የሁለተኛ ዙር የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ግምገማዊ ስልጠና በሻሸመኔ ከተማ ነገ ይካሄዳል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 13/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 12/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የ2019/1448 የሐጅ ጉዞ አገልግሎትና መስተንግዶን ውጤታማ ለማድረግ በማሰብ እየተካሄደ ያለው ግምገማዊ ስልጠና በነገው ዕለት ለሁለተኛ ዙር በሻሸመኔ ከተማ ይቀጥላል።
በግምገማዊ ስልጠናውም ላይ የክልል መጅሊስ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎችና የምዝገባ ጣቢያዎች ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን ስልጠናው የ2018/1447 የሐጅ ጉዞ ምዝገባን ለማስጀመር ከሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መካከል አንዱ እንደሆነ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሸይኽ ኢስሀቅ አደም ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም የዚህን ዓመት የሐጅ ምዝገባ አገልግሎት ፈጣን፣ ምቹና ተደራሽ ለማድረግ ግምገማዊ ስልጠናው ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
የስልጠና መረሀ ግብሩ ከተጠናቀቀና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከተጠናቀቁ በኋላ የ2019 የሐጅ ምዝገባ በቅርብ ቀናት የሚጀምር በመሆኑ ንያ ያላቸው ሁሉ አስፈላጊ ሰነዶችን አዘጋጅተው እንዲጠብቁም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

የ1448 ዓ.ሂ የሐጅ ጉዞን አስመልክቶ በሐጅና ዑምራ ዘርፍ እና በዑለማ ጉባዔ መካከል ውይይት ተካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 14 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ እና የዑለማእ ጉባኤ የሥራ ኃላፊዎች በ2019 የሐጅ ጉዞ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ በውይይቱ ላይ ሁጃጆች ወደ ሳውዲ አረቢያ ከማቅናታቸው በፊትና በጉዞው ወቅት ተከታታይ የሐጅ አደራረግ ትምህርት (መናሲከል ሐጅ) እንዲያገኙ ዑለማዎች ከዚህ ቀደሙ የተሻለ የዳዕዋ ስራ ይሰራሉ ብለዋል።
የዳዕዋ ስራው ሁጃጆች የሐጅን ህግጋት በደንብ እንዲረዱና እንዲተገብሩት ያግዛልም ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝደንቱ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጂና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ዑስታዝ ፈይሰል ዑመር በበኩላቸው በዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እና በዐሊሞች መካከል ያለው ቅንጅት የሐጅ ጉዞው የተሳካና ለሁጃጆች ምቹ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
በውይይቱ የሐጅ ተጓዦች (የአል-ራሕማን እንግዶች) የሐጅ ሥርዓታቸውንና ዒባዳቸውን በእውቀት ላይ ተመስርተው እንዲፈጽሙ በሚቻልባቸው መንዶች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወላይታ ሶዶ ለ100 ኢማሞችና ኡስታዞች ስልጠና መስጠት ጀመረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 14 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ወላይታ ሶዶ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ከቡንያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 50 ኢማሞች እና 50 ኡስታዞች አቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስተባባሪነት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ስልጠና፥ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማዕ ጉባዔ ከፍተኛ የኢስላም ምሁራን (ልሂቃን) የሚሰጥ ነው።
የስልጠናውን መርሃ ግብር በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ኡስታዝ ፋሪስ ጀማል እንደገለጹት ሰልጣኞች የሚሰጣቸውን ትምህርት በጥንቃቄ በመከታተል ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ማህበረሰባቸውን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አካባቢው የኢስላም ምሁራን እጥረት ያለበት በመሆኑ፥ ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ለሌሎች በማካፈልና በማስተላለፍ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ኡስታዝ ፋሪስ ጥሪ አቅርበዋል።
ለስድስት ቀናት ያህል የሚቆየው ይህ ስልጠና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማእ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ከቡንያን አለማቀፍ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ሲያካሂዳቸው የቆያቸው ተመሳሳይ የአቅም ግንባታ ስራዎች አካል መሆኑም ተመልክቷል።