Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.76K photos
76 videos
20 files
1K links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ የተመራ ልዑክ ለስራ ጉዳይ ጎዴ ከተማ ገባ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 29 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 22 /1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጎዴ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ የተመራው የስራ ልዑክ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ገባ።
​
ልዑኩ በጎዴ ኡጋዝ ሚራድ ኤርፖርት ሲደርስ በሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዳዕዋ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አብዱሽኩር ሸይኽ አብደላ፣ የጎዴ ከተማ እስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ ሸይኽ ኢስማኢል ሙዓሊም እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችና የአካባቢው አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

​ልዑኩ ጎዴ ከተማ የገባው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባዔ ከቡኒያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በጎዴ ከተማና በሸበሌ ዞን ለሚገኙ አንድ መቶ ኢማሞችና አሳቲዞች የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በማስተባበር ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የስራ አቅጣጫ እና መመሪያ ለመስጠት ነው።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከቡኒያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከዚህ በፊትም በተለያዩ ከተሞች ለኢማሞችና ለኡስታዞች ተመሳሳይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
በአይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂ ለሆኑ ዜጎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ::
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 27 /1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የሆነው አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ከአል በስር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሊሰጥ ነው።

ነጻ ህክምናው በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት በከፊልና ሙሉ በሙሉ ለሙሉ የእይታ እክል ላጋጠማቸው ወገኖች የሚሰጥ ሲሆን ለህክምናው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች ከወዲሁ መጠናቀቃቸውን የአወልያ እርዳታ እና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ሰዒድ አስማረ ተናግረዋል።

የመጀመሪያው ዙር ነጻ የህክምና አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በአወሊያ ጤና ጣቢያ ከመስከረም 4 እስከ መስከረም 7 /2019 እንደሚሰጥም ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

​የህክምናው ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በአወሊያ ጤና ጣቢያ በመገኘት የነጻ ህክምና አገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ሐጅ ሰዒድ አስማረ ጥሪ አቅርበዋል።

​ነጻ የአይን ሞራ ግርዶች ህክምናው በቀጣይም በጅማ እና በወሎ አካባቢዎች እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1