ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ ከህዝበ ሙስሊሙ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 25/2018 ዓ.ል| ረቢዕ አል አወል 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ|
በሙስሊሞች መብት መከበር ዙሪያ ትኩረት አድርጎ ለበርካታ ዓመታት እየሰራ የሚገኘው ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ ለህዝበ ሙስሊሙ መብት መከበር ላበረከተው እና እያበረከተ ላለው ጉልህ አስተዋጽኦ ከህዝበ ሙስሊሙ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት።
ደረሳው ሰዒድ በሚል ስያሜ በሚሰራቸው ኢስላማዊ የኪነ ጥበብ ስራዎቹ የሚታወቀው ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ አሁን ላይ ሀሩን ሚዲያ በሚል ስያሜ በመሰረተው የሚዲያ ተቋሙ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሙስሊሞች መብት እንዲከበር እየሰራ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ሳፋየር አዲስ በተካሄደው የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ የምስክር ወረቀት፣ የዋንጫ እና ልዩ ልዩ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሚዲያን ሃያልነት እና ህዝበ ሙስሊሙ በዘርፉ ያለው ክፍተት የተገለጹ ሲሆን ለህዝበ ሙስሉሙ መብት መከበር እየተንቀሳቀሱ ያሉበእንደ ሃሩን ሚዲያ ያሉ ተቋማት እንዲጠናከሩ ሁሉም ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ተላልፏል።
በበጎ ፈቃደኛ ሙስሊሞች አስተባባሪነት እውቅና የተበረከተለት አብዱረሂም አህመድ የተሰጠው እውቅና በሚዲያ ዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።
በእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ መሻይሆች፣ ዱዓቶች፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች፣ የበጎ አድራጎት ተቋማት አመራሮችና የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የስራ ባልደረባዎቹ ተገኝተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጋራ እያካሄደ ነው ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 26/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 19/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከምስረታው 15ኛ ዓመት በዓል ጋር በማያያዝ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
ጉባኤው በይፋ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን ተግባራትና ያመጣቸውን ስኬቶች የሚዘክረው ይህ ጉባዔ ፤ "15 ዓመታት - እምነትን በቀጣይነት፣ ሰላምን ህብረብሔራዊ ልማት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየተከናወነ ነው።
በዚሁ ታሪካዊ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የየሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ፣ሚኒስቴሮች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣የክልል ቤተ እምነት ዋና ጽሕፈት ቤቶች እና ከክልል ጉባኤዎች የተወከሉ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጥሪ ተደርጎላቸዋል እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዕለቱ የክቡር እንግዳ የኢፌዲሪ ፕረዚዳንት ክቡር አቶ ታዬ አጽቀስላሴ የእምነት አባቶች የሀገራችን አያሌ ዘመናት የአብሮነትና የመተባበር ና የሰላም ዕሴትን ምዕመናን ሲያስተምሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
የእምነት አባቶች በጨለማ ብርሀንን ፣በተከፋፈሉ ልቦች ውስጥ አንድነትን የሚያመጡ በመሆኑ መከፋፈልን እንደስኬት የሚቆጥሩ አካላትን እንዲያወግዙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ከኢትዮጵያዊነት ባህል ውጪ የሆኑ ቅጥፈት ፣ እብለትን ፣ሌብነትን ና ለሰዎች ደንታቢስነትን እንዲታረሙ ማስተማር የተቋማቱ ቀዳሚ ተግባር መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል።
የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ሙሀመድ ኢድሪስ አባል ቤተ ዕምነቱ ተቋማቱ የሀገራችንን ሰላምና አብሮነት ላይ ላለፉት አስራ አምስት አመታት በመስራት ታሪካዊ ድል ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
ተቋማቱ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስኬት ያደረጉት አስተዋፅኦ በምሳሌነት ጠቅሰዋል።በቀጣይም በትብብርና በአንድነት በመቆም በጋራ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉኅን ታጋይ ታደሰ ሁሉም ሃይማኖቶች የሚሰብኩት ሰላም በመሆኑ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑ በመታመኑ የሃይማኖት አባቶች በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች ያላቸውን ተሰሚነትን ተጠቅመው
በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እንዳይፈጠሩ በማድረግ፣ ጥያቄዎች ካሉ ደግሞ በውይይት መፍታት እንደሚቻል በማሳየት ስራዎች መስራቱን ገልጸዋል፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የጠቅላላ ጉባዔና የሥራ አመራር ቦርድ አባል ዑስታዝ ሀሰን ዓሊ ባደረጉትን ንግግር ፣አባል የሃይማኖት ተቋማቱ ከመንፈዊ አገልግሎታቸው ጎን ለጎን በጋራ ሀገራዊ የሰላም ፣ የልማት ስራ ባሻገር በሃይማኖት ተቋማትና የሃይማኖት አባቶች መካከል የእር በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረጉን ተናግረዋል።
ጉባዔው በአባል ቤተ እምነቶች መካከል ለግጭት መንስዔ የሆኑ ጉዳዮችን በውይይት በመፍታት ፣ማሕበራዊ እድገትን የሚያፋጥኑ የልማት ሥራዎችን በትብብር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በ መርሃ ግብር ላይ ጉባኤው ባለፉት 15 ዓመታት በሀገሪቱ ሰላም፣ አብሮነት እና ህብረብሔራዊ ልማት እንዲጸና ያከናወናቸው አዎንታዊ ተግባራት የሚገመገሙ ሲሆን፣ በቀጣይ አቅጣጫዎችና በ18ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ላይም ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጊቢው ውስጥ ሊያስገነባ ላሰበው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ የመኪና ማቆሚያ ግንባታ ብቁ ተጫራቾችን ማወዳደር ይፈልጋል
በመሆኑም ከስር በተያያዘው ሰነድ ላይ በዝርዝር የቀረቡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት