Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.66K photos
76 videos
20 files
995 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞች የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 1/ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 30/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞች (ቃዲዎች) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት የተጀመረው የ"ሸገርን ማስበብ" ፕሮጀክት አካል የሆነውን የእንጦጦ እስከ ፒኮክ ና ቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኝተዋል።

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተጀመሩ ታላላቅ የከተማ ውበት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የመዝናኛ ልማት ስራዎች መካከል አንዱ እና ዋነኛው መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተነግሯል።

​የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ መከተ ሙሄ
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ራዕይ አፍላቂነት እና በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራር ሰጪነት የተከናወነው የወንዝ ዳርቻ ልማት በከተማችን ያመጣውን ዘመናዊ ለውጥና ውበት ማሳየት መሆኑን ተናግረዋል።

ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞቹ (ቃዲዎቹ) "አይቻልም" የሚለውን አስተሳሰብ በመስበር፣ ወደየክልሎቻቸውና ወደተሰማሩበት የሙያ መስክ ሲመለሱ አወንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ለማነሳሳት ያለመ መሆኑን አመላክተዋል።

የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼይኸ አብዱልመናን መሀመድ አህመድ በበኩላቸው፣ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞች (ቃዲዎች) መንግስት የሰራቸውን ታላላቅ የልማት ስራዎች በአካል ተገኝተው በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
የፌደራል ፣ የክልልና የከተማ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞች በበኩላቸው በጉብኝቱ መደሰታቸውን ተናግሰዋል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባኤ በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 1/ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 30/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባኤ በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።

ዛሬ በተደረገው የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕረዚዳንት ሼይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ ጨምሮ ዓሊሞች የጠቅላይ ምክር ቤቱና የአዲስ አበባ መጅሊስ ሥራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕረዚዳንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በስልጠና መርሀ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የዘመናት የሕዝበ ሙስሊሙ የፍትሕ ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኝ ብቃት ያላቸውን ቃዲዎችን በውድድር እንዲሟሉ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

አዲሱን አዋጅ ታችኛው መዋቅር ድረስ በማስረፅ ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ቃዲዎች እራሳቸውን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ቴውድሮስ ምህረት በበኩላቸው የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አሰራር እንዲሻሻል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ቤቱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ መቆየቱን ተናግረዋል።

ጥናቶችን መሠረት ያደረገ የመጀመሪያ መፍትሔ የሆነው የህግ ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን ፕረዚዳንቱ ተናግረው ዳኞች በነፃነት ፣ በፍትሐዊነት ና በገለልተኝነት ሕግና አሰራርን መሠረት በማድረግ በቁርጠኝነት የሰጣቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት ሼይኽ መከተ ሙሄ በበኩላቸው የዳኝነት ተቋማት በሰዎች ንብረትና ነፃነት ላይ የሚወስኑ በመሆናቸው ዳኞች የሚሰሩባቸው ህጎች ላይ በቂ እውቀት፣ የዳበረ ክህሎት እና የተጣለባቸውን ከባድ ሀላፊነት በብቃትና በታማኝነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የፍትህ አስተዳደር ጥራትና እድገት የዳኞች ወቅታዊና ተከታታይ ስልጠና አማራጭ ሳይሆን ግዴታ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1