስጂድ አድርጎ መያዝ ያስፈልጋል ። (በዚህ ሁኔታ የተገነጠለችው) ቡድን ጌታዋን በትክክለኛ መንገድ የመገዛት ተግባሯን ትፈፅማለች, …… "። እያለ ይቀጥላል ።
ውድ ሰለፍዮች እንዲሁም አንባቢዮች የሰይድ ቁጥብ ኡማውን የማክፈር ዘመቻ በሙሉ ከራሱ መፅሓፎች ይዘርዘሩ ቢባል ራሱ የቻለ ሙጀለድ ይወጣዋል ። በግልፅ ቋንቋ የማክፈር ዘመቻውን ለማሳየት የተጠቀሱት ይበቃሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
ሰይድ ቁጥብ ኡማውን የሚያከፍርበትን ንግግሩ አምኖበት መሆኑን ጠበቃው ሙሐመድ ሓሚዲን ሲገልፅ ንግግሮቹ አምኖባቸው ስለሆነ የሚናገረው ሀይለኞች ናቸው ብሎ መስክሯል ። ነገሩ ወሸሂደ ሻሂዱን ሚን አህሊሃ ነው ። በሌላ በኩል ቀርዳዊን ጨምሮ ሌሎችም የኢኽዋን መሪዮች የሰይድ ቁጥብ ኡማውን ማክፈር በግልፅ ተናግረው አውግዘዋል ።
እዚህ ጋር ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው ይህ የሰይድ ቁጥብ የማክፈር ዘመቻ ኢኽዋኖች ባንዲራውን ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡት መሆኑ ነው ። ነገር ግን ከለራቸውን እየቀያየሩ እንደአየሩ ሁኔታ የመገለባበጥ ብቃታቸው አንዳንዴ እንዳይታወቅባቸው ሊያደርግ ይችላል ።
አላህ ካለ ይቀጥላል ።

https://t.me/bahruteka
✅ አላህ ሴትን መልእክተኛ አድርጎ አላከም !

يقول ابن الجوزي – رحمه الله –

" ما بعث الله تعالى امرأة بالرسالة ، ولا جعلها قاضييا، ولا إماما ولا مؤاذنا، كل ذلك لأنها محل فتنة ".

ኢብኑል ጀውዝይ የተባለ ሰው እንዲህ ይላል : –

" አላህ ሴትን መልእክተኛ አድፍጎ አላከም, ዳኛም አላደረጋትም, ኢማምም ሆነ ሙአዚን አላደረጋትም, ይህ ሁሉ እሷ መፈተኛ በመሆኗ ነው "።

https://t.me/bahruteka
Audio
የጃሲያ ምእራፍ ክፍል 02

" እነዚያ ኀጢአቶችን የሠሩ ሕይወታቸውም ሞታቸውም ትክክል ሲኾን እንደእነዚያ እንደ አመኑትና መልካሞችን እንደሠሩት ልናደርጋቸው ይጠረጥራሉን? (አይጠርጥሩ) ፡፡ የሚፈርዱት ምንኛ ከፋ "! የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
👉 በዚክር ወንጀልህን አራግፍ !

يقول ابن القيم – رحمه الله تعالى –

" أن العبد يأتي يوم القيامة بسيئات أمثال الجبال، فيجد لسانه هدمها من كثرة ذكر الله "

الداء والدواء ص (231)

ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" አንድ ሰው የቂያማ ቀን ተራራ የሚያክል ወንጀል ሰርቶ ይመጣል ። ነገር ግን ምላሱ በዚክር ብዛት እንደሌለ አድርጎት ያያል "! ።

https://t.me/bahruteka
🚫   እውነትም እንቁ – ጣጣሽ

     እንቁ የሚለው ቃል እኔ የማውቀው የከበረ ማእድን መሆኑን ነው ። እኛ ሀገር ግን ዘመን መለወጫ ላይ የሚወጣን አበባ ለመግለፅ ይጠቀሙበታል ። በእነርሱ እይታ አበባዋና ጣጣዋ ምን እንደሆነ ባላውቅም በኔ እይታ ግን የዘመን መለወጫን ተክትላ የምትመጣው እንቁ ብዙ ጣጣ አላት ። በሌላ አባባል ዘመን መለወጫው ብዙ ጣጣ አለው ።
     ከሁሉም በፊት ይህ ባአል ከክርስትና እምነት ጋራ የተገናኘ ስለሆነ ሙስሊሞችን አይመለከትም ። ሙስሊሞች በአመት ሁለት ዒድ ( ባአል አላቸው) እነርሱም ዒደል አድሓና ዒደል ፊጥር ናቸው ። የዘመን አቆጣጠራቸውም የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ሂጅራ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ በሂጅሪያ አቆጣጠር ነው የሚቆጥሩት ። በዚህ አቆጣጠር መሰረት አመቱ አልቆ አዲሱ የሚጀምርበት ወር ሙሐረም ይባላል ። ይሁን እንጂ ይህን የዘመን መለወጫ ቀን  እንደ ባአል አያከብሩትም ።
    እንቁጣጣሽ የሚባለው ግን ከክርስትና እምነት ጋር የተገናኘ ባአል ነው ። ዘመኑንም ዘመነ ዮሐንስ, ዘመነ ማቲዮሰ, ዘመነ ሉቃስና ዘመነ ዻውሎስ ብለው ይሰይሙታል ። ታዲያ ይህንን እንዴት ሙስሊሞች ያከብሩታል ?
   የሀገረችን ሙስሊም በሱፍይ መሪዎች አማካይነት ታቦት ሲሸኝና ጥምቀት አብሮ እየጨፈረ ሲያከብር ኖራል ። ይህም ለሙስሊሙ ወላእና በራእ የሚለው የዐቂዳ ውድቀት ሰበብ ሆነ ። የአላህ መልእክተኛ ለኡመቴ የምፈራው አጥማሚ መሪዎችን ነው ያሉት ይህን ነው ።
       ወደ ርእሴ ስመለስ እንቁ – ጣጣሽ እውነትም ብዙ ነው ጣጣሽ እላለሁ ። በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ዐቂዳ ሁሌም ኮተት አያጣውም ። ዘመን መለወጫ ሲመጣ ሰዎች ካለፈው አመት ድክመታቸውና ስህተታቸው ታርመው የበለጠ ለመስራት ከመዘጋጀት ይልቅ የህይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀየር ወደ መተትና ኮተት ያማትራሉ ። በመሆኑም ከምን ጊዜውም በላይ በዚህ የእንቁ–ጣጣሽ በአል ላይ መተትና ድግምት ይሰራል ። ጠንቋዮች በጣም ቢዚ ይሆናሉ ። ይህ መተትና ድግምት የእነርሱ ህይወት ሊለውጥ የሌላው ህይወት ማጥፋት አለበት ብለው ነው የሚያስቡት ። በመሆኑም በአብዛኛው የሚሰሩ ድግምትና መተቶች በሰዎች ላይ ይሆናል ።
   አላህ ከፈቀደው ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ። መጠንቀቁና ሰበብ ማስገኘቱ መልካም ነው ። በዘመን መለወጫው ማለዳ ( ጠዋት)  ላይ የተለያዩ ዶሮዎች በተለያየ መንገድ ተገለው በሰዎች መውጫና መግቢያ ላይ ወይም መንገድ ላይ ሊጣሉ ይችላሉ ። በሌላ መልኩ መሬት ተቆፍሮ ሊቀበሩም ይችላሉ  ። ሙስሊሞች በተለይ በዚህ ቀን ጠዋትም ሆነ ቀኑ ላይ ከቤታቸው ሲወጡ
" ቢስሚላህ ተወከልቱ ዓለላሂ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ " ብለው መውጣት ይኖርባቸዋል ። ለልጆቻቸው ይህን ዚክር ማስተማርና መንገድ ላይ የሚያገኙትን ነገር እንዳይረግጡ ፣ እንዳያነሱና እንዳይጫወቱበት መንገር ይኖርባቸዋል ። ይህን ዚክር አድርገው ሰበብ ካስገኙ በአላህ ይጠበቃሉ ። በእንቁጣጣሽ ጣጣ እንዳይጎዱ ይረዳቸዋል ።
    በመጨረሻም ይህን ኮተት ተሸክሞ የሚመጣውን ዘመን መለወጫ የሁሉም ነው ከማለት ተቆጥቦ ይዞት ከሚመጣው ጣጣና ኮተት በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል ።
አላህ ሙስሊሞችን ከሸረኞች ተንኮል ይጠብቅልን ።

https://t.me/bahruteka