Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.55K photos
76 videos
20 files
992 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የ2019 (1448ዓ.ሒ) የሀጅ ምዝገባ ጥቅምት 12/2019 በመላው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ በተደራጁ 33 የሀጅ ምዝገባ ማዕከላት እንደሚጀምር ተገለጸ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 12፣ 2019 ዓ.ል| ጁማዱ አል ኡላ 09 1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ "የላቀ አገልግሎት ለሐጃጅ እርካታ" በሚል መሪ ሃሳብ የሚያቀርበውን የ2019 (1448 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ የሀጅ አገልግሎት ምዝገባ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

​የዘንድሮው የሀጅ ምዝገባ ሐሙስ ጥቅምት 12/ 2019 ዓ.ል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደራጁ 33 የማስተባበሪያ ጣቢያዎች መካሄድ እንደሚጀምር በመግለጫው ተመላክቷል።

የሀጅ ምዝገባው ጥር 10/2019 ዓ.ል እንደሚጠናቀቅ እና አጠቃላይ ክፍያውም 827,000 (ስምት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ) ብር እንደሆነ ተገልጿል።

የሐጅ አገልግሎት ዋጋ ተመን የወጪ መጠንን ለመቆጣጠርና ጥራቱን ለማሻሻል የሳዑዲ ዓረቢያ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የተሻለ ስራ ስለመሰራቱም በመግለጫው ተመላክቷል።

በመግለጫው መክፈቻ ላይ ንግገር ያደረጉት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ​የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሃሚድ ሙሣ የሐጅ አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸው ባለፈው ዓመት የተገኘውን የላቀ ውጤት በዚህ ዓመትም አሻሽሎ ለማስቀጠል የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ምዝገባ መጀመሩን አብስረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በጋዜጣዊ መግለጫው ዕለት እንዳስረዱት ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ባለፈው ዓመት ባስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም ከሳዑዲ ዓረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር ከፍተኛው የክብር ማዕረግ የሆነውን የለበይቱም የአልማዝ ደረጃ ሽልማት አግኝቷል።

ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ አክለውም በዚህ ዓመትም አገልግሎትና መስተንግዶውን የሳዑዲ ሀጅ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ደረጃውን ጠብቆ እንዲፈጸም ለማድረግ በቂ የዝግጅት ስራ መሰራቱን ጠቅሰው ንያ ያላቸው ሁሉ ከወዲሁ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የሀጅ ምዝገባ ማዕከል እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ​የፕሬዝዳንት ዋና ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው ሐጅ በእስልምና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የአምልኮ ስርዓት በመሆኑ ሀጅ የማድረግ አቅሙ ያላቸው ምእመናን በመዘግየታቸው ምክንያት እድሉን እንዳያጡና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጫና እንዳይፈጥሩ በጊዜ እንዲመዘገቡ ጥሪ አድርገዋል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ጉዳዮችና የተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ የሐጅ ምዝገባ የልዩ መስተንግዶ (VIP) እና የትውልደ ኢትዮጵያ (ዲያስፖራ) የሐጅ አገልግሎትን በተመለከተ በቀጣይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን መግለጫው በተለያዩ ቋንቋዎች ይፋ ሆኗል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሞስኮ አቀኑ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 13 / 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 12/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ|

የሩሲያ ፌዴሬሽን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ አስተዳደር ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት እና ለኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ ለክቡር ደክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በሞስኮ በሚካሄደው ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በክብር እንግድነት እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ አቀርቧል።

​ፕሬዝደንቱ ጥሪ የቀረበላቸው በሩሲያ መዲና ሞስኮ በሚካሄደው ከሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን «በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያሉ መንፈሳዊ ድልድዮች ለሰላም እና ለልማት» በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንዲሳተፉ ነው።

​ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዋና ትኩረቱ ሰላም፣ ልማትና ደህንነት ሲሆን ከውይይቱ በኋላ በዓለም ዙሪያ ለሚስተዋሉ ግጭቶች የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው የሃይማኖት ተቋማት የጋራ መንፈሳዊና ስነ ምግባራዊ እሴቶች መጎልበት በሚችሉባቸው ነጥቦች ዙሪያ ቀጥተኛና ውጤታማ ውይይት በማድረግ በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ላለው ሰብአዊ ግንኙነት መጠናከር ምክንያት እንደሚሆኑም በግብዣ ደብዳቤው ላይ ተመላክቷል።

​በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከሩሲያ ፌዴሬሽን እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች የሚሳተፉ ሲሆን የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉባዔው ላይ በመገኘት ንግግር በማድረግ የሀገራቸውን መልካም ልምድና ተመክሮ ያካፍላሉ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የቀጣይ 5 ዓመታት ስልታዊ ዕቅድ ዝግጅት ማስጀመሪያ ምክክር አደረገ።
​••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 14/2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ|

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የሆነው አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የአምስት ዓመታት ስልታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት የሚያስችለውን ውይይት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችናየዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት አስጀመረ።

ተግባራዊ የሚያደርገው የሚተገብረውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ይፋ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አዘጋጀ።

ስልታዊ ዕቅዱ ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን የልማት፣ የበጎ አድራጎት እና የትምህርት አገልግሎቶች ጥራት ይበልጥ ውጤታማ እና ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ በውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል።

​የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ ተቋማት ያለ ስልታዊ ዕቅድ የሚያደርጉት የስራ እንቅስቃሴ ለሀብት ብክነትና ለውጤት አልባነት የሚዳረግ መሆኑን ውይይቱን ባስጀመሩበት ንግግራቸው ገልጸዋል።

አወልያ እያከናወናቸው ያሉት የልማትና የሰብዓዊ ዕርዳታ እና የትምህርት ሥራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃ እያደረጉ እንደሚገኙ አስታውሰው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለስልታዊ ዕቅድ ዝግጅቱና ለትግበራው ተባባሪ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

​የአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጀማል መሐመድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለው አወልያ የጠቅላይ ምክር ቤቱን እና የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸው ለድርጅቱ ርዕይ መሳካት ባለድርሻ እና አጋር የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

​የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ በዚሁ መድረክ እንደተናገሩት የሚዘጋጀው ስልታዊ ዕቅድ ጥራት በአማካሪው ብቃት ብቻ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ የመረጃ ምንጮች ትክክለኛ፣ ግልጽና ጥራት ያለው መረጃ መስጠት አለባቸው።

የእርዳታና ልማት ድርጅቱ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በሥሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በተቀናጀ አሰራር በመምራት በአገር ደረጃ ውጤታማ ማድረግ መቻሉንም ሀጅ ሰዒድ አስማረ አክለዋል።

​ስልታዊ ዕቅዱን የማዘጋጀት ኃላፊነት የተረከበው የሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌዲዮን ገሞራ በዕቅድ ዝግጅት ሂደቱ ላይ ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የዕቅድ ዝግጅቱ ቡድን መሪ የሆኑት ዶክተር ብርሃኑ ነገሪ እና ዶክተር ጀሚላ ሁሴን ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ሰነድ አቅርበው ተሳታፊው ሰፊ ውይይት አድርጎባቸዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1