Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለክልል እና ከተማ አስተዳደር መጅሊሶች የተሽከርካሪ ድጋፍ አደረገ ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 13/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 12/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክልልና የከተማ አስተዳደር መጅሊሶችን አቅም ለማጠናከር እና አገልግሎታቸውን ለማፋጠን ያለመ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዚሁ ዕቅዱ አካል የሆነ የዘመናዊ ተሽከርካሪ ድጋፍ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች አድርጓል።

​በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ባደረጉት ንግግር ድጋፉ በየደረጃው የሚገኙ መጅሊሶች ህዝበ ሙስሊሙን በቅንነት እንዲያገለግሉ፣ የዳዕዋና የልማት ስራዎችን እንዲያስፋፉ እንዲሁም የአስተዳደር ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት እንዲያከናውኑ ያግዛል ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለውም የተበረከቱ ተሽከርካሪዎች ወጪ ከመቆጠብ ባሻገር የአረንጓዴ አሻራ ግብን ለማሳካት የሚያስችሉ ዘመናዊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቋማዊ ቁመናውን ከፍ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ ሂጅራ ባንክ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያወጣውን ያወጣውን መስፈርት በማሟላት ለተሽከርካሪዎቹ መግዣ የሚሆን የረጅም ጊዜ የብድር ስርዓት ማመቻቸቱንም አክለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልዕቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ በበኩላቸው
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የክልል እና የከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤቶች መጅሊሶች እንዲጠናከሩ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

​የሂጅራ ባንክ ፕሬዝደንት አቶ ዳዊት ቀኖ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የህዝበ ሙስሊሙ መሪ ድርጅት በመሆኑ ከተቋሙ ጋር አብሮ መስራት መላውን ህዝበ ሙስሊም ለማገልገል ያስችላል።

ባንኩ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ በአነስተኛ የትርፍ መጠን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ተሽከርካሪዎችን ማቅረቡን ፕሬዝደንቱ አስታውሰዋል።

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲንን
ጨምሮ የዑለማእ ምክር ቤት አባላት፣ የአስፈጻሚ እና የስራ አመራር አባላት፣ የክልል መጅሊስ ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የሂጅራ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የሁለተኛ ዙር የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ግምገማዊ ስልጠና በሻሸመኔ ከተማ ነገ ይካሄዳል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 13/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 12/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የ2019/1448 የሐጅ ጉዞ አገልግሎትና መስተንግዶን ውጤታማ ለማድረግ በማሰብ እየተካሄደ ያለው ግምገማዊ ስልጠና በነገው ዕለት ለሁለተኛ ዙር በሻሸመኔ ከተማ ይቀጥላል።

በግምገማዊ ስልጠናውም ላይ የክልል መጅሊስ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎችና የምዝገባ ጣቢያዎች ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን ስልጠናው የ2018/1447 የሐጅ ጉዞ ምዝገባን ለማስጀመር ከሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መካከል አንዱ እንደሆነ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሸይኽ ኢስሀቅ አደም ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም የዚህን ዓመት የሐጅ ምዝገባ አገልግሎት ፈጣን፣ ምቹና ተደራሽ ለማድረግ ግምገማዊ ስልጠናው ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የስልጠና መረሀ ግብሩ ከተጠናቀቀና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከተጠናቀቁ በኋላ የ2019 የሐጅ ምዝገባ በቅርብ ቀናት የሚጀምር በመሆኑ ንያ ያላቸው ሁሉ አስፈላጊ ሰነዶችን አዘጋጅተው እንዲጠብቁም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1