Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.76K photos
76 videos
20 files
999 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ የተመራ የጤና ባለሙያዎች ልዑክ ጂግጂጋ ከተማ ገባ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 9/2019 ዓ.ል| ረቢዕ አል ሳኒ 08/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር ኢብራሂም አህመድ የተመራ የአል በስር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የጤና ባለሙያዎች ልዑል ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ጂግጂጋ ከተማ ገባ።

በኢትዮጵያ ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ምርመራ እና ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የጤና ባለሙያዎች ልዑክ ጂግጂጋ ከተማ ሲገባ የጂግጂጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዱሏሂ ኢብራሂም፣ የካራ ማራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሙሀመድ ሷሊሃ እና የሶማሌ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ተወካይአቶ ሁሴን ሙሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የጤና ልዑኩ ከፊታችን ሰኞ 11/01/2018 ጀምሮ ለአራት ቀን የሚቆይ ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ምርመራ እና ቀዶ ህክምና ለ400 ዜጎች ይሰጣል።

አልበሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ከአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ነጻ የአይን ሞራል ግርዶሽ ምርመራ እና ህክምና መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eias1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሀጅ አገልግሎት እና መስተንግዶ ግምገማ ማካሄድ ጀመረ::
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 9 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 8/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጅግጂጋ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የ1447/2018 የሐጅ መስተንግዶ አፈጻጸምን ለመገምገም እና በቀጣይ የ1448/2019 በጀት ዓመት የሥራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ያለመ ግምገማ በጂግጂጋ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።

በግምገማው ላይ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እና የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን መድረኩን የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ አህመድ መሀመድ መልዕክት በማስተላለፉ አስጀምረውታል።

ሸይኽ አህመድ መሀመድ በመልዕክታቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ በ1447/2018 የሀጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ያስመዘገበው ውጤት የጠቅላይ ምክር ቤቱንና የሀገርን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ በመልካም ያስጠራ መሆኑን አስታውሰዋል።

​ውጤቱ የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ጋር በቅንጅት በመስራት የመጣ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ የ2019 የሐጅ ምዝገባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በላቀ የኃላፊነት ስሜት እንዲሰሩም የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

​የጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሸይኽ ኢስሀቅ አደም በበኩላቸው የ2019 የሐጅ ጉዞ ምዝገባ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር ገልጸው ግምገማዊ ስልጠናው ከምዝገባ ቅድመ ዝግጅቶ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በሁሉም የምዝገባ ማዕከላት ለአገልግሎት ፈላጊዎች የተቀናጀና ጥራት ያለው አገልግሎት በመሰጠት እርካታ ለመፍጠር የምዝገባ ጣቢያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሸይኽ ኢስሀቅ አስረድተዋል።

ባለፈው ዓመት የታዪ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና በቀጣይም የነበሩ ክፍተቶች እንዲታረሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ የስልጠናው ተሳታዎች የገለጹ ሲሆን በዛሬው ዕለት በጂግጂጋ ከተማ የተጀመረው ግምገማዊ ስልጠና በሌሎች ከተሞች እንደሚካሄድም ተመላክቷል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1