Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.54K photos
76 videos
20 files
991 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከተለያዩ ባንኮች ጋር የስራ ውል ስምምነት ተፈራረመ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 16/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ የ2019 ዓል.(1448 ዓ.ሒ) የሐጅ ጉዞ ምዝገባና ክፍያን በተሻለ የአገልግሎት ጥራት ለማከናወን የሚያስችለውን መጠነነሰፊ የዝግጅት ስራ እያከናወነ ይገኛል።

ዘርፉ በዛሬው ዕለትም ከተመረጡ ባንኮች ጋር በአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ዙሪያ ውይይት ካደረገ በኋላ የሁለትዮሽ ውል ስምምነት ተፈራርሟል።

ውይይቱ የአረህማን እንግዶች የሚፈጽሙትን ክፍያ ዘመናዊ፣ ግልጽና ፈጣን ለማድረግ ያለመ ነው።

​በስምምነት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን የሑጃጆች ምዝገባ "የላቀ አገልግሎት ለሑጃጆች እርካታ" በሚል መሪ ሀሳብ መጀመሩን አስታውሰው ባንኮቹ በተፈራረሙት ውል ስምምነት መሠረት ለአረህማን እንግዶች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሷሊህ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ከሳውዲ አረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር የተገኘው የዳይመንድ ደረጃ ሽልማት የባንኮችም ጭምር መሆኑን ጠቅሰው የዘንድሮው የሐጅ አገልግሎት በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

​ንያ ያላቸው አማኞች የሳዑዲ አረቢያ ሀጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የመመዝገቢያ ጊዜ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ወዳዘጋጃቸው ዘመናዊ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት ምዝገባቸውን ከወዲሁ እንዲያከናውኑ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ ጥሪ አቅርበዋል።

ከተጀመረ ቀናት ያስቆጠረው የዚህ ዓመት የሐጅ ጉዞ ምዝገባ እስከ ጥር 10 /2019 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ባንኮች በገቡት ውል መሰረት ለአረህማን እንግዶች በሁሉም የምዝገባ ማዕከላት ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያና የሩሲያ ኢስላማዊ ተቋማት ሃይማኖታዊ ትብብራቸውንና የጋራ ልማታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አካሄዱ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 16/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሞስኮ|

በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከርና በኢስላማዊ ተቋማት ደረጃ ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ውይይት ተካሄደ።

​በሁለትዮሽ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና የሩሲያ ሙስሊሞች መንፈሳዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሙፍቲ ዐይነዲን ራዊ ተሳትፈዋል።

​የዚህ ታሪካዊ ውይይት ዋና ዓላማ በሁለቱ አገራት ኢስላማዊ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር፣ የሰላም ግንባታ፣ የሰብአዊ እርዳታና የጋራ ልማት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሆነ ተገልጿል።

​በውይይቱ ወቅት በሁለቱ አገራት ኢስላማዊ ተቋማት መካከል ያለውን የልምድ ልውውጥ ማሳደግ፣ የዘካ ፈንድ አስተዳደርን ማዘመን፣ በሰብአዊ እርዳታ ፕሮጀክቶች ላይ በትብብር መስራት፣ በሃይማኖቶች መካከል ያሉትን የጋራ እሴቶች ማጠናከር የሚያስችሉ ነጥቦች በስፋት ተነስተዋል።

በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የሰላም ጥረቶችን በጋራ መደገፍ በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

​ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ሃይማኖታዊ ተቋማት መካከል ያለውን ወዳጅነት የሚያጠናክር ከመሆኑም ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከናወኑ የሰላምና የልማት ስራዎች አዎንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ይህ ዓለም አቀፍ ውይይት በነገው ዕለትም የሚጠናቀቅ ሲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ለማወቅ ችለናል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1