ዳሸን ባንክ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በመተባበር ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 28 /1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
ዳሸን ባንክ ማህበራዊ ሀላፊነትን መሠረት በማድረግ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለ100 አቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ በተከናወነው የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ማዕድ ማጋራት የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የበጎነት ተግባራትን በማጠናከር ለማህበራዊ አብሮነት ግንባታ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል።
አቅመ ደካሞችን መመገብና መንከባከብ ኢስላማዊ እሴት መሆኑን ያስታወሱት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ዳሸን ባንክ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በመቀናጀት ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራቱ ለማህበራዊ ኃላፊነት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ያሳያል ብለዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ ዶክተር ኢብራሂም አህመድ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖችን ማዕድ ለማጋራት ጠቅላይ ምክር ቤቱን በአጋርነት ስለመረጠ ያላቸውን ምስጋናቸው ገልጸው ማዕድ ማጋራት በእስልምና አስተምህሮም ሆነ በማንኛውም በጎ ባህል ውስጥ ከፍተኛ መንፈሳዊ ዋጋ ያለው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።
አቅመ ደካሞችንና ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን መንከባከብ የአንድ ወገን ወይም የኃይማኖት ተቋም ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሰው የሞራል እና የዜግነት ግዴታ ነው ያሉት ዶክተር ኢብራሂም አህመድ ሁሉም ሰው በሚችለው አቅም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ ሠማን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የሕዝብ አጋርነቱን ለማረጋገጥ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በየዓመቱ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንደሚደግፍ አንስተዋል።
ዳሽን ባንክ በሸሪክ የወለድ አልባ መረሀ ግብሩ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በመቀናጀት ይህን መሠል የማዕድ ማጋራት ተግባር ማከናወኑ የተጠቃሚዎችን ችግር ከማቃለሉ በተጨማሪ በመረዳዳት የተጠናከረ ማህበረሰብ ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ዳሸን ባንክ በቀጣይም በጎ ተግባራት ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የተጠቀሰ ሲሆን የእርዳታው ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባልና የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ዑስታዝ ፋሪስ ጀማል እና የዳሸን ባንክ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት