ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
✔
135K subscribers
6.27K photos
119 videos
6 files
1.09K links
Journalist-at-large
Download Telegram
የአሜሪካንን የ Midterm ምርጫን ከንጋት እስከ አሁን እኩለ ለሊት ድረስ በመላው ግዛት እየተከታተልን ዜናዎችን እየሰራን እንገኛለን። በጋዜጠኝነት ሙያዬ የሌላ ሀገር ምርጫ ስዘግብ ይሄ የመጀመርያዬ ባይሆንም ለአሜሪካ ምርጫ አዲስ ነኝ።

አንድ ነገር አስገረመኝ: የአሜሪካ የምርጫም ይሁን የፖለቲካ ስርዐት ከችግር የፀዳ ባይሆንም የአሜሪካ ህዝብ እጅግ ብልህ፣ ነፃነቱን እና ሀገሩን የሚወድ እና ቃል የገባውን የማይፈፅም ፖለቲከኛ አሽቀንጥሮ የሚጥል ጀግና ህዝብ ነው። እኛስ ነፃ ምርጫ ኖሮን እዚህ ደረጃ ላይ መቼ እንደርስ ይሆን?

America, you continue to surpise me!

Photos: Amjambo Africa

@@EliasMeseret
❤392👍137😢49😁32🙏10🕊7🤔4😱2
ትናንት ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት እስካሁን ብቻ የ34 ምዕመናን አስከሬን መገኘቱ ተሰምቷል፣ ይህ እየሆነ ያለው እዛው አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ከ45 የሚበልጡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ላይ አሰቃቂ ግድያ ከተፈፀመ  ከ11 ቀን በኋላ ነው።

ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም ትንፍሽ የማትሉ የመንግስት ሚድያዎች ውስጥ የምትሰሩ ጋዜጠኞች ምን ይሰማችሁ ይሆን? ህዝብን ወክላችሁ የመንግስት ወንበር ላይ የተቀመጣችሁ ባለስልጣናትስ? ከሁሉም በላይ ሀገሪቱን እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትርስ?

አንዳንዱ 'ለምን?' ብሎ ሲጮህ የነበረ ድርጊቱ ተደጋግሞ ሲፈፀም ሰልችቶት ሊተው ይችላል፣ ይህ ሁሉ ጉድ የሚፈፀምባቸው በህይወት የተረፉ ዜጎች ግን ምን እየተሰማቸው ይሆን? በቁማቸው ሞታቸውን እየተጠባበቁ?

የመንግስት ዋና ስራ ግን ምንድን ነው?

@EliasMeseret
😢862🙏89❤77👍23🤔11😱2
X/Twitter ላይ ይህን መልዕክት ወስዶ በማስተጋባት ቢያንስ ድምፅ እንሁናቸው

ALERT: The violence in Ethiopia’s Arsi Zone is escalating. 34 more Christians bodies discovered yesterday in Robe Woreda just 11 days after the Shirka massacre of 45+ believers. Ongoing silence enables ongoing atrocities.

@StateDept @USCIRF @HouseForeign
@HouseForeignGOP @SenateForeign @SecRubio @USEmbassyAddis @RepGregoryMeeks @BrianMast @SenatorRisch @USAmbUN @VOLKER_TURK @EUinEthiopia @hrw @amnesty @ADFIntl

- Impose Global Magnitsky sanctions
- Demand accountability & protection for target communities

#ProtectArsiChristians #EthiopiaHumanRights
😢533🙏238👍82❤64😁11🤔11
ጠ/ሚር አብይ እንደ ፕሬዝደንት ትራምፕ!?

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፉት ሁለት አመታት አብዛኛው ህዝብ በኑሮ ውድነት በተጨነቀበት ወቅት ትኩረታቸውን ዋይት ሀውስን በወርቅ ማንቆጥቆጥ፣ በግብዣ አዳራሽ እና በሚያንፀባርቅ ፑል ግንባታ እና ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው "የካቢኔ ፕሮጀክቶች" ላይ አድርገው ነበር። በዚህ ምክንያት በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ አሜሪካውያን በድምፃቸው የሪፐብሊካን ፓርቲን በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥተዋል።

በኢትዮጵያም በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የሚካሄዱት ደም አፋሳሽ ግጭቶች በየሳምንቱ የብዙ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እያጠፉ ባሉበት እና የኑሮ ውድነቱ ህዝቡን ክፉኛ ጎዳበት በአሁኑ ወቅት የመንግስት ዋና ትኩረት የኮሪደር ልማት፣ የከተማ ማስዋብ፣ የቤተ-መንግስት ፕሮጀክቶች እና የከባድ መሳሪያዎች ግዢ ላይ ሆኗል።

በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ዋና ልዩነት የመፍትሔ መንገዱ ላይ ነው። አሜሪካ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ስላላት ህዝቡ በምርጫ የፖሊሲ ስህተቶችን መቅጣት እና ለውጥ ማምጣት ችሏል። በኢትዮጵያ ግን ዜጎች መሰረታዊ ችግሮቻቸው ተረስተው በመንግስት ፕሮጀክቶች ጥላ ስር እንዲኖሩ ቢገደዱም ይህን አሰራር የሚቀይሩበት ወይም ድምፃቸውን በዲሞክራሲያዊ መልኩ ሰጥተው ነገሮችን መቀየር ባለመቻላቸው ችግራቸውን ተሸክመው ይኖራሉ። 

ዜጎች የሀገር ውበት እና ልማት አይጠሉም። ነገር ግን የህይወት ዋስትና፣ ሰላም እና የዕለት ተዕለት የኑሮ እድገት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አገራዊ ጉዳዮች ናቸው። ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሰረታዊ እና አስቸኳይ የህይወት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ይፈልጋል።

@EliasMeseret
❤609👍282🙏64😢35😁19🤔1
የኢትዮጵያ ቡና ተወዳጅ በሆነበት እና በየዕለቱ እየተፈላ በብዛት በሚሸጥበት የፖርትላንድ፣ ሜይን Coffee by Design አዳራሽ/መጋዘን ውስጥ ከሀገር ቤት እስከ አሜሪካ የነበረንን ጉዞ አንስተን ከበርካታ ሰዎች ጋር ተወያየን፣ መልካም ግዜ ነበር።

What a powerful time of reflection!

@EliasMeseret
❤236👍96🙏15😁5😱4🤔1
ከሰሞኑ መሠረት ሚድያ አርሲ ውስጥ እየተፈፀሙ ባሉ ግድያዎች ዙርያ የሰራቸው ዘገባዎች ለአለም አቀፍ ሚድያዎች ጭምር ምንጭ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፣ ድርጊቱን የመንግስት ሚድያዎች እንዳላየ ያለፉት ቢሆንም ክስተቱ የነፃ ሚድያዎች አስፈላጊነትን አጉልቶ ያሳያል።

የመሠረት ሚድያ ባልደረቦች የሚያስመሰግን ስራ እየሰሩ ነው፣ በርቱ እንበላቸው።

ትዊተር/ኤክስ ላይ ለህዝብ በማጋራት የተሳተፍንባቸው መልዕክቶችም ውጤት አሳይተዋል። መልዕክቱን ለበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት እና ግለሰቦች ጋር ማድረስ የቻልን ሲሆን አሁን ለሚድያ ፍጆታ የማይውል ነገር ግን በኮሚቴ ደረጃ የህግ አውጪ እና አስፈፃሚ አካላት ሊያነጋግሩን ጥያቄ አቅርበው እየሄድንበት ነው። ሳንጨምር እና ሳንቀንስ ከተጎጂ አካላት የደረሰንን መረጃ መሠረት አርገን የህዝብን ሀቅ እናስረዳለን።

The world is watching!

@EliasMeseret
❤920🙏421👍138😁28🤔9😱2
የቡጢ፣ የቲክቶክ፣ የቁንጅና ወዘተ. ውድድሮችና ደመቅ ያሉ የገንዘብ ወይም የዓይነት ሽልማቶች እየገነኑ ሲመጡ በአንድ ወቅት እንደ አገር ጎላ ያለ ፋይዳ የነበራቸው፣ ቢቀጥሉ ኖሮ ለብዙ ታዳጊዎች አርአያዎች መሆን የሚችሉ ሰዎች የሚደምቁበት እንዲሁም የሙያተኞችን ተስፋ ሊያለመልሙ ይችሉ የነበሩ የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሞች ትዝ አሉኝ። አንዱ የሚከተለው ነው።

