EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
133K subscribers
45.3K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙበት ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ፦ (በምሥል)
🔥2❤1
“የምንከተለው ፖሊሲ ‘የሕዝባችንን የዕለት ተዕለት ሕይወት ቀይሯል ወይ?’ የሚለው ጥያቄ ዋነኛ የሕልውና መለኪያ ነው”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"የሕዝባችን የዕለት ተዕለት ሕይወት በምንከተለው ፖሊሲ እና እምነት ምክንያት የተሻለ ሆኗል ወይ?” የሚለው ጥያቄ እያንዳንዱ የፖለቲካ መሪ ራሱን ሊጠይቅ የሚገባው ዋነኛ የሕልውና መለኪያ መሆን እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ::

“ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መፃኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ባለው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል
🙏5❤1
“ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሀገራዊ ግቦች ላይ እየተስማሙ፣ የዕቅዶችን አፈጻጸም፣ ወጪ እና ውጤታማነት መጠየቅ እና መሞገት ይችላሉ፤ መንግሥትም ለጥያቄዎቹ ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት አለበት።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍5❤2
ከመደመር ማዕቀፍ እስከ አህጉራዊ ትሥሥር

መደመር ለአፍሪካ ማለት የጋራ ሉዓላዊነትን፣ የኢኮኖሚ ትሥሥርን እና የሰላም አርማን ከፍ አድርጎ ማስቀጠል ማለት ነው::

አፍሪካዊ ብልጽግና በእጃችን ተቀርጿል!
❤6
የአፍሪካ መጻኢ ዕድል የተመሠረተው ሀገራዊ አቅማችንን ወደ ውጤታማ አቅም መቀየር በምንችልበት ቁመና ላይ ነው፦ አቶ አደም ፋራህ

በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ መጻኢ ዕድል ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው የያዝነውን ሀገራዊ አቅም ወደ እውነተኛ እና ውጤታማ አቅም መቀየር በሚቻልበት ቁመና ላይ ነው ሲሉ ገልጸዋል::

“ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አደም ፋራህ፣ የፖለቲካ ኃላፊነት ሁልጊዜም የልማት እና የዕድገት ማዕከል ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል
👍4❤1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ::

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በአህጉራዊ አስተዳደር፣ አካታች የፖለቲካ ሂደቶች፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ የልማት ጉዳዮች እንዲሁም የአፍሪካን አመራር በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ አድርገናል” ብለዋል
🙏5❤1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ሐሳቦች

• የማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የመንግሥት ውሳኔ ትክክለኛ መለኪያ የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ሕይወት ማሻሻል መቻሉ ነው::

• ዕድገት እና ለውጥ ወደ ዜጎች ደጃፍ ካልደረሰ፣ ሕዝቡ በፓርቲዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የፖለቲካ ሥርዓቱ ላይ እምነት ያጣል
❤8
በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕዝብ እና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል አለባቸው፡- መሀሙድ አሊ ዩሱፍ

በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕዝብ እና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል እንዳለባቸው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ አስገነዘቡ::

2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ “ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል
👍2❤1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቧቸው ሁለቱ ዋና ዋና ምክረ ሐሳቦች

በሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ መድረክ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በሚጸድቀው ‘የአዲስ አበባ የአቋም መግለጫ’ ውስጥ እንዲካተቱ አህጉራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሁለት ታላላቅ ሐሳቦች ለአፍሪካ የፖለቲካ መሪዎች አቅርበዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት የመጀመሪያው ጥሪ፤ “ከምርጫ ውድድሮች ባሻገር የሚጸኑ ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ግቦች ላይ መስማማት” የሚል ነው
❤7
መደመር መከፋፈልን አሸንፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚገነባ የጋራ ቤታችን ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መሪዎች የተውጣጣ አዲስ የመደመር መንግሥት ማቋቋሙን ተናግረዋል
❤7
መደመር መከፋፈልን አሸንፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚገነባ የጋራ ቤታችን ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መሪዎች የተውጣጣ አዲስ የመደመር መንግሥት ማቋቋሙን ተናግረዋል
❤4
"መደመር ማለት ሌሎች በጀመሩት ላይ መገንባት ማለትም ነው። ቀደም ሲል የተጀመሩ ሀገራዊ ሥራዎችን አጠናክሮ መጨረስ፤ ለዚህም የሕዳሴ ግድብ ማሳያ ነው።” …

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤9
ከደመና በላይ የCOP32 ጉባኤን ስኬት ለማብሰር ሁሌም ዝግጁ ሆኖ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ማንኛውም ታላቅ ጉዞ የሚጀምረው በእምነትና በተቋማዊ ጥንካሬ ነው፤ እያንዳንዱ መዳረሻ ደግሞ ሕዝቦችን፣ ባህሎችንና አዳዲስ ዕድሎችን እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ወሳኝ ድልድይ ይፈጥራል::

