Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.56K photos
76 videos
20 files
993 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ለ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቀቀ ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 21/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 20/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አዳማ |

ለ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቋል።

አውደ ጥናቱ ፈትዋ ለማዘጋጀት የሚረዱ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችና ተሞክሮዎች ለፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀርቧል።

በአውደ ጥናቱ የብሔራዊ የቤተሰብ እቅድ፣ እናቶችና ህፃናት ጤና አፈፃፀም እና ዋና ዋና ማስረጃዎች (እ .አ. 2024/25 የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብ እና ጤና ዳሰሳ /EDHS/ በአቶ ሙባረክ ሐሚድ ከጤና ሚኒስቴር ፣በቤተሰብ ዕቅድ እና በእናትና ሕፃናት ጤና ላይ ያለው ክልላዊ እይታ አቶ አብዲራህማን ፡ ከሱማሌ ክልል ጤና ቢሮ በቀረቡት ሰነዶች ላይ ከወቅታዊነትኒ ከግልፀኝነት አኳያ በሊቃውንቱ የተለያዩ የማብራሪያ ጥያቄዎች ቀርበውበታል።

ሌላው የቤተሰብ ምጣኔ (FP) ፈትዋ ለማዘጋጀት በሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ላይ የተደረገ ውይይት፡ ዋና ዋና ግኝቶች፣ ችግሮች እና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች በ አቶ አድነው ሁሴን፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና (RH) አማካሪ ፣በአቶ ሱልጣን አህመድ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አቅራቢነት ከሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች ጋር በቤተሰብ ዕቅድ፣ በእናትና ሕፃናት ጤና፣ በጾታዊ ጥቃትና መቀንጨርን በመከላከል ዙሪያ የኢንዶኔዢያ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ስልታዊ እቅድ ሰነድ ሊቃውንቱ በሰፊው ውይይት አድርገውበታል።

ፈተዋ መስጠት የነብያችን ሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሃይማኖታዊ መመሪያን የማድረስ ሚናን የሚተካና ከፍተኛ ኃላፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ፤ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህና የኡሱል አል-ፊቅህ እውቀት ባላቸው ሙፍቲዎች ፈትዋ ለመስጠት እንዲቻል የአዲስ አበባ ፣ የሶማሌና የአፋር የፈተዋ ቋሚ ሰብሳቢዎች በአውደ ጥናቱ ላይ በተለያየ ምክንያት ባለመገኘታቸው ምክንያት የጥናቱ ሰነድ ቅጂ ተልኮላቸው በቀጣይ ብያኔያቸው ለፌደራል ፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ እንዲልኩ ፤ የፌደራሉም የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ም የቀረቡ ሰነዶቹን መርምሮ በቀጣይ ፈተዋ ለመስጠት ወስኗል።

በአውደ ጥናቱ ላይ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጥናትና ምርምር ዘርፍ በዶክተር ኢብራሂም ሀሰን አቅራቢነት የቀረበው ሰነድ ፣ የሸሪዓ ዓላማዎችን፣ የጋብቻና የልጆችን ደረጃ፣ እንዲሁም የቤተሰብ ምጣኔና ወሊድን መቆጣጠርን በሸሪዓ እይታ ቀርቦ በፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ በሆኑት በዶክተር ሙሀመድ ሀሚዲን አወያይነት በሊቃውንቱ የማዳበሪያ ሃሳብ ተሰጥቶበት ሰነዱ በኮሚቴው ፀድቋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc