Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.66K photos
76 videos
20 files
995 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
በሻሸመኔ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የ2019 ግምገማዊ ስልጠና ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 14/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የ2019 የሀጅ ጉዞን ከቀደሙ ዓመታት የላቀ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስስሳረዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የቅድመ ዝግጅቱ አካል የሆነው ግምገማዊ ስልጠና በሻሸመኔ ከተማ ሲከናወን የቆዬ ሲሆን በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በስልጠናው ላይ የኦሮሚያ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ እና የሶማሌ ክልል የሀጅ ዑምራ ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሀጅ ምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሀጅና ኡምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሐመድሷሊህ በበይነ መረብ ለሰልጣኞች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዶክተር መሐመድሳሊህ በዚህ መልዕክታቸው የባለፈው ዓመት የሀጅ አገልግሎት በስኬት እንዲጠናቀቅ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎችእና የምዝገባ ጣቢያ ሠራተኞች ሚና ከፍተኛ እንደነበረ ገልጸው ባለፈው ዓመት የተገኘው የላቀ ውጤት በተሻለ ሁኔታ እንዲደገም በቅንጅት መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሸይኽ ኢስሀቅ አደም በበኩላቸው በአቅም ግንባታ ስልጠናው ባለፈው ዓመት የነበሩ ክፍተቶች ታርመው ካለፉት ዓመታት የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ በሚያስችል መልኩ እንዲከናወን ያግዛል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ጉዞ ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ ሀጅ ጀማል ኢብራሂም እና የሲስተም ዴስክ ኃላፊ ሀጂ አብዱሰላም ዑስማን በጋራ ስለዲጂታል ሲስተም አጠቃቀም ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱና በክልል የሐጅና ዑምራ ዘርፎች መካከል ያለውን የመረጃና የሥራ ቅንጅት በማጠናከር ሁጃጆች ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ስልጠናው እንደሚያግዛቸው ሰልጣኞች ጠቅሰዋል።

ሶስተኛው ዙር የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ግምገማዊ ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1