የአፍሪካ ግዙፉና መሪው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Ethiopian Airlines) የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሀገራችንን ታሪክ፣ ቅርሶች፣ ራዕይና የከፍታ ምኞት ወደ ተለያዩ የዓለማችን ማዕዘናት የሚያደርስ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የብሔራዊ ማንነታችን ሕያው መገለጫ ነው
❤11
መረጃ ማሻሻያውና የኢትዮጵያ አዲስ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ እውነት በጂዲፒ መለኪያ ለውጥ አንድምታ

ኢትዮጵያ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረቷንና የመነሻ ዓመቷን በማሻሻል የአህጉራችን 5ኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ መሆኗ ተረጋግጧል::

በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት በሐምሌ ወር በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት 210.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል
❤4👍2
የመደመር መንግሥት የዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት የመለወጥ ጉዞ

የፖለቲካ አስተሳሰቦች፣ ርዕዮተ ዓለሞች እና የመንግሥታት ፖሊሲዎች እውነተኛ ፋይዳ የሚለካው፤ በሚተላለፉ ውሳኔዎች፣ በሚወጡ መመሪያዎችና በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት በበጎ መልኩ መቀየር ሲችሉ ነው::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የመንግሥት ውሳኔ ትክክለኛ መለኪያ የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ሕይወት ማሻሻል መቻሉ ነው" በማለት በሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፣ የፖለቲካ ሥልጣንና የአመራር ሚና የመጨረሻ ግብ ምን መሆን እንዳለበት ግልጽ ያደረገ መርህ ነው
❤3
የፖሊሲ ልዩነቶች ሳይገድቧቸው በጋራ ግብ ላይ መስማማትና አዲስ መሪዎችን ማፍራት ይገባል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፖሊሲ ልዩነቶች ሳይገድቧቸው በጋራ ግብ ላይ መስማማትና አዲስ መሪዎችን ማፍራት ይገባቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና ጉባኤ ባደረጉት ንግግር፣ ከምርጫ በላይ የሆኑ እና የሀገርን የረጅም ጊዜ የልማት ግቦች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊያስቀጥሉ የሚችሉ የብሔራዊ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

የፖሊሲ ልዩነቶች ቢኖሩም ገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በዋና ዋና የረጅም ጊዜ ግቦች ላይ ሊስማሙ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ "ፖሊሲዎቻችን ይለያያሉ፣ መራጮች ይመርጣሉ፣ ነገር ግን አንዳንድ ብሔራዊ ጥረቶች ለመንግሥት ውጥን መትረፍ አለባቸው" ሲሉ አስረድተዋል::

በተጨማሪም አዲስ መሪዎችን ማፍራት እና ተተኪዎችን ማዘጋጀት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል
❤3👍3
የመደመር እሳቤ ኢትዮጵያን የታላቅነት ማሳያ እያደረጋት ነው፡- የአህጉራዊ ጉባኤው ተሳታፊዎች

የመደመር እሳቤ አዲስ አበባን የአፍሪካ እውነተኛ መዲና እና ኢትዮጵያን ደግሞ የታላቅነት ማሳያ እያደረጋት መሆኑን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት እሳቤ ከተሞቿን በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እና የተቀላጠፈ አኗኗርን ለመፍጠር የሠራቻቸው ሰፊ ሥራዎች ፍሬ እያፈሩ ይገኛሉ::

ይህንኑ እውነታ በሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተሳታፊዎች በሰጡት ምስክርነት አረጋግጠዋል
❤10👏1
ከአፍሪካ ሕብረት እስከ ኮፕ 32፤ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ዲፕሎማሲ የምታስመዘግበው ታሪካዊ ምዕራፍ

መዲናችን አዲስ አበባ ለዓመታት የአፍሪካ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ የልብ ትርታ ሆና የቆየች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ተመራማሪዎች ተሰብስበው የአህጉሪቱን የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚወስኑባት፣ የሚደራደሩባት እና የጋራ ራዕይ የሚቀርጹባት ናት::

ከተማዋ የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) ዋና መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከ130 በላይ የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ ከኒው ዮርክ እና ጄኔቫ ቀጥሎ በዓለም ላይ ሦስተኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል ናት
❤7
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ታሪካዊ ግንኙነታቸውንና ስትራቴጂያዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የመከላከያ ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ከውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር የሚያደርጉትን ተከታታይ የወታደራዊ ዲፕሎማሲ ውይይት በመቀጠል፣ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጃሲንቶ ማሲንጋ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል::

ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት፣ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራና በውጤት የታጀበ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል
❤20👍6