Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.55K photos
76 videos
20 files
992 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ለ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቀቀ ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 21/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 20/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አዳማ |

ለ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቋል።

አውደ ጥናቱ ፈትዋ ለማዘጋጀት የሚረዱ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችና ተሞክሮዎች ለፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀርቧል።

በአውደ ጥናቱ የብሔራዊ የቤተሰብ እቅድ፣ እናቶችና ህፃናት ጤና አፈፃፀም እና ዋና ዋና ማስረጃዎች (እ .አ. 2024/25 የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብ እና ጤና ዳሰሳ /EDHS/ በአቶ ሙባረክ ሐሚድ ከጤና ሚኒስቴር ፣በቤተሰብ ዕቅድ እና በእናትና ሕፃናት ጤና ላይ ያለው ክልላዊ እይታ አቶ አብዲራህማን ፡ ከሱማሌ ክልል ጤና ቢሮ በቀረቡት ሰነዶች ላይ ከወቅታዊነትኒ ከግልፀኝነት አኳያ በሊቃውንቱ የተለያዩ የማብራሪያ ጥያቄዎች ቀርበውበታል።

ሌላው የቤተሰብ ምጣኔ (FP) ፈትዋ ለማዘጋጀት በሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ላይ የተደረገ ውይይት፡ ዋና ዋና ግኝቶች፣ ችግሮች እና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች በ አቶ አድነው ሁሴን፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና (RH) አማካሪ ፣በአቶ ሱልጣን አህመድ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አቅራቢነት ከሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች ጋር በቤተሰብ ዕቅድ፣ በእናትና ሕፃናት ጤና፣ በጾታዊ ጥቃትና መቀንጨርን በመከላከል ዙሪያ የኢንዶኔዢያ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ስልታዊ እቅድ ሰነድ ሊቃውንቱ በሰፊው ውይይት አድርገውበታል።

ፈተዋ መስጠት የነብያችን ሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሃይማኖታዊ መመሪያን የማድረስ ሚናን የሚተካና ከፍተኛ ኃላፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ፤ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህና የኡሱል አል-ፊቅህ እውቀት ባላቸው ሙፍቲዎች ፈትዋ ለመስጠት እንዲቻል የአዲስ አበባ ፣ የሶማሌና የአፋር የፈተዋ ቋሚ ሰብሳቢዎች በአውደ ጥናቱ ላይ በተለያየ ምክንያት ባለመገኘታቸው ምክንያት የጥናቱ ሰነድ ቅጂ ተልኮላቸው በቀጣይ ብያኔያቸው ለፌደራል ፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ እንዲልኩ ፤ የፌደራሉም የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ም የቀረቡ ሰነዶቹን መርምሮ በቀጣይ ፈተዋ ለመስጠት ወስኗል።

በአውደ ጥናቱ ላይ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጥናትና ምርምር ዘርፍ በዶክተር ኢብራሂም ሀሰን አቅራቢነት የቀረበው ሰነድ ፣ የሸሪዓ ዓላማዎችን፣ የጋብቻና የልጆችን ደረጃ፣ እንዲሁም የቤተሰብ ምጣኔና ወሊድን መቆጣጠርን በሸሪዓ እይታ ቀርቦ በፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ በሆኑት በዶክተር ሙሀመድ ሀሚዲን አወያይነት በሊቃውንቱ የማዳበሪያ ሃሳብ ተሰጥቶበት ሰነዱ በኮሚቴው ፀድቋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc
የፌዴራል የክልልናከተማ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 24/ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 23/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ           
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባኤ   በመተባበር ያዘጋጁት  የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምሯል።

በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ ባደረጉት ንግግር፣ የሕዝበ ሙስሊሙ የመልካም አስተዳደር የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው አዲሱ የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1428/2018 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።

አዲሱ አዋጅ ላለፉት 25 ዓመታት አገልግሎት ላይ የቆየውን አዋጅ ቁጥር 188/1992 ሙሉ በሙሉ የሚተካ መሆኑንም አብራርተዋል።

​ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም ዳኝነት (ቃዷእ) በኢስላም ውስጥ ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን፣ የሰዎችን መብት ለማስከበር እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው በመሆኑ፣ ሰልጣኞች ለትምህርቱ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ አገልግሎታቸው ላይ ሊተግብሩት  እንደሚገባም   የአደራ መልዕክታቸውን  አስተላልፈዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ መከተ ሙሄ በበኩላቸው፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁ የሆነ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል።
​በዚሁ መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የተቋሙን አደረጃጀት የሚያጠናክሩና የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የአሰራር ስርዓቶችን ከመዘርጋት ጎን ለጎን፣ የባለሙያዎችን ብቃት የሚያሳድጉ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በቀጣይነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

​ለተከታታይ 10 ቀናት በሚቆየው በዚህ የስልጠና መርሃ ግብር ላይ የፌዴራል እና የክልል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች (ቃዲዎች) በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1