የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከተለያዩ ባንኮች ጋር የስራ ውል ስምምነት ተፈራረመ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 16/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ የ2019 ዓል.(1448 ዓ.ሒ) የሐጅ ጉዞ ምዝገባና ክፍያን በተሻለ የአገልግሎት ጥራት ለማከናወን የሚያስችለውን መጠነነሰፊ የዝግጅት ስራ እያከናወነ ይገኛል።
ዘርፉ በዛሬው ዕለትም ከተመረጡ ባንኮች ጋር በአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ዙሪያ ውይይት ካደረገ በኋላ የሁለትዮሽ ውል ስምምነት ተፈራርሟል።
ውይይቱ የአረህማን እንግዶች የሚፈጽሙትን ክፍያ ዘመናዊ፣ ግልጽና ፈጣን ለማድረግ ያለመ ነው።
በስምምነት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን የሑጃጆች ምዝገባ "የላቀ አገልግሎት ለሑጃጆች እርካታ" በሚል መሪ ሀሳብ መጀመሩን አስታውሰው ባንኮቹ በተፈራረሙት ውል ስምምነት መሠረት ለአረህማን እንግዶች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሷሊህ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ከሳውዲ አረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር የተገኘው የዳይመንድ ደረጃ ሽልማት የባንኮችም ጭምር መሆኑን ጠቅሰው የዘንድሮው የሐጅ አገልግሎት በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
ንያ ያላቸው አማኞች የሳዑዲ አረቢያ ሀጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የመመዝገቢያ ጊዜ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ወዳዘጋጃቸው ዘመናዊ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት ምዝገባቸውን ከወዲሁ እንዲያከናውኑ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ ጥሪ አቅርበዋል።
ከተጀመረ ቀናት ያስቆጠረው የዚህ ዓመት የሐጅ ጉዞ ምዝገባ እስከ ጥር 10 /2019 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ባንኮች በገቡት ውል መሰረት ለአረህማን እንግዶች በሁሉም የምዝገባ ማዕከላት ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
የኢትዮጵያና የሩሲያ ኢስላማዊ ተቋማት ሃይማኖታዊ ትብብራቸውንና የጋራ ልማታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አካሄዱ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 16/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሞስኮ|
በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከርና በኢስላማዊ ተቋማት ደረጃ ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ውይይት ተካሄደ።
በሁለትዮሽ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና የሩሲያ ሙስሊሞች መንፈሳዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሙፍቲ ዐይነዲን ራዊ ተሳትፈዋል።
የዚህ ታሪካዊ ውይይት ዋና ዓላማ በሁለቱ አገራት ኢስላማዊ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር፣ የሰላም ግንባታ፣ የሰብአዊ እርዳታና የጋራ ልማት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሆነ ተገልጿል።
በውይይቱ ወቅት በሁለቱ አገራት ኢስላማዊ ተቋማት መካከል ያለውን የልምድ ልውውጥ ማሳደግ፣ የዘካ ፈንድ አስተዳደርን ማዘመን፣ በሰብአዊ እርዳታ ፕሮጀክቶች ላይ በትብብር መስራት፣ በሃይማኖቶች መካከል ያሉትን የጋራ እሴቶች ማጠናከር የሚያስችሉ ነጥቦች በስፋት ተነስተዋል።
በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የሰላም ጥረቶችን በጋራ መደገፍ በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ሃይማኖታዊ ተቋማት መካከል ያለውን ወዳጅነት የሚያጠናክር ከመሆኑም ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከናወኑ የሰላምና የልማት ስራዎች አዎንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
ይህ ዓለም አቀፍ ውይይት በነገው ዕለትም የሚጠናቀቅ ሲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ለማወቅ ችለናል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልኡክ በቱርክ በተካሄደው 3ኛው ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ጉባኤ ላይ ተሳተፈ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 16/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ኢስታንቡል |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአስተዳደር ጉዳዮች እና የተቋማት ልህቀት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱሏሂ የተመራው ልኡክ በቱርክ ኢስታንቡል በተካሄደው 3ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተሳተፈ።
“በትምህርት ዘላቂነት እና ተቋማዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደ ሲሆን ይህን ዓለም አቀፉ ጉባኤ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ ዚያድ አሊዩ በቁርአን ከፍተውታል።
በጉባኤው ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ የሚዳስስ ጥናታዊ ጽሁፍ በዘርፉ ተመራማሪዎች የቀረበ ሲሆን ጥናታዊ ጽሁፎችን መነሻ በማድረግ አርቴፊሻል ኢንቴለጀንስ በትምህርት ጥራት፣ በተቋማዊ ለውጥ እና በዲጂታላይዜሽን ሂደት ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ በሚመለከት ሰፊ የልምድ እና የተሞክሮ ልውውጥ ተደርጓል።
ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ከተቋማዊ እና አስተዳደራዊ ቅልጥፍና ባሻገር ለሰብአዊነ አገልግሎት፣ ለማህበራዊ ሽግግር እንዲሁም የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት ለማስፈን ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር በጉባኤው ላይ በስፋት ተነስቷል።
የመረጃ ፍሰትን ለማቀላጠፍ፣ ትምህርታዊና ማህበራዊ ውጤቶችን ለመከታተል እንዲሁም የማህበረሰብ ልማቶችን ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ ጠንካራ አሰራሮችን ለመገንባት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚና የጎላ መሆኑ በስፋት ተዳሷል።
የዲጂታል አሰራር ስርዓትን ለመገንባት ዓለም አቀፍ አጋርነቶች፣ ሙያዊ ትብብሮች እና የልምድ ልውውጦች ወሳኝ መሆናቸው የተመላከቱበት ጉባኤው ሂደቱን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመምራት ዓለም አቀፍ ትስስር ለሥነ ምግባራዊ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት በይፋ በመመስረት ተጠናቋል።
በኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልኡክ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት ለጋሽ ተቋማትና የድርጅት መሪዎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይቶችን አድርጓል።
ልኡኩ በቅርቡ ከአጋር አካላት ጋር የጋራ የትብብር ስምምነቶችን ይፈራረማል ተብሎም ይጠበቃል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••