ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ምርመራ እና ህክምና በአወልያ ጤና ጣቢያ ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 4/2019 ዓ.ል| ረቢዕ አል ሳኒ 03/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የሆነው አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ከአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በሳዑዲ ንጉሥ ሰልማን የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የአይን ሞራ ግርዶሽ ነጻ የሕክምና አገልግሎት በአወልያ መሥጠት ጀመረ።
በአወልያ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው የነጻ ህክምና ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጠቅላይ ምክር ቤት የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኸ ሐሚድ ሙሣ የአይን ህክምና አገልግሎት በነጻ እየሰጠ ለሚገኘው የሳዑዲ ዓረብያ የንጉሥ ሰልማን የሰብዓዊ እርዳታ ድረጅት አልበሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን አመስግነዋል።
አወሊያ እርዳታና ልማትድርጅት ከአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለሚሰራው የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ስራ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥም ምክትል ፕሬዝደንቱ አረጋግጠዋል።
የአልበሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጀኔራል ሴክሬታሪ የሆኑት ዶክተር አዲል አብዱልአዚዝ አል ረሹድ ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ ከ26 ዓመታት በላይ የሰበአዊ እና የጤና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ መር ሃ ግብርም በሺዎች ለሚቆጠሩ የአይን ህሙማን የምርመራና የህክምና እንዲሁም ነጻ የመድኃኒትና የመነጽር አቅርቦት ይካሄዳል ብለዋል።
የእንኳን ደህና መጣቹህ መልዕክት ያስተላለፉት የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አሰኪያጅ ሀጂ ሰዒድ እስማረ በበኩላቸው አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት በቀጣይም መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራትን በማጠናከር የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ለማቃለል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በነመርሃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ቦርድ አባልና የፕሮግራም ዳይሬክተር ኢንጂነር ናስር ሙሐመድ አልሱወይዳን፣ የአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በአወልያ ጤና ጣቢያ ለ4 ቀናት የሚቆየው ነጻ የዓይን የህክምና አገልግሎት በጂግጅጋ እና በወራቤ አካባቢዎች አንደሚቀጥል ተገልጿል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eias

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኢማሞችና ዑስታዞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 4 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 3/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ቦንጋ |
ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኢማሞችና ዑስታዞች ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና በቦንጋ ከተማ ተጀመረ።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ እና በቡኒያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀው ሲሆን በስልጠናው ላይ ከክልሉ ስድስት ዞኖች የተውጣጡ 100 ኢማሞች፣ ዱዓቶች እና ዑስታዞች ይሳተፋሉ።
ስልጠናውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ አሊ መሐመድ ዔባ በንግግር ያስጀመሩት ሲሆን በንግግራቸውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር እየሰጠ ያለው የኢማሞች፣ የዱዓቶችና የዑስታዞችን የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤታማ እንደቀጠለ ጠቅሰዋል።
የሰልጠኞችን አቅም በማጎልበት ህዝቡ የተሻለ አገልግሎት ከማድረግ አንጻር ስልጠናው ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ሸይኽ አሊ ሙሃመድ አክለው ገልጸዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ያሲን አወል አብዱ በበኩላቸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚያዘጋጃቸው ሥልጠናዎች የዑስታዞችንና የኢማሞችን አቅም ከመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።
በስልጠና ማስጀመሪያ መድረኩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የክልሉ መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1