Forwarded from Gech
የማስተማሪያ ዘዴዎች አተገባበር
🔜 የተለመዱ የማስተማሪያ ዘዴዎችን መምህራን በክፍል ውስጥ እንዴት መተግበር እንዳለባቸው የሚረዳ ዝርዝር ተግባራት እንመልከት። እነዚህ ተግባራት መምህሩ ከዝግጅት እስከ ግምገማ ያለውን ሂደት በግልጽ እንዲረዳ ያግዛሉ ብለን እናስባለን።
📘 1. የቃል ዘዴ (Lecture Method)
➡️ ዝግጅት፦ ዋና ዋና ነጥቦችን የያዘ አጭር ማስታወሻ ያዘጋጁ።
➡️ ትግበራ፦ ንግግርዎን በቁልፍ ጥያቄ ይጀምሩ። ድምጽዎን ይለዋውጡ (አንዳንዴ ከፍ፣ አንዳንዴ ዝቅ)።
➡️ ትኩረት፦ ተማሪዎች እንዳይሰለቹ በየ 10 ደቂቃው ጥያቄ በመጠየቅ ንቁ እንዲሆኑ ያድርጉ።
➡️ማጠቃለያ፦ የንግግሩን ፍሬ ሃሳብ በ 2 ደቂቃ ውስጥ ደግመው ይግለጹ።
🧪 2. የማሳያ ዘዴ (Demonstration Method)
➡️ዝግጅት፦ የሚያሳዩትን ሙከራ ወይም ተግባር አስቀድመው ለብቻዎ ሰርተው ይለማመዱ።
➡️ትግበራ፦ ተማሪዎች በሙሉ በግልጽ ማየት በሚችሉበት ቦታ ይሁኑ። እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በዝግታ እያደረጉ ያብራሩ።
➡️ተሳትፎ፦ አንድ ወይም ሁለት ተማሪዎች መጥተው እንዲረዱዎት ወይም እንዲደግሙት ያድርጉ።
➡️ ደህንነት፦ ለሳይንስ ሙከራዎች ጥንቃቄ የሚሹ ኬሚካሎች ካሉ አስቀድመው ያስረዱ።
🗣 3. የቡድን ውይይት (Group Discussion)
➡️አደረጃጀት፦ ከ 4 እስከ 6 ተማሪዎችን የያዘ ቡድን ይመድቡ። በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ መሪና ፀሐፊ እንዲኖር ያድርጉ።
➡️ትግበራ፦ ግልጽ የሆነ የውይይት ርዕስና የጊዜ ገደብ (ለምሳሌ 15 ደቂቃ) ይስጡ።
➡️ክትትል፦ መምህሩ በቡድኖች መካከል እየተዘዋወሩ ሃሳባቸውን ያዳምጡ፣ ካስፈለገም አቅጣጫ ያስይዙ።
➡️ሪፖርት፦ እያንዳንዱ ቡድን የተወያየበትን ሃሳብ ለአጠቃላይ ክፍሉ እንዲያቀርብ ያድርጉ።
🏗 4. የፕሮጀክት ዘዴ (Project Method)
➡️እቅድ፦ ሊደረስበት የሚገባውን ግብ (ለምሳሌ፦ ሞዴል መስራት ወይም ጥናት ማካሄድ) ይግለጹ።
➡️ግብአት፦ ፕሮጀክቱን ለመስራት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችንና የመረጃ ምንጮችን ይጠቁሙ።
➡️ክትትል፦ ፕሮጀክቱ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ከሆነ በየሳምንቱ የደረሱበትን ደረጃ ይፈትሹ።
➡️ውጤት፦ ተማሪዎች የሰሩትን ስራ በክፍል ፊት ለፊት አቅርበው እንዲያስረዱ እድል ይስጡ።
🎭 5. የትወና/ሚና መጫወት (Role Play)
➡️ሁኔታ፦ የሚመሰለው ታሪክ ወይም ሁኔታ (Scenario) ምን እንደሆነ በግልጽ ይግለጹ።
➡️ምደባ፦ ተማሪዎች እንደ ፍላጎታቸው ገጸ-ባህሪያትን እንዲመርጡ ያድርጉ።
➡️ትግበራ፦ ተማሪዎቹ በነጻነት እንዲተውኑ ይፍቀዱ (በጣም ጥብቅ መሆን አያስፈልግም)።
➡️ትንተና፦ ትወናው ሲያበቃ "ከዚህ ትወና ምን ተማራችሁ?" በሚል ውይይት ያድርጉ።
🚌 6. የመስክ ጉዞ (Field Trip)
➡️ቅድመ-ጉዞ፦ የሚሄዱበትን ቦታ ይጎብኙና ፍቃድ ያግኙ። ተማሪዎች ምን ማየትና መጠየቅ እንዳለባቸው ዝርዝር (Checklist) ይስጧቸው።
➡️በጉዞ ወቅት፦ ተማሪዎች ማስታወሻ እንዲይዙና ፎቶ እንዲያነሱ ያበረታቱ።
➡️ከጉዞ በኋላ፦ ተማሪዎች ያዩትንና የተማሩትን የሚገልጽ አጭር ሪፖርት እንዲያቀርቡ ያድርጉ።
🙋♂️ 7. የጥያቄና መልስ ዘዴ (Question-Answer)
➡️ጥራት፦ "አዎ" ወይም "አይደለም" የሚሉ ጥያቄዎችን ይቀንሱ። "እንዴት?" እና "ለምን?" የሚሉ ጥያቄዎችን ያብዙ።
➡️ፍትሃዊነት፦ እጃቸውን ለሚያወጡ ብቻ ሳይሆን ዝም ለሚሉ ተማሪዎችም እድል ይስጡ።
➡️ምላሽ፦ ተማሪው የተሳሳተ መልስ ቢሰጥ እንኳን ሳይነቅፉ ወደ ትክክለኛው መልስ የሚመራ ፍንጭ ይስጡት።
🔄 8. ተግባራት ተኮር (Activity based)
➡️ ዝግጅት፦ መምህሩ የተግባራቱን አሠራር እና ውጤት ቀድሞ ከቤቱ መስራት
➡️መግቢያ፦ የተግባሩን ምንነትና አላማ መግለጽ
➡️ ሥልት፦ ልሥራ ↪️ እንሥራ ↪️ ሥሩ ስልትን መከተል
➡️ትግበራ፦ ተማሪዎች ተግባራትን እንዲሠሩ ግልጽ መመሪያ መሥጠት፣ መከታተል፣ መደገፍ
➡️ግብረ መልስ፦ ግብረ መልስ በአቻ፣ በመምህሩ መስጠት
➡️ማጠቃለያ፦ የተግባሩን ዋና ፍሬ ሀሳብ ማጠቃለል።

Forwarded from Zege
G-8 Citizenship Model 2018.pdf
544.4 KB
❗️❗️❗️የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና
👉አዘጋጅ ቦሎ ክ/ከተማ❗️❗️❗️
👉አዘጋጅ ቦሎ ክ/ከተማ❗️❗️❗️
Forwarded from Zege
G-6 Moral Education Model 2018.pdf
519.7 KB
❗️❗️❗️የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና
👉አዘጋጅ ቦሎ ክ/ከተማ❗️❗️❗️
👉አዘጋጅ ቦሎ ክ/ከተማ❗️❗️❗️
Forwarded from Zege
yaka sub city social studies model exam.pdf
186.1 KB