Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.55K photos
76 videos
20 files
992 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ለ1448 ዓ.ሂ. ሐጅ ከሳዑዲው መሻሪቅ አልማሲያ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 24/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 23/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ለ2019 (1448 ዓ.ሂ) ኢትዮጵያዊ ሑጃጆች ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ከሳዑዲ ዓረቢያው ግዙፍ የአገልግሎት አቅራቢ ተቋም መሻሪቅ አልማሲያ ሸሪካ ጋር ተፈራረመ።

​በመካ ከተማ የተከናወነውን የውል ስምምነት የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሷሊህ ጀማል እና የመሻሪቅ አልማሲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በንደር ቢን አብዱረህማን አልደመንሁሪ ሰነዱን ተፈራርመዋል።

​የውል ስምምነቱ በ2019 (1448 ዓ.ሂ) የሐጅ ጉዞ ለሚሳተፉ 8,000 ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ደህንነታቸው የተረጋገጠ እና ተጠያቂነት የሰፈነባቸው ለማድረግ ያለመ ነው።

ሁለቱ ወገኖች በሐጅ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የሁጃጆችን ምቾት፣ ደህንነትና እርካታ እንዲረጋገጥ ለማስቻል በትኩረት እንደሚሰሩ የተመላከተ ሲሆን የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሃመድ ሷሊህ የ2019 (1448 ዓ.ሂ) የሐጅ ዝግጅት በዘመናዊ አሰራር ተደራጅቶ በአግባቡ እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ከመሻሪቅ አልማሲያ ጋር የተደረሰው ስምምነት የቅድመ ዝግጅት ስራው አካል መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ሀጅና ዑምራ ዘርፉ በቀጣይም ከሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የሁጃጆችን የትራንስፖርት አገልግሎት ምቾትና ደህንነት የሚያረጋግጥ የውል ስምምነት ተፈረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 26/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 25/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከሳዑዲ ዓረቢያው የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ሰማያ የትራንስፖርት ኩባንያ ጋር የትራንስፖርት አገልግሎት ውል ስምምነት ተፈራረመ።

​የውል ስምምነቱ ለ2019 (1448) ሁጃጆች ደህንነቱ የተረጋገጠ፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ እና በሰማያ የትራንስፖርት ኩባንያ መካከል የተፈረመው የውል ስምምነት በጥብቅ መስፈርቶችና የአሠራር መርሆዎች መሰረት ተፈጻሚ እንደሚደረግም ተመላክቷል።

የሁጃጆች የጉዞ መርሃ ግብር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ብቻ እንዲከናወን የሚያስችለው ይህ የውል ስምምነት በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች በቅንጅትና በፍጥነት ለመፍታት ትልቅ አቅም ከመፍጠሩ ባሻገር የትራንስፖርት አገልግሎቱ የሁጃጆችን አጠቃላይ የጉዞ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የሚያካትትም ይሆናል።

​የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ የ2019 (1448 ዓ.ሂ.) የሐጅ አገልግሎት ቅድመ ዝግጅቱን በተቀናጀ መንገድ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከሰማያ የትራንስፖርት ኩባንያ ጋር የተደረገው ስምምነትም የዚሁ አካል እንደሆነ የጽህፈት ቤቱ የስራ ኃላፊዎች በውልል ስምምነቱ ወቅት አብራርተዋል።

​ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ለኢትዮጵያዊ ሁጃጆች የተሟላና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
​
​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ የሰጠውን ውሳኔ ተከተሎ በትላንትናው ዕለት የኢፌዴሪ መንግስት በመመስረቱ የተሰማውን ደስታ ይገልፃል።
​
ለተከበሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ለክልል እና ለከተማ አስተዳድር ፕሬዝደንቶችና ከንቲባዎች በሙሉ ከህዝብ የተጣለባችሁን አደራ እና ኃላፊነት በአግባቡ እንድትወጡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲያግዛችሁ እንማጸነዋለን።

የመረጣችሁ ህዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋቸውን ሰላም፣ ልማት እና እድገት ለማምጣት በምታደርጉት ጥረት ሁሉ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ለመግለጽ እንወዳለን።

​ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሀገራችን ወንድማማችነት፣ የህግ የበላይነት እና እኩልነት እንዲሰፍን ከመንግስት እና ከህዝባችን ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ እየገለጽን ዘመናትን ያስቆጠረው የሀገራችንን የመቻቻል፣ የመከባበር እና የአብሮነት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህዝበ ሙስሊሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ አዎንታዊ ሚናውን እንዲወጣ አደራ እንላለን።

​በመጨረሻም አዲሱ መንግስት የተጣለበትን ሀገራዊ አደራ እና የህዝብ ፍላጎት በትክክል ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እንዲሰራ እየጠየቅን ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን እንመኛለን።

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

26/01/209
ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ለ2019 (1448 ዓ.ሂ.) ሁጃጆች የምግብ አቅርቦት ውል ስምምነት ተፈራረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 27/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 26/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ለ2019 (1448 ዓ.ሂ.) ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የሚቀርበውን የምግብ አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ ማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ከሳዑዲ ዓረቢያ የምግብ አቅራቢ ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ።

​የውል ስምምነቱ በሀጅ ወቅት ለሁጃጆች ምግብ በወቅቱና በጥራት ለማቅረብ እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን የምግብ አቅርቦቱ የሁጃጆችን ጤና፣ ደኅንነትና ምቾት የጠበቀ ይሆናልም ተብሏል።

​የምግብ አቅራቢ ድርጅቶቹ በየዕለቱ የሚያቀርቡት ምግብና መጠጥ ጥብቅ የንጽህና፣ የጥራትና የደኅንነት መስፈርቶችን ማሟላቱ የሚረጋገጥ ሲሆን አቅርቦቱ ስምምነት በተደረበት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በመካ፣ በመዲና እና የሐጅ ሥርዓት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ሁሉ ያለ ምንም መስተጓጎል ተደራሽ ይሆናል።

በአቅርቦት ሂደት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ እክሎችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋትም የውል ስምምነቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶውን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት በቀጣይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1