በአገር አቀፍ ደረጃ ለአገር ባበረከቱት አስተዋጽዖ 5 ሰዎች ከፍተኛ እውቅናና ሽልማት እንዲያገኙ የተደረገበት ጊዜ ነበር። ይህን ከሰማን ከአስር ዓመት በላይ ስላስቆጠረ ሁለቱን ተሸላሚዎች ዘንግቻቸዋለሁ። ከሶስቱ፦

የመጀመሪያው እና ትልቅ እውቅና ያገኙት ዶ/ር አብርሐም የሚባሉ በራስ ደስታ ሆስፒታል ስፔሻሊስት ሐኪም የነበሩ ናቸው። የሽልማቱ ምክንያት ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ጨምሮ በቁጥር በጣም በርካታ ህሙማንን ከስራ ሰዓት ውጪ ያለማንም አስገዳጅነት በግል ፈቃደኝነት ለረዥም ጊዜ በነፃ የሕክምና አገልግሎት መስጠታቸው፤

ሁለተኛዋ ስሟን የዘነጋኋት በሙያዋ ነርስ የነበረች ናት። ይህቺ ነርስ ተሸላሚ የነበረችው በራሷ ፈቃደኝነት በራሷ ወጪ በአገሪቱ በሚገኙ በርካታ የጸበል ሥፍራዎች 'ደከመኝ ሰለቸኝ' ሳትል እየተዘዋወረች የጸረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒት ያቋረጡ ሰዎችን ጸበልም እየተጠመቁ መድኃኒታቸውንም እንዲወስዱ ለረዥም ጊዜ ስታስተምር (ስትወተውት) የቆየች በመሆኗ፤

ሦስተኛው የመቄዶንያው ቢንያም በለጠ ነው። በተለይ በተለይ የአዕምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት እያነሳ ሕክምና እንዲያገኙ በማድረጉ፤

ነበር።

እንደዚህ ያሉ የእውቅና እና የሽልማት (ትርጉም ያለው እና ሕይወትን የሚለውጥ) ፕሮግራሞች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች (ለምሳሌ ጤና፣ ትምህርት፣ በጎ አድራጎት...) በአገር አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ታግዘው መከናወን አለባቸው። ተጽዕኖአቸውን በበጎ መስመር በብዙ አቅጣጫ መመንዘር የሚቻል በመሆኑ ብናስብበት መልካም ነው።

ልጆቻችንን አርአያ አናሳጣቸው!

Via Hawlet Ahmed

@EliasMeseret
❤962👍291🙏72🤔11😢9😁2
ልክ የዛሬ አንድ ወር ገደማ ይህን መረጃ አጋርቼ ነበር። ታድያ በወቅቱ አንድ የመንግስት ሹም "ፍፁም ውሸት ነው፣ አንድም የካቢኔ አባል በአምባሳደርነት አይሾምም፣ እንደውም ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለው በውስጥ መልዕክት ልከው ነበር። ዛሬ ግን ይፋ የተደረገው እውነታውን አረጋግጧል ⤵️

"ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሙስና፣ በሌብነት እና የህዝብን ሀብት በመበዝበዝ የተደረሰባቸው የካቢኔ አባላት አሉ ብለዋል... ይሁንና እነዚህኑ ግለሰቦች መልሶ አምባሳደር እና ዲፕሎማት አድርጎ መሾም ምን ማለት ይሆን?

አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን በርካታ ከስልጣን ተነሺዎች በዲፕሎማትነት ወደ ውጪ እንደሚላኩ መረጃዎች ደርሰውኛል፣ አንደኛውማ 'ቻይና ልመደብ ስለሆነ እዛው እንቀጥለዋለን' በማለት ለሀገር ውስጥ እና ለቻይና ባለሀብቶች መናገር ጀምረዋል።

ሌባ ቢሆኑም ዲፕሎማት ተደርገው ቢላኩ ብዙም ብር ስለሌለው አይሰርቁም በሚል ስሌት ይሆን? ሌባ ለአመሉ እንዲሉ መስረቅ የለመደ የኤምባሲዎችን ጣርያ ነቅሎ ሊሸጥ ይችላል።

ከሁሉም በላይ ግን ዲፕሎማትነትን እና ዲፕሎማሲያችንን የሰረቀ የሚላክበት፣ የሚቀጣበት ተደርጎ የሚወሰድበት አግባብ ልክ አይደለም፣ ሀገራቸውን በቅንነት ለሚያገለግሉ ዲፕሎማቶችም fair አይደለም። የሰረቀን ክስ መስርቶ መፋረድ እንጂ በየኤምባሲው ማጨቅ መፍትሄ አይሆንም።"

