Condominuim Market in Addis Ababa
3.81K subscribers
2.39K photos
62 videos
10 files
1.04K links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.etsecurities.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@antget1
Download Telegram
በሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም የተደቀነው አደጋ!😡

#condoaddis : በአዲስ አበባ ፣አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው የሚኪሊላንድ (ብርጭቆ) ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ካለፈው ዓመት የክረምት ወራት ጀምሮ በሚኖሩበት የኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተትና መሰነጣጠቅ ሳቢያ ለከፍተኛ ስጋት መጋለጣቸውን ገለጹ።

ችግሩ ከተከሰተ አስር ወራት ቢቆጠሩም፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ለጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠታቸው ነዋሪዎቹ አሁንም ለሞትና ለንብረት ውድመት አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ የመሬት መሰነጣጠቁ የጀመረው በ2017 ዓ.ም ክረምት መውጪያው ላይ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጥልቀቱ እስከ ሦስት ሜትር የሚደርስ ጉድጓድ ፈጥሯል።

ይህ አደጋ የመኖሪያ ህንጻዎችን ግድግዳ ከማላቀቁ ባለፈ በአቅራቢያው በሚገኘው የሚኪ ሌላንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይም ጉዳት አድርሷል።

ስጋቱን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው አንድ ነዋሪ “መሬቱ እየተንሸራተተና እየተሰነጠቀ መጣ፤ አስፋልቱም ወደ ታች ወረደ አሁን ወደ ሦስት ሜትር ያክል ወደታች ወርዷል በጥልቅ ወደ ታች ጉድጓድ ይታያል” በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጸዋል።

አደጋው በተከሰተበት ወቅት የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢ/ር ወንዱሙ ሴታ ቦታው ድረስ በመገኘት የተመለከቱ ሲሆን ችግሩ እስከሚስተካከል ለደህንነታቸው ሲባል ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እና በሌሎች አካባቢዎች ተጠልለው እንዲቆዩ ምክረሃሳብ ማስቀመጣቸውን አስታውሰዋል።

በሁለት ብሎክ 58 አባውራ በችግሩ ምክንያት ለአደጋ ተጋልጠው የነበረ ቢሆንም የበለጠ የሚያሰጋቸው 29 አባውራ መኖሪያዎች በወቅቱ እንዲታሸጉ እና ለደህንነታቸው ሲባል ለቀው እንዲወጡ ተደርጎ ነበር።

ይሁን እንጂ ለተፈናቀሉት 29 አባወራዎች ዘላቂ የመኖሪያ መፍትሄ ባለመሰጠቱና የቤት ኪራይ ዋጋ በመናሩ፣ ነዋሪዎቹም አቅም የሌላቸው በመሆኑ ስጋት ወዳለበት መኖሪያ ቤቶቻቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ጉዳዩን ሲያስረዱ “ ወጥቶ የመከራየት አቅም ስለሌለው [ነዋሪው] ተመልሶ ገብቷል።ጥቂት ሰው ቢቀር ነው እንጂ ሁሉም ገብቷል፤ አሁን ደግሞ ክረምት ሲመጣ ቦታው በጣም ያሰጋል ” ብለውናል።

ነዋሪዎቹ መፍትሄ ፍለጋ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ጀምሮ እስከ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድረስ ደጋግመው ቢመላለሱም፣ እስካሁን ያገኙት ምላሽ “ይሰራል” የሚል የተስፋ ቃል ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ።

በተለይም የመንግስት መስሪያ ቤቶቹ ሃላፊነቱን አንዱ ወደ ሌላው በመግፋት መፍትሄውን እንዳዘገዩት ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

“ከማዘጋጃ ወደ መንገዶች ደብዳቤ ተልኳል ይሉናል፤ መንገዶች ስንሄድ ደግሞ መልሰው ወደዚህ ይልኩናል። ስራውን አስጀምረው ኦፊሻሊ እንኳን ኑሩበት የሚባል መልስ የለም፤ በእንጥልጥል ላይ ነው ያለነው” ሲሉ በቢሮክራሲው መጉላላታቸውን ነዋሪው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የክረምቱ ወቅት መቃረቡ ስጋቱን እጥፍ ድርብ አድርጎታል ብለውናል።

በህንጻው ውስጥ የሚኖሩ ህጻናትና አረጋውያን ህንጻው ላይ በሚፈጠር ንቅናቄና ንዝረት ሳቢያ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ነግረውናል።

ነዋሪዎቹ “ሰው በስጋት ነው፤ ኃይለኛ ዝናብ ሲጥል ሁሉም ወደ ውጭ ነው የሚወጣው ቢያንስ መንገዱ ባይሰራ እንኳ ህንጻው እንዳይናድ ማጠናከሪያ ስራ እንዲሰራ ነው ጥያቄያችን” በማለት የሚመለከተው አካል ከመዘናጋት ወጥቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ይመለከታቸዋል የተባሉት እና በቦታውም ተገኝተው ተመልከተው ለነበሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንዱሙ ሴታ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልክ ሊነሳለት አልቻለም።

መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው
Tiktok.com/@condoaddis
https://m.youtube.com/@condoaddis
T.me/condoaddis
Linkedin.com/company/condoaddis
Facebook.com/condoadis
❤3