ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.3K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
ከቢድዐህ ሰዎች እውቀት የሚቀስሙ ሰዎች ቢያንስ በሚከተሉት ነጥቦች የልብ በሽተኛ ይሆናሉ!!
———
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን አማን አልጃሚይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
:
ከቢድዐህ ሰዎች እውቀት የሚወስድ ሰው የሚፈተንበት ነገር በቀላሉ የሚከተለው ነው:-


↪️ ቢድዐን፣ ወንጀልን እና ከሸሪዓ መቃረንን መጥላት ከልቡ ይወጣል።
:
↪️ ለአላህ ብሎ መጥላትና ለአላህ ብሎ መውደድ የሚባለውን ነገር ያጣል።
:
↪️ ከሱኒዩም ይሁን ከሙብተዲዑ ጋር ለመቀማመጥ ግድ አይኖረውም። ምክንያቱም በሱ ግምት እርሱ ዘንድ ያለው ብይን ለደዕዋ መስለሃ የሚባል ነገር ነው፣ በመሆኑም (በአላህ እንታገዛለን!) በዞረበት ይዞራል።

🚫 ይህ ደግሞ (በአላህ እንጠበቃለን!) ወደ ኒፋቅ አይነቶች ከሚያደርሱ የልብ በሽታዎች ነው!!
[መጅሙዕ አርረሳኢል አልጃሚ 42]
:
ብዙዎች ዘንድ እያየን ያለው ከባድ ፈተና ይህ ሸይኹ የጠቀሱት መሰል ፈተና ነው!! በተለይ ደግሞ (አላህ ይጠብቀንና) ቢድዐን እና የቢድዐ ሰዎችን የመላመዱ ፈተና የጎላ ነው።
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የሙነወር ልጅ ሆይ የተለመደውን ቅዠትህን ብትቃዥም፣ እነዚህና መሰል ማንነታችሁንና ልዩነታችን ምን ላይ እንደሆነ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ጥያቄዎችና ነጥቦች ከማህበረሰባችን ጭንቅላት አይጠፉምና በከንቱ አትልፋ።
👇👇👇

እኛም እንጠይቅ፣ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ልዩነታችሁ ምንድነው??!!

————— ልብ ያለው ልብ ይበል!!
የሙነወር ልጅ ሆይ!፣ ሳዳት ከማል፣ ኸድር ከሚሴ፣ ሙሀመድ ሲራጅ… ያቺ በባጢል ባለ ቤቶች ላይ ብርቱ የነበረችውን አንደበታችሁን ምን ለጎማት? ከዚህ ቀደም ከ4/5 አመታት በፊት በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ ከሰልላ ሰይፍ የበለጠ የቢድዐህ ባለ ቤቶችን ወገብ የሚበጥስ የነበረው ብዕራችሁን አሁን ላይ ለቢድዐህ ባለ ቤቶች ጊዜ ምን አደለዶመው??
ይሀው "ነጭ ነጩን እንናገራለን" ስትሉባቸው የነበሩት የመርከዙ አመራሮች ትላንት ኢኽዋን ሲሏቸው ከነበሩት ከነ ሙሀመድ ሃሚዲን ከነ ጀይላንና… መሰል ከሌሎችም የመጅሊሱ ሰዎች መደመራቸውን እናንተ ዑዝር ብትደረድሩላቸውም "ካፈርኩ አይመልሰኝ" ብለው በግልፅ በአደባባይ እያሳዩዋችሁ ነው። ታዲያ የናንተ ዝምታ እስከ መቼ ነው? ወይስ እናንተም ሳዳት ከማል የመጅሊሱን ሰዎች "በእድሜ የጠገቡ ናቸው፣ ልጅና ጅል አይደሉም" ብሎ ማወዳደስ እንደጀመረው በሂደት መደመራችሁን ለቴፎዞዋችሁ ግልፅ እስክታደርጉ ነው የጠበቃችሁት?? ከእነዚህ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎችና ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ያላችሁ ልዩነት ምንድነው? ለቲፎዞዎቻችሁ መደመራችሁን በአደባባይ ግልፅ ማድረግ የቀራችሁ ቢሆን እንጂ ምን ልዩነት አላችሁ? በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ የተለጎመው አንደበታችሁና የደሎደመው ብዕራችሁ በሰለፊይ መሻይኾችና በሰለፊይ ወንድሞች ላይ በርትቷል!! ሰለፊይ መሻይኾችን "የረድ ጉረኛ፣ በእንጨት የበቀለ ሽበት…" መሰል ቃላቶችን ተጠቅማችሁ እየወረፋችሁና ረድን እያጣጣላችሁ የመጅሊስ ሰዎችን "እድሜ የጠገቡ…" ምናምን እያላችሁ ታወድሳላችሁ!! ታዲያ ምኑ ጋ ነው ልዩነታችሁ?!
ይልቅ እናንተም ለቲፎዞዎቻችሁ መደመራችሁን ቶሎ ግልፅ አድርጋችሁ ገላግሏቸው። በእርግጥ በርካታ እህትና ወንድሞች ነቅተው በጊዜ ቢርቋችሁም አንዳንድ በእናንተ ጭፍን ተከታይነት የሚሰቃዩ አሉና በቃችሁ አትሰቃዩ እኛም ከነዛ ሰዎች ልዩነት የለንም ብላችሁ ገላግሏቸው!!

