Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.55K photos
76 videos
20 files
992 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባኤ በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 1/ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 30/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባኤ በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።

ዛሬ በተደረገው የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕረዚዳንት ሼይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ ጨምሮ ዓሊሞች የጠቅላይ ምክር ቤቱና የአዲስ አበባ መጅሊስ ሥራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕረዚዳንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በስልጠና መርሀ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የዘመናት የሕዝበ ሙስሊሙ የፍትሕ ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኝ ብቃት ያላቸውን ቃዲዎችን በውድድር እንዲሟሉ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

አዲሱን አዋጅ ታችኛው መዋቅር ድረስ በማስረፅ ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ቃዲዎች እራሳቸውን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ቴውድሮስ ምህረት በበኩላቸው የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አሰራር እንዲሻሻል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ቤቱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ መቆየቱን ተናግረዋል።

ጥናቶችን መሠረት ያደረገ የመጀመሪያ መፍትሔ የሆነው የህግ ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን ፕረዚዳንቱ ተናግረው ዳኞች በነፃነት ፣ በፍትሐዊነት ና በገለልተኝነት ሕግና አሰራርን መሠረት በማድረግ በቁርጠኝነት የሰጣቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት ሼይኽ መከተ ሙሄ በበኩላቸው የዳኝነት ተቋማት በሰዎች ንብረትና ነፃነት ላይ የሚወስኑ በመሆናቸው ዳኞች የሚሰሩባቸው ህጎች ላይ በቂ እውቀት፣ የዳበረ ክህሎት እና የተጣለባቸውን ከባድ ሀላፊነት በብቃትና በታማኝነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የፍትህ አስተዳደር ጥራትና እድገት የዳኞች ወቅታዊና ተከታታይ ስልጠና አማራጭ ሳይሆን ግዴታ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የጋራ ትብብር የሚያጠናክረው ፍኖተ ካርታ በኢስላሚክ ልማት ባንክ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኸ ሃሚድ ሙሣ
ገለጸ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት፣ 5/2019 ዓ.ል | ጁማደል አወል 4፣ 1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በኢስላማዊ ልማት ባንክ የሙስሊም ማህበረሰብ የትብብር ቻርተር/ሮድማፕ ማዕቀፍ፤ የሙስሊም ተቋማትና የአባል ድርጅቶች አበይት ተወካዮች የልምድ ልውውጥ እና በቀጣይ ስትራቴጂያዊ ውይይት መክፈቻ ስነስረዓትላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኸ ሃሚድ ሙሣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ በእስላማዊ ልማት ባንክ (IDB) ድጋፍ የሚተገበረው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የጋራ ትብብር ፍኖተ ካርታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ።
​ሸይኽ ሐሚድ አክለውም ግብረሰናይ ድርጅቶች ተቋሙን ጥላ በማድረግ ለሀገርና ለማህበረሰብ የሚጠቅሙ እሴቶችን ከፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። አሰራራቸውና ልምዳቸው ለተቋሙ ትልቅ ግብአት በመሆኑ፣ በቅርቡ በጋራ በመገናኘት ተቋሙ በልማት ላይ ያለው ሚና የላቀ የሚሆንበትን መንገድ ለመምከር ጥሪ እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል። በተጨማሪም፣ በየተሰማሩበት የማህበረሰብ ችግር ፈቺ ስራ ሁሉ
ተቋሙ ከጎናቹህ ይቆማል ብለዋል።

በኢስላማዊ ልማት ባንክ የሙስሊም ማህበረስብ የትብብር ፎኖተ ካርታ የሙስሊም ተቋማት የትብብር አባል ድርጅቶች የልምድ ልውውጥ እና ውይይት ላይ

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ሀላፊ እና በRCMC የኢትዮጵያ የግብረ ኋይል ዋና አስተባባሪ ኢንጂነር አኑዋር ሙስጠፋ እና

የኢትዮጵያ ልማት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የRCMC የኢትዮጵያ የግብረ ኋይል ምክትል አስተባባሪ
አቶ ጂደዲንሰዒድ በጋራ በመሆን የትብብር ፎኖተ ካርታ የሙስሊም ተቋማት የትብብር አባል ድርጅቶች ሂደት የወደፊት አቅጣጫን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አልዩ ሰዒድ፣ ከ28 ያላነሱ የሙስሊም ተቋማት የትብብር አባል ድርጅቶች በሩዋንዳ ኪጋሊ ከወሰዱት ተሞክሮ በመነሳት የተዘጋጀ ሪፖርት አቅርበዋል።
​በሪፖርቱም የትብብር ድርጅቶቹ የአቅም ግንባታ፣ የሩዋንዳ ሙስሊሞች ተሞክሮ፣ እንዲሁም ሥልጠናው ለተቋማዊ ግንባታና ለልምድ ልውውጥ ያለውን አስተዋጽኦ የሚዳስሱ የመወያያ ሀሳቦች ቀርበዋል።
ለቀጣይ መሰል መድረኮች አጋዥ የሚሆን ዘላቂ አደረጃጀትና የቅርብ ትስስር ለመፍጠር ስለሚረዳ፣ የጋራ ትብብሩ አሁኑኑ ሊጠናከር እንደሚገባ ከመድረኩ ተሳታፊዎች አጽንኦት ተሰጥቶበታል።
••••••••••••••••••••••••
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eias