Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.54K photos
76 videos
20 files
991 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የክቡር ዶክተር  ሼይኽ  ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ  የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ክቡር አቶ ሙሳ አደምን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 23/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል  አወል  22/1448 ዓ.ሒ

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                    
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
​አዲስ  አበባ |

የኢትዮጵያ  እስልምና  ጉዳዮች  ጠቅላይ  ምክር ቤት  ፕረዚዳንት  የክቡር ዶክተር  ሼይኽ  ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ  የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ክቡር አቶ ሙሳ አደምን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ክቡር   ሚኒስትሩ  ከጠቅላይ ምክር ቤቱ መሪዎች እና የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ እና ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶክተር  ሼይኽ  ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሙስሊሙን አንድነት እና ሀገራዊ ሰላምን ለማጠናከር ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ  ተናግረዋል።
በቀጣይም ጠቅላይ ምክር ቤቱ   ከሚኒስቴር   መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ በሆኑ የሰላም ና የልማት ሥራዎች ላይ   ተቀናጅቶ  እንደሚሰራም ለክቡር  ሚኒስትሩ አረጋግጠውላቸዋል።

የኢፌዲሪ   የሰላም ሚኒስትር  ሚኒስትር  ክቡር  ሙሳ አደም  በበኩላቸው  ለችግሮች መፍቻ የሚኾን ባሕል እና ልምድ ያላት ኢትዮጵያ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት ለችግር መዳረግ የለባቸውም ብለዋል።
ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት ለችግር እንዳይዳረጉ የሃይማኖት ተቋማት ሚና የላቀ በመኾኑ ለሰላም ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ጠይቀዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተደረገው ትውውቅ እና ውይይት ላይ  የጠቅላይ  ምክር ቤቱ   ምክትል  ፕረዚዳንቶች  ፣የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር  ከይረዲን ተዘራ  ፣
የኢትዮጵያ   ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ታጋይና  የሚኒስቴር  መስሪያ ቤት  ከፍተኜ  የስራ  ኅላፊዎች  ተሳታፊ  ሆነዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1