Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.55K photos
76 videos
20 files
992 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሙስሊም የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር የህዝበ ሙስሊሙን ንቃተ ህግ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 7/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 6/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ ሙስሊም የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር የሙያ ሥነ ምግባርን ማሳደግ እና የሥራ ዕድገት አቅጣጫዎችን ማሻሻል ላይ ያተኮረ የፓነል ውይይት አካሄደ።

የውይይት መድረኩን የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ጠበቃ ሙህዲን ጀማል በንግግር የከፈቱት ሲሆን በንግግራቸውም ማኅበሩ በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ቁጥር 404 እና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኢስላማዊ ተቋማት ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 01/2015 መሠረት በየካቲት ወር 2017 ዓ.ል መቋቋሙን አስታውሰዋል።

ከማኅበሩ ዋና ዋና ዓላማዎች መካከል በሕግ እና ሕግ ነክ ጉዳዮች የሙስሊም ሕግ ባለሙያዎችን እና የአጠቃላይ የህዝበ ሙስሊሙን ሀገራዊ ጥቅም እና ፍላጎት ማስጠበቅ መሆኑን በንግግራቸው የጠቀሱት ጠበቃ ሙህዲ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ከማድረግ አንጻርም ማኅበሩ በንቃት እንደሚሳተፍ ጠቁመዋል።

የህዝበ ሙስሊሙን ንቃት ሕግ ለማሳደግ በሚረዱ የተለያዩ የሀገራችን ሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ኮንፈረንሶችን፣ ሴሚናሮችን፣ ሥልጠናዎችን እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን እያከናወነ እንደሚገኝም ሥራ አስኪያጁ አመላክተዋል።

በዉይይት መርሃ ግብሩ ላይ በሙያ ሥነ ምግባር እና በሥራ ዕድገት ዙሪያ የሚያተኩሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት እንደሚደረግባቸው እና በቀጣይም ተመሳሳይ ሕግ-ነክ ሙያዊ መድረኮች ጠናክረው እንደሚቀጥሉን ተመላክቷል።

"ኢኽሳን እንደ ሙያ ስነ ምግባር መለኪያ" በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የውይይቱ መድረክ ላይ የማኅበሩ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለ1448ቱ የአረህማን እንግዶች የጤና ምርመራ አገልግሎት ከሚሰጡ የጤና ተቋማት ጋር ውል ተፈራረመ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 9 /2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 8/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለ2019 ዓ.ል (1448 ዓ.ሂ) የሐጅ ተጓዦች የጤና ምርመራ አገልግሎት ከሚሰጡ 29 የህክምና ተቋማት ጋር ውል ተፈራረመ።

የውል ስምምነቱ የአረህማን እንግዶች ወደ ሳውዲ አረቢያ ከማቅናታቸው በፊት አስፈላጊውን የጤና ምርመራ በተቀናጀ መልኩ በጥራት ለማግኘት እንደሚያስችላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኅላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል።

ዘርፉ በዚህ ዓመት የሚያቀርበው የሀጅ አገልግሎትና መስተንግዶ "የላቀ አገልግሎት ለሑጃጆች እርካታ!" በሚል መሪ ሀሳብ ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለጹት ኅላፊው የጨረታ መስፈርቱን አሟልተው የተመረጡት 29 የህክምና ተቋማት ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለሁጃጆች እንደሚሰጡም አክለዋል።

ውል የፈረሙ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁስና ባለሙያ ያላቸው በመሆኑ የአረህማን እንግዶች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት አግኝተው የጉዞ ብቃት ማረጋገጫ የህክምና የምስክር ወረቀት እንደሚቀበሉም ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ ጨምረው አብራርተዋል።

የሀጅና ዑምራ ዘርፉ የሳዑዲ ዓረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ያመላከቱት ኃላፊው በዛሬው ዕለት ውል የተፈራረሙ የጤና ተቋማት በፈረሙት ውል መሰረት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲውጡም አደራ ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጅ ከማል ሀሩን በበኩላቸው ለሑጃጆች የሚሰጠው የጤና ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ዲጅታል በመሆኑ አገልግሎቱን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል።

​የዘንድሮውን የሐጅ ጉዞ ዝግጅት ቀደም ብሎ የጀመረው ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ከምግብ፣ ከትራንስፖርት እና ከሆቴል አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ጋር የስራ ውል በመፈራረም አገልግሎቱን ስኬታማ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1