የጀርህና ተዕዲል ባንድራ ተሸካሚና በሂዝቢዮች ላይ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ረቢዕ ቢን ሓዲ'ል መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ ምላሽ ከመስጠት የተለጎሙ ሰዎችን እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ:-

“ቢድዓንና የጥመት ባለ ቤቶችን የማትዋጋና በስሜት ባለ ቤቶች ላይ ምላሽ የማትሰጥ ከሆንክ በአንተና በነዚያ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?!፣ በእነሱና በአንተ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? በጥፋታቸው ላይ እየተመለከትካቸው ዝም የምትል ከሆነ አንተ የጥመት ባለ ቤቶችን ቁጥር እያበዛህ ነው ማለት ነው። በምድር ላይ ብልሽትን እያዳረሱ እየተመለከትክ ዝም የምትል ከሆነ አንተ እነሱን እያገዝካቸውና እያጀገንካቸው ነው። ሌባ ወደ ሰዎች ግቢ ሊገባ ሲዘል አይተህ ማሻአላህ ዝም ትላለህ? ይሄ ምን ማለት ነው? ይህ ነው እንዴ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል?

ወደ ቢድዐህ ተጣሪዎች ከሌባና መንገድ ከሚቆርጡ ሽፍቶች የበለጠ ሸረኛ ናቸው። ኢብኑ አቢ ዘይድና ኢብኑ ዐብዱልበር እንዲህ ብለዋል:- "እነሱ እኮ መንገድ ከሚቆርጡ ሙጅሪም የሆኑ ሽፍቶች የበለጠ ሸረኞች ናቸውና ከእነሱ ሁልጊዜም ማስጠንቀቅ ግዴታ ይሆናል። ሰዎች እስከሚጠነቀቋቸው ድረስ እነሱን ማጋለጥ፣ገመናቸውን ማውጣትና ሰዎች ፊት እርቃናቸውን ማስቀረት ግዴታ ነው።"

ለዚህም ነው የደጋግ ቀደምቶች ኪታቦች የቢድዐህ ባለ ቤቶችን በመቃረን ቢድዓቸውን (በማፍረስ)፣ ከእነሱ በማስጠንቀቅና ከመቀማመጥ… መሰል ነገሮች በማስጠንቀቅ የተሞላ ሆኖ ታገኘዋለህ። ብዙ ሙስሊሞች በቢድዐህ ባለ ቤቶች ጥመት አልጠፉም ምክንያቱ ይህን "በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ ምላሽ የመስጠትና የማስጠንቀቅን" መሰረት በመተዋቸው ቢሆን እንጂ።
ለዚያም ነው በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ጥመት የተሰባሰበበት። ከጥመታቸው ነጃ የሚወጣ የለም ጥቂት ብልሃትም ሆነ አቅም የሌላቸው ሚስኪኖች ቢሆኑ እንጂ። እነዚያ ረድ ረድ… እያሉ ረድን የሚያጣጥሉ ሰዎች ጠማሞች ናቸው። ውዳቂ ተግባራቸውን ነው የሚያሰራጩት፣ አንድም ሰው ምላሽ እንዲሰጥባቸው አይፈልጉም። ተገንዘቡ አላማቸው ይህ ነው። ለዚያም ነው በተሳሳተ ሰው ላይ ረድ ማድረግን (ምላሽ መስጠትን) የረድ ኪታቦች ልብ ያደርቃሉ… መሰል ቃላትን በመጠቀም የሚያጠለሹት። ይህ ማለት እንግዲህ ግሳንግሱ ተግባራቸውና ቢድዓቸው ልብ ያረጥባል እያሉ ነው ማለት ነው። ከተንኮላቸውና ከሴራቸው ቢድዓንና ጥመትን ያሰራጫሉ። አህሉሱንናዎችንና መንገዳቸውን በተቀማመጡበት፣ በሙሃዶራቸውና በመፅሃፎቻቸው… በሁሉም ነገራቸው ይዋጋሉ። ከመሆኑም ጋር ግን በቢድዐህ ሰዎች ላይ ሲሆን ምላሽ አትስጥ ምላሽ መስጠት ልብ ያደርቃል ይላሉ። ሐቅንና የሐቅ ባለ ቤቶችን መተቸት ግን እነሱ ዘንድ ማሻአላህ ችግር የለውም¡¡። ሐቅንና ባለ ቤቱን መዋጋትም ማሻአላህ እነሱ ዘንድ ልብ ያረጥባል¡¡።”
[አል መጅሙዕ 14/280]
ይሄው ነው ተጨባጩ!። ቅንና ሚዛናዊ ልቦና ያለው ሰው ከጭፍን ተከታይነት ወጥቶ ይመከርበት!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ምንዳህ የስራህ ውጤት ነው!!
—————
ሰዎችን በምን አይነት መስተጋብር እንደምንኗኗር እራሳችንን እንተሳሰብ!!፣ አላህ ለእነርሱ በምንኗኗረው መልኩ ነው የሚኗኗረን፣ ምንዳ የስራ ውጤት ነው። ብዙዎቻችን መከራ፣ ርሃብ፣ የኑሩ ውድነት፣ መጨካከን፣ መበዳደል… ወዘተ በዛ፣ በተቃራኒው ደግሞ መዋደድ፣ መተዛዘን፣ ይቅር መባባል… ወዘተ፣ ጠፋ እንላለን፣ ነገር ግን እነዚህና መሰል ነገሮች እንዲሆኑ የራሳችን ሚና ዋናው ድርሻ እንደሆነ ዘንግተናል።
ብዙ ሰዎች የሚዘነጓት መርሆ ትልቅ የሆነች መርሆ አለች እሷም “አላህ ከአንተ ጋር የሚኖረው መስተጋብር ከባሪያው ጋር በሚኖርህ መስተጋብር ልክ ነው” የሚለው ነው።

ይህቺ መርሆ ከብዙ የእውቀት ባለ ቤቶች ንግግር በኩል የመጣች መርሆ ስትሆን፣ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃዎችም ረድቶ (አጠናክሯታል)፣ ጠቃሚ ስለሆነች ወደ አማርኛ መልሰን እንደሚከተለው እናሰፍራታለን። ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“✅ እርሱ አላህ (ጥራት ይገባውና) አዛኝ ነው አዛኞችን ይወዳል፣ ከባሮቹ አዛኝ ለሆኑት ነው የሚያዝነው።
🔹እርሱ አላህ የባሮቹን ነውር የሚደብቅ ነው!፣ ለባሮቹም የሚሰትርላቸውን ባሪያ ይወዳል።
አላህ ይቅር ባይ ነው!፣ ከባሪያውም ይቅር ባዩን ይወዳል።
🔹እርሱ አላህ መሃሪ ነው!፣ ከባሪያውም ለአላህ ባሪያዎች የሚምር (የሚተውን) ባሪያ ይወዳል።
🔹እርሱ አላህ የልስላሴ ባለ ቤት ነው፣ ከባሪያዎቹ ለስላሳ የሆነውን ይወዳል።
↪️ ደረቅ፣ ልበ ደንዳና፣ ጨካኝና (በሰውነቱ ግዝፈት የሚንቦጣረር) ኩራተኛ የሆነን ሰው ይጠላል።
🔹 እርሱ አላህ ቻይ ነው፣ ቻይ የሆነን ሰው ይወዳል።
🔹እርሱ አላህ መልካም ሰሪ ነው፣ መልካም ስራን እና ሰሪውንም ይወዳል።
🔹ሚዛናዊ ነው ሚዛናዊነትን ይወዳል።
🔹እርሱ አላህ ምክንያት (ዑዝር) ተቀባይ ነው፣ የባሪያውን ዑዝር ተቀባይ የሆነን ሰው ይወዳል።