@EliasMeseret
❤345👍190😁58😢25🤔9🙏9😱3
ባለፈው ወር ታጣዊዎች ዮርዳኖስ (Jordan) ውስጥ በሚገኝ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ፈፅመው ዘጠኝ ክርስቲያኖችን ገድለው 34 ሰዎችን አቁስለው ነበር። ይህን ተከትሎ ሀገሪቱ የሀዘን ቀን ያወጀች ሲሆን ቡድኑን ይደግፋሉ በተባሉ ሀይሎች ላይም የአየር ጥቃት ፈፅማ ነበር። ዛሬ ደግሞ ጥቃቱን ፈፅመዋል ተብሎ የተፈረደባቸው 3 ሰዎች የሞት ፍርድ እንዳገኙ አለም አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡ ነው።

እኛ ጋርስ?

ጭራሽ "ይህ ለምን ይፈፀማል?" ብሎ ጥያቄ የሚያነሳ "አሸባሪ!" ተብሎ የሚፈረጅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።

@EliasMeseret
❤732😢398🙏116👍86😁22🤔11
ይህ ወንድማችን በርካታ ማስታወቂያዎችን እየሰራ ነው፣ አንድ ሰው በቅርብ እንዳጫወተኝ ከታች ተነስቶ በቅርቡ ሰርግ ላይ በተለቀቀ አንድ ቪድዮ ምክንያት ተወዳጅ ሆኗል፣ መልካም ነው።

ከተሰሩት ማስታዊቂያዎች መሀል ግን ይህ የካናዳ እና የውጭ ጉዞ ማማከር... ወዘተ የሚል እንዲሁም ማስታወቂያው ላይ "በኢትዮጵያ ብቸኛው ከካናዳው IRCC ፈቃድ ያለው" የሚል ይገኝበታል። ይህ አሳሳች የሆነ እንዲሁም ብዙ ህዝብ እንዲጭበረበር ምክንያት ሊሆን የሚችል ጉዳይ ነው።

በኢትዮጵያ ቼክ በኩል የካናዳ ኤምባሲን ደጋግመን ስንጠይቅ እንደነገረን እንዲህ አይነት የማጭበርበርያ ስልቶች እንጂ የካናዳ መንግስትም ሆነ ኤምባሲው ከማንም የሀገር ውስጥ ኤጀንት ጋር ስራ አይሰራም፣ ፈቃድም አይሰጥም።

ካናዳ የሰው ሀይል ሲያስፈልጋት በመንግስት ተቋሞቿ እና አብራቸው በምትሰራቸው አለም አቀፍ ኤጀንሲዎች በኩል እንጂ በደላሎች ወይም በቲክቶክ እና ቴሌግራም በሚያስተዋውቁ ግለሰቦች እንዳልሆነ የካናዳ ኤምባሲ በአንድ ወቅት ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቆ ነበር። የካናዳ ፍቃድ ያላቸውን ወኪሎች በተመለከተ የበለጠ ለመረዳት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይከተሉ እና ራስዎን ከአላስፈላጊ ወጪ ይጠብቁ:

https://www.canada.ca/en/immigration-refugees-citizenship/services/immigration-citizenship-representative/learn-about-representatives.html

ማስታወቂያውን የሰራው ወንድማችንን የምታውቁም ቪድዮው የለፍቶ አዳሪ ህዝብን ገንዘብ አስበልቶ እንደ ፊንቴክ አስተዋዋቂ አርቲስቶች ችግር ውስጥ እንዳይገባ ጠቁሙት።

@EliasMeseret
❤686👍385🙏77😁24😱7🤔3🕊2
በመጨረሻም በትዊተር (X) ያረግነው ትብብር ውጤት አሳይቷል፣ ይዘገይ ይሆናል እንጂ የህዝብ ሀቅ ቀስ እያለ መውጣቱ አይቀርም።

በቅርቡም ሁለት አለም አቀፍ ተቋማት በዚህ ዙርያ ስብሰባ ይቀመጣሉ፣ አብረን እንከታተላለን።

https://www.meseretmedia.org/p/620
🙏731❤237👍105😁36🕊7😢6