Commercial Bank of Ethiopia - Official
✔
218K subscribers
12.2K photos
474 videos
34 files
2.45K links
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ
ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

ትኬትዎን ባሉበት በሲቢኢ ብር ፕላስ ይቁረጡ፤
ጨዋታውን በስታዲየም ከነድባቡ ይታደሙ!

*******
 
የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2019 የስታዲየም መግቢያ ትኬትዎን ባሉበት በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለመቁረጥ እንዲህ ያድርጉ፡
 
⚽️ የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ላይ ወደሚገኘው ‘ሚኒ አፕስ’/ ‘Mini Apps’ ይግቡ፣
⚽️ ‘Ethio Sport’ የሚለውን ሚኒ አፕ ይክፈቱ፣
⚽️  ሊመለከቱ የፈለጉትን ጨዋታ ይምረጡ፣
⚽️  ሊቀመጡበት የፈለጉትን የስታዲየም ቦታ ይምረጡ፣
⚽️  የትኬት ብዛት ይወስኑና ‘Next’ የሚለውን ይጫኑ፣
⚽️ ስም እና ባለ 16 አሀዝ የፋይዳ ቁጥር ያስገቡ፣
⚽️ ‘Pay with CBE Birr’ የሚለውን ይጫኑ፣
⚽️ የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ያጠናቁ፣
⚽️ ክፍያው በተሳካ ሁኔታ ሲፈጸም የሚደርስዎትን ዲጂታል ትኬት ስክሪን ሾት አድርገው ወይም አውርደው ይያዙና ወደስታዲየም ሲገቡ ያሳዩ።
 
***
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ለማግኘት፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

#cbe #PremierLeague #EthiopianPremierLeague #CBEEthiopianPremierLeague
❤21👍6
የመጨረሻው ዙር ዕጣ ወጣ
እድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!
***********


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዘመን መለወጫን በዓል ምክንያት በማድረግ ከውጭ ሀገር ገንዘብ ለሚላክላቸው እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ለሚመነዝሩ ደንበኞቹ ያዘጋጀው የሽልማት መርሐ ግብር የመጨረሻ ዙር ዕጣ በዛሬው ዕለት በዋናው መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ተወካይ በተገኙበት ወጥቷል፡፡
 
ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም  በወጣው ዕጣ 136 ደንበኞች፣ እንዲሁም ከጳጉሜ 2/ 2018 እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም በቆየው የሽልማት መርሐ ግብር በአጠቃላይ 461 ደንበኞች የ10 ሺ ብር እና 50 ሺ ብር ተሸላሚ መሆናቸውን የባንካችን የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ተስፋ ተክሌ ተናግረዋል።
 
የባንካችን የሪቴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ ዓለሙ የሽልማቱ ዓለማ ደንበኞች በህጋዊ መንገድ ከውጭ ሀገር ገንዘብ እንዲያስልኩ እና እንዲመነዝሩ ለማበርታታት መሆኑን ተናግረዋል።
 
አቶ ደሳለኝ የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ የሚያገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለሀገል ልማት እና ዕድገት መልሶ በማዋል  ሕብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ባንካችን ዲጂታል አማራጮችን ጨምሮ በርካታ ገንዘብ መላኪያ አማራጮችን ማዘጋጀቱን የገለፁት አቶ ደሳለኝ፣ ደንበኞች የውጭ ምንዛሪን በሕጋዊ መንገድ መላክ እና መመንዘር  ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ በውጭ ሀገራት ላሉ ዘመዶቻቸው በማሳወቅ  በባንኩ በኩል ገንዘባቸውን እንዲልኩ እንዲሁም የዲያስፖራ ባንክ አገልግሎት እንዲጠቀሙ በማስተዋወቅ ለባንካችን አምባሳደር እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
 
 በሦስተኛው ዙር ዕጣ አሸናፊ የሆኑ ደንበኞች በሥነ-ሥርቱ ላይ በመገኘት ከባንኩ የሥራ ኃላፊች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡
❤31👏12🔥3
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ ታሪካዊ አሻራ፣ ዲጂታል ፈጠራና ጠንካራ የሕዝብ እምነት!
*****
በዲጂታል ዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ማድረስና ለደንበኞች ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለባንካችን ስኬቶች ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ገለፁ።

አቶ አልሰን ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ፣ ታሪካዊ ጉዞና በዲጂታል ዘመን የተቋሙን ማንነትና መልካም ስም ለማጠናከር የሚያስችለውን የተቀናጀ የኮሙኒኬሽን አቅጣጫ የሚዳስስ ገለጻ ዛሬ በሰጡበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦሌ ዲስትሪክት ኃላፊዎችና የባንካችን የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች በተገኙበት፣ ገለጻው በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተካሂዷል።

አቶ አልሰን በገለጻቸው በዲጂታል ዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ማድረስ፣ ለደንበኞች ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠትና የባንካችን ስኬቶች ለሕዝብ በተቀናጀ መንገድ ማስተዋወቅ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የባንካችን መልካም ስም መጠበቅና የሕዝብን እምነት ማሳደግ የአንድ ክፍል ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን፣ የሁሉም ሠራተኞች የጋራ ተግባር መሆኑም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታሪካዊ አደራውን በመጠበቅ፣ የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግና ከማኅበረሰቡ ጋር ያለውን ቁርኝት በማጠናከር፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ለማስቀጠል እየሠራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ጫላ ገመቹ ናቸው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገርና ለህዝብ እያበረከተ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለማህበረሰቡ ማድረስና የባንካችንን መልካም ስም መጠበቅ ከሁሉም ሰራተኛ የሚጠበቅ የጋራ ስራ መሆኑን አቶ ጫላ አስምረውበታል።
❤27👍11👏7