አላህ እነዚህ ባህሪያት ከባሪያው በመገኘታቸውና ባለ መገኘታቸው ልክ ባሪያውን ይመነደዋል።
— ዓፉ ያለን ዓፉ ይለዋል።
— የተወን ይተውለታል።
— ይቅር ባይን ይቅር ይለዋል።
— ለጓደኛው ሐቅ ይገበዋል ብሎ የተከራከረ አላህ ሀቁን ይጠብቅለታል።
— ለፍጡሩ ያዘነ ያዝንለታል።
— ለፍጡሩ መልካም የዋለ አላህ መልካም ይውልለታል።
— አላህ ፍጡሮቹን በጥፋታቸው ይቅር ብሎ ያለፋቸውን ባሪያውን ይቅር ብሎ ያልፈዋል።
— በመልካም ነገር ያበረታታን ያበረተዋል።
— ለፍጡሮቹ የጠቀመን ይጠቅመዋል።
— የአላህን ባሮች ነውር የሸፈነ ይሸፍንለታል።
— ነውሩን የሚከታተል ነውሩን ይከታተልበታል።
— የአላህን ባሪያ ለማጋለጥና ለማዋረድ አስቦ የሚንቀሳቀስን አላህ እራሱን ያጋልጠዋል።
— ለሰዎች መልካም ነገሩን የከለከላቸው ሰው አላህ መልካም ነገሩን ይከለክለዋል።
— አላህን የሚፃረርን ሰው አላህ የሚፃረረውን ያደርግበታል።
— በባሪያው ላይ የሚያሴርን ሰው አላህ ያሴርበታል።
— የሚያታልልን አላህ እንዲታለል ያደርገዋል።
አንድ ሰው ለአላህ ፍጡሮች በሚኖረው መስተጋብር መልኩ ነው በቅርቢቱም በሩቁም ዓለም (በአዱኒያም በአኼራም) ከአላህ ጋር  መስተጋብር የሚኖረው። አላህ ለባሪያው የሚሆነው ባሪያው ለአላህ ፍጡር በሚሆነው ልክ ነው። ለዚያም ነው ከአቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈ ሀዲስ እንዲህ የሚል የመጣው:-
“ሙስሊም የሆነን ሰው ነውሩን የደበቀለት አላህ ነውሩን ይደብቅለታል፣ አማኝ የሆነን ሰው ከዱኒያዊ ጭንቀት ያወጣ ሰው፣ አላህ ከቂያማ ጭንቀቶች ያወጠዋል፣ ለተቸገረ ሰው ያግራራ ሰው አላህ በእለተ ትንሳዔ ሂሳቡን ገር ያደርግለታል።" [ሙስሊም 2699 ላይ ዘግበውታል]
በሌላ ሀዲስ:- "ባሪያው ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ አላህ ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው።" የሚል አለ። [አል ዋቢሉ ሶይብ… ገፅ 36]
✍🏻ኢብን ሽፋ #join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
👇 ዛሬ ይጀመራል
ልዩ ወርሃዊ የኮርስ ዝግጅት በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አዲስ አበባ

:
🕰 ቅዳሜ እና እሁድ ጥቅምት 23 እና 24/2017
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

ኮርሱ የሚሰጥበት ኪታብ
الأربعون اللتمية في العقائد والمناهج السلفية
"አል አርበዑን አልለተሚየህ"
አዘጋጅ:- ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ)

ኮርስ ሰጪ:- የኪታቡ አዘጋጅ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ) ናቸው

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031
የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
🔹 ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል


በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 6/2017 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሙሃዶራ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:30 (በጊዜ ይገኙ)

ተጋባዥ እንግዶች:-
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን (ሀፊዘሁላህ)
በተለያየ ርእስ ይቀርባል

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

የፊታችን እሁድ በቀን 16/06/2017  ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም በመድረሳችን አልኢስላሕ ለየት ባለና ባማረ ሁኔታ እንኳን መቅረት በማርፈድ የሚያስቆጭ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡ 

ተጋባዥ እንግዶች፡-

1ኛ.   አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁሏህ)

2ኛ.   አሸይኽ ሐሰን ገላው (ሐፊዘሁሏህ)

3ኛ.   አሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዘሁሏህ)

በተጨማሪ ሎሎችም ኡስታዞች የሚገኙ ይሆናል፡፡

👌 በአሽይኽ ዓብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚይ የሚሰጠው ወርሀዊ ፕሮግራማችን ከፊታችን ጁሙዓህ ከአስር ሰላት በኋላ ጀምሮ በተለመደው ሰአት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

አድራሻ፡-  አልኢስላሕ መድረሳ ፉሪ ኑሪ ሜዳ ባጃጅ  ተራ መጨረሻ

ሰዓት፡- ልክ 2፡30 ይጀምራል፡፡

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል!!!!!



የአልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ። https://t.me/medresetulislah
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️
በምስሉ በምትመለከቱት መልኩ በቴሌግራም እና ዋትሳፕ የውስጥ መልእክት በምታውቁት ሰው ስም መስለው የሚመጡላችሁን ሊንኮች ከመክፈት ተጠንቀቁ!!
🔸እንደሚታወቀው ሃከሮች በተለያየ ጊዜ ዘዴዎችን ቀያይረው የሰዎችን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስሮችን ይጠልፋሉ፣ አሁን ደግሞ በዚህ መልኩ የአንድን ሰው ከጠለፉ በኋላ የሱን ጓደኞች ደግሞ በተጠለፈው ሰው ስም አድርገው ሊንክ እየላኩ በቀላል መንገድ የብዙዎችን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስሮችን መጥለፍና የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።
"ሊንኩን ተጭናችሁ ፎቶዋችሁን ተመልከቱ…" እያሉም በስልካችሁ የከፈታችሁትን አካውንት ከመጥለፍ ባሻገር የብልግና ምስሎችን እያሰራጩ ይገኛሉ፣ በምንም ተኣምር በዚህ መልኩ በምታውቁት ሰው ስም የተላኩ ምንነታቸው ግልፅ ያልሆኑ ሊንኮችን ከመክፈት ተጠንቀቁ!! ብዙዎች ቴሌግራማቸው እየተጠለፈ ስለሆነ ለሌሎችም ሸር በማድረግ አዳርሱ!!
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የሙመይዓዎች ሸይኽ ተማሪ ለሆነው ለሙመይዑ ዳውድ ያሲንና በደፈረሰ ውሃ ውስጥ ለሚያድን ሁሉ የተሰጠ ምላሽ!!
——ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
ሙመይዑ ዳውድ ያሲን ለራሱ ጉዳይ ሲል ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚን ከታላላቅ መሻይኾች መሆናቸውንና የተረጋጉ ልምድ ያላቸው እንደሆኑ በማወደስ በሸይኹ እውቀት መጠቀም ተገቢ እንደሆነ ጥሪ ያደረገባት የሆነችን ፅሁፍ አንብቤያለሁ።

ለዚህ ሴረኛ፣ አታላይ ለሆነው እና በእሱ መንገድ ለሚጓዙት የመሰብሰብ ተጣሪና የወላእና በራእ ዐቂዳ (እምነት) ጠላት ለሆኑ ዳዒዎች በሙሉ እንዲህ እላለሁ:-
በመጀመሪያ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ ከታላላቅ የሱንና ዑለማዎች በመሆናቸው ጥርጥር የለውም!። ነገር ግን ማንኛውም ዓሊም ከንግግሩ የሚያዝና የሚመለስ አለው፣ በዚያ ዓሊምም ማስረጃ አይደረግም ለዚያ ዓሊም ማስረጃ ይፈለግለታል እንጂ፣ ይህ በሁሉም ዓሊሞች ላይ የሐቅ ባለ ቤቶች አካሄድ ነው።

ሁለተኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ተቃራኒ ናቸው፣ እንደ ኢኽዋን፣ ሱሩሪየህ፣ሱፊየህና ሙመይዐህ… መሰል ከጥመት ቡድኖች ተቃራኒ ናቸው። ከእነዚህ ማስጠንቀቅና መራቅም ግዴታ መሆኑን ያምናሉ (ይመለከታሉ)፣ በኢትዮጵያ ያሉ ሙመይዓዎችና የመሰብሰብ ተጣሪዎች ይህ የሸይኹ አቋም አላቸውን?! እናንተ ቀጣፊዎች ሆይ! ከኢኽዋን ከሱሩሪየህ አስጠንቅቃችኋልን?! ይልቁንም ከነዚህ የጥመት ቡድኖች ሙሉ በሙሉ ጥቅልል ብላችሁ አልተቀላቀላችሁምን?! ታዲያ ለምንድነው ይህ ውሸት፣ ማለባበስና ማታለል?! ለምንድነው በሸይኹ ውስጥ መደበቅ የፈለጋችሁት?! ንፁህ አዕምሮ ላለው ሁሉ ጉዳያችሁ ግልፅልፅ ብሏል!፣ በአላህ ፈቃድ ለሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚም በሀበሻ ምድር የመሰብሰብና የማቅለጥ ተጣሪ የሆናችሁ በውሸት የሰለፊያን ልብስ ለባሾች ጉዳይ ግልፅ ይሆንላቸዋል።

ሶስተኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚ ተንቢህ ዘዊል አልባብ በተሰኘው ኪታባቸው ገፅ 66 ላይ እጅግ በርካታ የሆኑ በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ ጠንካራ የሆኑና በሱንና በመጣበቅ ላይ የሚያነሳሱ የሰለፎችን ፋና (ንግግሮችን) ጠቅሰዋል። ሙመይዓዎች እንዲህ ያሉ ጠንካራ የሆኑ የሰለፎችን ንግግሮች በሚመለከቱ ጊዜ "ከጊዜያችን ጋር አይሄድም፣ ለጊዜያችን ጥሩ አይደለም…" ይላሉ፣ ልክ ሙመይዑ ሸይኽህ ኢልያስ እንዳደረገው ማለት ነው።

አራተኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ከመቀማመጥ አስጠንቅቋል፣ በሰለፊያ ደዕዋ ላይ የሚፈጥረውን ተፅዕኖና አደጋውንም አብራርተው ገልፀዋል፣ በርካታ የሆኑ ግልፅ ማስረጃዎችንም አስቀምጠዋል። (ተንቢህ ዘዊል አልባብ ከገፅ 73 ጀምረህ ተመልከት)
አንተ አምታቹ ሆይ! ታዲያ በዚህ ተግባሩ ሸይኹን ተከትለሀዋል?!፣ ይልቅ እናንተ ወደዚህ አቋም የሚጣራችሁን ለተሚይ በማለት፣ ሙተሸዲድ በማለትና የደዕዋን መስለሃ አያውቅም በማለት ትተቹታላችሁ!!

አምስተኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ ቢድዐህ ለመስፋፋቱ ዋነኛው ምክንያት መጥፎ ሰዎችን መቀማመጥ፣ ማድመጥና ዑለማዎች ዝም ማለታቸው (ባጢልና ሀቅን ግልፅ አድርገው አለመናገራቸው) መሆኑን ጠቅሰዋል። (ተንቢህ ዘዊል አልባብ ከገፅ 144 ጀምረህ ተመልከት)
ይህ ከኢኽዋን ጋር የተቀላቀሉ ሙመይዓዎች የወደቁበት ተግባር ሲሆን ከኢኽዋን ተከላክለዋል፣ ለሚያገኙት ጥቅማጥቅምና ገንዘብ መሰብሰብ ሲሉ በኢኽዋን ላይ መናገርንም ጠልተዋል።
ዳውድ ያሲን ሆይ! አላህን አትፈራም?! ባልተሰጠህ ነገር ብዙ የተሰጠህ ታስመስላለህ? ባልተሰጠው ነገር ብዙ ያለው የሚመስል ሰው ሁለት የማስመሰል ልብሶችን እንደሚለብስ አይነት ሰው ነው። በሙመይዓዎችና የመሰብሰብ ተጣሪ በሆኑ ሰዎች ሶፍ ውስጥ መጥፎ ተጣሪዎችን ምንኛ አበዛቸው?! አላህ አያብዛቸውና!!

ስድስተኛው: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ እንዲህ ብለዋል:- "ለቢድዐህ አደገኝነት ከትልቁ ማስረጃ አንዱ ባለቤቶቿ፣ አራጋቢዎቿና ውዴታዋን ያጠጡት አካል ሐቅንና ባለቤቱን ይጠላሉ!፣ በተለይ ወደ ሱንና እና ቅኑን መንገድ ወደ መከተል የሚጣሩ ሰዎችን በማይግገባቸው ገለፃ ይገልጿቸዋል፣ ይልቁንስ ነገሩ በተቃራኒ ነው በእንደዛ አይነት ገለፃ ሊገለፁ የሚገቡት ትክክለኛው ሙብተዲዖች ናቸው።" [ተንቢህ ዘዊል አልባብ ገፅ 160]
ይህ ንግግር የሚገባው በአንተና በመሰብሰብና በተምይዕ ባለ ቤቶች ላይ ነው።

ሰባተኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ የጥመት ቡድኖች መብዛት የሙስሊሞችን ግርማሞገስና አንድነት እንደበታተነ አረጋግጠዋል [ተንቢህ ዘዊል አልባብ ከገፅ 227 ጀምሮ ማየት ይቻላል] እንዲህ ያለውን ንግግር አምሳያውን ከሙመይዑ ሸይኽህ ሰምተሃል? ይህ ከመርከዝ ኢብኑ መስዑ ጥቅም፣ የመሰብሰብና ወደ ሰለፊያ መጠጋትን ከሚያወግዙ ዳዒዎች አይገጥምም።

ስምንተኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ እነዚህ የጥመት ቡድኖች ወደ ትክክለኛው እምነት (ዐቂዳ) ከመጣራት ችላ በማለት እንደሚሰባሰቡ ጠቅሷል፣ እሱም ይህ ወደ ትክክለኛው ዐቂዳ መጣራቱ ኡማውን ይበታትነዋል በሚል ሙግት ነው። [ተንቢሁ ዘዊል አልባብ 253]
በሀበሻ ምድር ይህን አረጋግጦ የሚንቀሳቀስ ሰው በሙተሸዲድነት፣ በጭፍንተኝነትና በለተሚይነት ይተቻል (ይወረፋል)። ሸይኽ ሷሊህስ ለተሚይ ናቸው?!

ዘጠነኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ እነዚህ አህሉሱናዎችን የሚቃረኑ የጥመት ቡድኖች በሸሪዓዊ እውቀት ህግጋት ላይ መሃይሞች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። [ተንቢሁ ዘዊል አልባብ 253]

አስረኛ: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ እነዚህ የጥመት ቡድኖች መኖራቸውና ወደ እነዚህ የጥመት ቡድኖች መካተት ቀዳሚ የሌለው ቢድዐህ መሆኑን ጠቅሰዋል። [ተንቢሁ ዘዊል አልባብ ገፅ 254]
እናንተ ሙመይዓዎች ሆይ! በዚህ ትስማማላችሁ?! ምክንያቱም የሰለፊያ ደዕዋን ግልፅ በማድረግ ለመርዳት፣ባንድራዋን ከፍ ለማድረግ፣ ከሷም በመከላከል ጥቅሟን ለማስከበር ሳይሆን የራሳችሁን ጥቅም ለማስከበር ብላችሁ ተጠቃላችኋልና። የተውሒድን እና የሱንናን ባንዲራ ከፍ በማድረግ የቆመ ሰው በተገለበጠችው ተፈጥሯችሁ እናንተ ዘንድ ሙተሸዲድ ነው።

አስራ አንደኛው: ሸይኽ ሷሊህ አስ-ሱሀይሚይ እነዚህ ቡድኖች ላይ ልዩነት የሚባል ነገር እንደሌለና በዚህ ምክንያት በሰልፎቻቸው ውስጥ ሁሉም የጥመት ቡድኖች እንደሚታዩ ገልፀዋል። [ተንቢሁ ዘዊል አልባብ ገፅ 254]
እናንተ ሙመይዓዎች ሆይ! የመሰብሰብና ወላእና በራእ ከሚባለው እምነት ዐቂዳ ድሃ የሆናችሁ የተምይዕ ተጣሪዎች ሆይ! ይልቅ ወደ ወላእና በራእ የሚጣራ ሰው እናንተ ዘንድ ለተሚይ ሙተሸዲድ ነው። በውሸትና በቅጥፈት የሰለፊያን ልብስ የለበሱ ውሸታሞችን አላህ ይርገማቸው!!።
🔹ማጠቃለያ
ተጨባጩ ሙመይዓዎችና የመሰብሰብ ተጣሪዎች በጥቅሉም ሆነ በዝርዝር ከሸይኽ ሷሊህ አቋም ተቃራኒ ናቸው። ይልቁንም በሸይኹ መንጠልጠልና ሞኛሞኝ የሆኑ ተከታዮቻቸውን ሊያታልሉባቸው ፈልገው ነው።
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ልዩ ወርሃዊ የኮርስ ዝግጅት በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አዲስ አበባ

: ስድስተኛ ዙር ደረሰ
🕰 ቅዳሜ እና እሁድ ግንቦት 16 እና 17/2017
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

ኮርሱ የሚሰጥበት ኪታብ
الأربعون اللتمية في العقائد والمناهج السلفية
"አል አርበዑን አልለተሚየህ" 
አዘጋጅ:- ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ)

ኮርስ ሰጪ:- የኪታቡ አዘጋጅ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ) ናቸው

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031
የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
👉 ታላቅ ብስራት ለዲን ተማሪዎች

✅ ከዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

خلق أفعال العباد وصحيح البخاري
👉 ኸልቁ አፍዓል አል'ዒባድ እና ሶሂህ አል-ቡኻሪ

🔹 የሁለቱም ኪታቦች ደርስ
🕰 ጁምዐህ፣ ከጁምዐህ ሶላት በኋላ እና እለተ ቅዳሜ፣ የዙሁር ሶላት ከተሰገደ በኋላ በ Online ከቆመበት የሚቀጥሉ መሆኑን ስናበስራችሁ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው!!
ደርሱ የሚሰጠው:- በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ነው

🕌 ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
📢 ሰበር ዜና 📢

🕰ዛሬ እለተ እሁድ ሰኔ 22/2017
ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ልዩ ሙሃዶራ አለ እንዳያመልጣችሁ!


