የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የቀጣይ 5 ዓመታት ስልታዊ ዕቅድ ዝግጅት ማስጀመሪያ ምክክር አደረገ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 14/2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ|
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የሆነው አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የአምስት ዓመታት ስልታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት የሚያስችለውን ውይይት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችናየዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት አስጀመረ።
ተግባራዊ የሚያደርገው የሚተገብረውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ይፋ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አዘጋጀ።
ስልታዊ ዕቅዱ ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን የልማት፣ የበጎ አድራጎት እና የትምህርት አገልግሎቶች ጥራት ይበልጥ ውጤታማ እና ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ በውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ ተቋማት ያለ ስልታዊ ዕቅድ የሚያደርጉት የስራ እንቅስቃሴ ለሀብት ብክነትና ለውጤት አልባነት የሚዳረግ መሆኑን ውይይቱን ባስጀመሩበት ንግግራቸው ገልጸዋል።
አወልያ እያከናወናቸው ያሉት የልማትና የሰብዓዊ ዕርዳታ እና የትምህርት ሥራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃ እያደረጉ እንደሚገኙ አስታውሰው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለስልታዊ ዕቅድ ዝግጅቱና ለትግበራው ተባባሪ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጀማል መሐመድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለው አወልያ የጠቅላይ ምክር ቤቱን እና የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸው ለድርጅቱ ርዕይ መሳካት ባለድርሻ እና አጋር የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ በዚሁ መድረክ እንደተናገሩት የሚዘጋጀው ስልታዊ ዕቅድ ጥራት በአማካሪው ብቃት ብቻ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ የመረጃ ምንጮች ትክክለኛ፣ ግልጽና ጥራት ያለው መረጃ መስጠት አለባቸው።
የእርዳታና ልማት ድርጅቱ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በሥሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በተቀናጀ አሰራር በመምራት በአገር ደረጃ ውጤታማ ማድረግ መቻሉንም ሀጅ ሰዒድ አስማረ አክለዋል።
ስልታዊ ዕቅዱን የማዘጋጀት ኃላፊነት የተረከበው የሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌዲዮን ገሞራ በዕቅድ ዝግጅት ሂደቱ ላይ ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
የዕቅድ ዝግጅቱ ቡድን መሪ የሆኑት ዶክተር ብርሃኑ ነገሪ እና ዶክተር ጀሚላ ሁሴን ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ሰነድ አቅርበው ተሳታፊው ሰፊ ውይይት አድርጎባቸዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት