Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.76K photos
76 videos
20 files
999 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማህበር 3ኛውን ዙር የክረምት ሰልጣኝ ተማሪዎቹን አስመረቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 2/2019 ዓ.ል| ረቢዕ አል ሳኒ 01/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
​የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማህበር ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፈቃድ ወስዶ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች የተሻለ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ህይወት እንዲኖራቸው እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።

ማህበሩ ላለፉት ሁለት ወራት ለሶስተኛ ዙር ያሠለጠናቸውን አንድ መቶ ሰባት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ አስመርቋል።

በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው መሠል ማህበራት ሕጋዊ ፍቃድ ሰጥቶ እንዲጠናከሩ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አካል ጉዳተኛ መሆነ ማለት አለመቻል ማለት አይደለም ያሉት ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ነጻ የቢሮ አገልግሎት ተሰጥቶች ስራዎቹን እያከናወነ የሚገኘው በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማህበር ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ዘርፍ ኅላፊ ሸይኽ ዑመር ያህያ በበኩላቸው መስማት የተሳናቸው ወገኖች ኢስላማዊና ዓለማዊ እውቀት ማግኘት እንዲችሉ የቁርዓንና የሐዲስ ትርጉሞችን ማመቻቸት እና በምልክት ቋንቋ እንዲማሩ ማስቻል ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቋማትና ማህበራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሀጅ አብዱልማሊክ ገቢ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ማሕበሩ በተቋቋመ የሶስት ዓመታት እድሜው ያስመዘገው ውጤት ለሌሎች ማህበራትም አርዓያ የሚሆን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ማሕበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሙሀመድ እንደገለጹት ማህበሩ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ለእስልምናና ለመደበኛ ትምህርት ያላቸውን የተደራሽነት ክፍተት ለመሙላት እውቀት ጥረት እያደረገ ይገኛል።

በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማህበር በዛሬው ዕለት 60 ሴቶች እና 47 ወንድ ሰልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ ዱዓቶች፣ የማሕበሩ የሥራ ኅላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
​•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1