👉 ልዩ ቆይታ
🎙ከሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር (ሀፊዘሁላህ) ጋር

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
አዲስ አበባ አለምባንክ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ሰበር ዜና ነገ እለተ ቅዳሜ ልዩ የኮርስና የሙሃዶራ ፕሮግራም

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
ከሳዑዲ በመጣ ትልቅ እንግዳ

ኮርስ የሚሰጥበት ኪታብ:- አል'ቀዋዒድ አል'አርበዐህ

القواعد الأربع
للشيخ محمد بن عبدالوهاب

ሸይኽ ዶ/ር ዐሊይ ቢን የህያ አል'ሀዳዲ  (ሀፊዘሁላህ) ሸርህ ያደርጉታል

🇸🇦 فضيلة الشيخ الدكتور علي بن يحيى الحدادي حفظه الله

ነገ ነሓሴ 17/2017
ሰኣት:- ዐሱር ሶላት ከተሰገደ ጀምሮ ሲሆን

👉 ልዩ ሙሃዶራ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ይቀጥላሉ

👌እንዳያመልጦት ዐሱር ዳር አስ-ሱንና ይስገዱ

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
አዲስ አበባ አለምባንክ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
#አስደሳች_ኸበር

💬 በአላህ ፍቃድ
ከሳዑዲ በመጡት እንግዳ የሙሃደራ ፕሮግራም ይኖረናል።

🕌 ቦታ ፦ አል-ኢስላህ መድረሳ

🗓 ጊዜ፦ ነገ ማክሰኞ ነሃሴ 20/2017

⏰ ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ

🎙 የሙሐደራው አቅራቢ

🇸🇦 فضيلة الشيخ الدكتور علي بن يحيى الحدادي حفظه الله
🎙 ሸይኽ ዶ/ር ዐሊይ ቢን የህያ አል'ሀዳዲ  (አላህ ይጠብቃቸው)

የአልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ።

https://t.me/medresetulislah
🛜ፕሮግራማችን ሰዓቱ እየደረሰ ነው ‼️

#አስደሳች_ኸበር

💬 በአላህ ፍቃድ
ከሳዑዲ በመጡት እንግዳ የሙሃደራ ፕሮግራም ይኖረናል።

🕌 ቦታ ፦ አል-ኢስላህ መድረሳ

🗓 ጊዜ፦ ማክሰኞ ነሃሴ 20/2017

⏰ ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ

🎙 የሙሐደራው አቅራቢ

🇸🇦 فضيلة الشيخ الدكتور علي بن يحيى الحدادي حفظه الله
🎙 ሸይኽ ዶ/ር ዐሊይ ቢን የህያ አል'ሀዳዲ  (አላህ ይጠብቃቸው)

የአልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ።

https://t.me/medresetulislah
ሰበር አስደሳች ዜና

👉 ነገ በአላህ ፈቃድ እለተ ጁምዐህ ከሳዑዲ ዐረቢየህ በመጡት እንግዳ
በሸይኽ ዶ/ር ኻሊድ ቢን ሰዕድ (ሀፊዘሁላህ)
🇸🇦 فضيلة الشيخ الدكتور خالد بن سعد السرهيد حفظه الله
እየተሰጠ ያለው ኮርስ ከዐሱር እስከ መግሪብ ባለው ሰዓት ተጠናቆ
ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ልዩ የሆነ ሙሃዶራ
أهمية العقيدة الصحيحة
የትክክለኛው እምነት አንገብጋቢነት በሚል ርእስ ከአስተርጓሚ ጋር ይደረጋል
ሁላችንም ፕሮግራማችን አስተካክለን በጊዜ እንገኝ

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ወቅታዊ ብስራት

አስፈላጊ የሙሐደራ ፕሮግራም

⁉️የት?
🕌 አል-ኢስላህ መድረሳ

💺 ተጋባዥ እንግዳ
🎙ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ያሲን አልለተሚይ

📝 ርዕስ፦
👉 ስለ ረመዷን ምን ያውቃሉ?

💬 የአልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ። https://t.me/medresetulislah
ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ የካቲት 29/2018 ረመዷን 19 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሙሃዶራ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:30
(በጊዜ ይገኙ፣ በሰኣቱ ይጀመራል)

🔹 ተጋባዥ እንግዶች:-
ሸይኽ አቡዘር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ) ከኮምቦልቻ

ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሀፊዘሁላህ) ከባህርዳር

ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ) ከአዳማ


👉 ሁሉም ርእሶች በሰኣቱ ይገለፃሉ
እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል!

🔶 ከአገር ውጪ የሆናችሁና መምጣት ያልቻላችሁ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ይተላለፋል።

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።

📲ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ሰለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?1706372650618
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ለኢብኑ ሙነወር የተሰጠ ምላሽ

ርእስ:- ሠለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
ጥር 17/2016 የተደረገ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444