Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
673 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
Say something engineer's about it.
👉@engineersWorks
➡Hydraulics and water supply Lecture @engineer03
.
👉ለዛሬ ደግሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች አዘጋጅተናል 👇
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት
ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ
ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን
አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው
እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3)
አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት
(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ
(በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።
፟
➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን✌
.
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
t.me/engineer03
👆👆👆👆👆
⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
#በኮንስትራክሽን_ውል_ጉዳይ_የክፍያ_ምስክር_ወረቀት(#PAYMENT_CERTIFICATE )
============== ============= ==================== ===================


የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ በአሰሪው በሚመደብ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና በተቋራጩ ተረጋግጦና ተማምነውበት የሚፈረም ሲሆን ለተቋራጩ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠንም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡


(የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪ አባሪ ተደርጐ ይያያዛል፡፡)
ቴክ ኦፍ ሽት የአሰሪው አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና የተቋራጩ መሀንዲስ በግንባታ ቦታ በአካል የሳይት ቪዚት በማካሄድ የተሰራውን ስራ መጠን እና አይነት ከለቀሙ በኋላ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ከተመለከተው የእያንዳንዱ ስራ አይተም ዩኒት ሬት/ነጠላ ዋጋ አንጻር በዝርዝር በተናጠል በዋጋ የሚያስቀምጡበት የተሰራውን ስራ መጠን እና የገንዘብ መጠን ገላጭ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡
ግራንድ ሳመሪ ደግሞ በዋናነት የግንባታወችን ዝርዝር/ብሎክ በማስቀመጥ የውሉን ዋጋ፣አስቀድሞ የተከናወነ ስራ መጠን፣አሁን የተከናወነ ስራ መጠን እና አጠቃላይ በተቋራጩ የተሰራውን የግንባታ ስራ መጠን ይጠቅሳል፡፡


የክፍያ ሰርተፍኬት በአብዛኛው በአንድ ገጽ ተጠቃሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በይዘት ደረጃ ግን ብዙ መረጃወችን አምቆ የያዘ ሰነድ ነው፡፡
የክፍያ ሰርተፍኬት በተለይ ክፍያው የመጀመሪያ ዙር፣ሁለተኛ ዙር እያለ በሚታወቅበት መንገድ የሚዘጋጅ ሲሆን የመጨረሻ ዙር ክፍያ የሚባልም አለው፡፡
የመጀመሪያ ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በአብዛኛው ከቅድሚያ ክፍያ በኋላ ሲሆን ክፍያውም ለተሰራ ስራ የሚፈጸም ነው፡፡


የመጨረሻ ዙር ክፍያ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ጊዜአዊ ርክክብ/provisional acceptance/ ከተከናወነ በኋላ በህግ ከተቀመጡ ተቀናሾች በስተቀር ቀሪውን የስራ ክፍያ ጠቅልሎ አካቶ ወዲያውኑ በግንባታ ውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡
የክፍያ ሰርተፍኬት የፕሮጀክቱን ስም፣ቦታ፣አሰሪውን፣ተቋራጩን፣አማካሪውን ይጠቅሳል፡፡ ዋናውን የውል ገንዘብ መጠን፣ተቀጽላ ስራዎችን፣ቫሬሽንን እና የተከናወነውን የስራ መጠን ያመለክታል፡፡ውሉ የተደረገበትን ጊዜ እና ኮመንስመንት ዴት ይጠቁማል፡፡በተጨማሪም የቅድሚያ ክፍያ መጠን እና አድቫንስ ሪፔይ ያመለክታል፡፡በዚህም አስቀድሞ የነበሩ የክፍያ ቁጥሮችን ጭምር ይጠቁማል፡፡ እንደዚሁም የሪቴንሽን መጠን እና የቅጣት መረጃንም የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ መረጃ በያዘ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ አሰሪው/ተቆጣጣሪው/አማካሪው እና ተቋራጩ የሚፈራረሙበት ይሆናል፡፡


ስለዚህ የክፍያ ሰርተፍኬት ጸደቀ ማለት በሰርተፍኬቱ ላይ የተመለከተው ስራ ስለመሰራቱ እና ዋጋውንም ጭምር አሰሪውና ተቋራጩ አምነውበታል ማለት ነው፡፡


((((እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የአሰሪው ዋና ግዴታ ለተቋራጩ በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ነው፡፡))))

የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ክሎስ 28.5 ላይ ስለኮንስትራክሽን ስራዎች ክፍያ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ይዘረዝራል፡፡


በዚህ ረገድ በተለይ ክሎስ 28.5(a) ላይ የተቀመጠው እንደሚያስገነዝበው በኮንስትራክሽን ስራዎች ጉዳይ ክፍያ የሚፈጸመው በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠና የጸደቀ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ እንዲቀርብ በማድረግ መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
እንግዲህ የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብ በመጀመሪያ ተቋራጩ እንደመሆኑ አማካሪው/ተቆጣጣሪው መሀንዲስ የሳይት ቪዚት በማካሄድ የክፍያ ጥያቄውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ የክፍያ ሰርተፍኬቱን፣ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪውን ጨምሮ የሚያጸድቅና አረጋግጦ የሚፈርምበት እና በማህተምም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡


አማካሪው/ተቆጣጣሪው በተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማረጋገጡን ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባው በዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(d) ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡


እንደዚሁም አሰሪው ደግሞ በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያውን መፈጸም እንደሚገባው በአስገዳጅ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡


እንግዲህ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በእጁ ይዞ እያለ እና አሰሪውም ደርሶት እያለ ሳይከፍለው ያዘገየበት እንደሆነ በግንባታ ውሉ እና የውል አካል በሚያደርጉት ጀኔራል ኮንዲሽን በተመለከተው አግባብ ተቋራጩ ኪሳራ ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል ዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(g) በግልጽ እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡


ፒፒኤ 2011 ክሎስ 59 እንደዚሁ የኮንስትራክሽን ጉዳይ የስራ ክፍያ የሚፈጸመው በክፍያ ሰርተፍኬት አማካይነት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡


በአጠቃላይ ከላይ የተመለከተው የክፍያ ሰርተፍኬት ባህሪ እና የህጉ ድንጋጌ የሚያስገነዝበው ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በአማካሪው/ተቆጣጣሪው እስከጸደቀለት ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ክፍያ ሊፈጸምለት እንደሚገባ ነው፡፡


ጉባዔ አሰፋ (ጠበቃና የህግ አማካሪ,
https://t.me/engineer03
#የቅድሚያ_ክፍያ (#ADVANCE_PAYMENT)


በዚህ ፅሁፍ ቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው? አላማውስ? አቅራቢውና ተጠቃሚውስ ማን ነው? ያለባቸው ግዴታስ ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች እንዳስሳለን፡፡


የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና በኮንስትራክሽን ዉሎች ከሚዘወተሩ የዋስትና አይነቶች አንዱና የተለመደዉ ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ የቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው እሚለውን እንይ፡፡ በመንግስት ግዢ አዋጁ አንቀፅ 48 ላይ በመንግስት ገዥ አፈፃፀም ጊዚ አቅራቢዎች ከክፍያው ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቅርቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደሚስጥ ይገልፃል፡፡


ይህ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ከጠቅላላው የውሉ ዋጋ ሰላሳ ፐርሰንት (30%) መበለጥ እንደለለበትና ሊከፈል የሚችለው የገንዘብ መጠንም በጨረታ መመሪያው ላይ መገለፅ እንደሚገባው የመንግስት ግዢ መመሪያ አንቀፅ 16.26.1 ያስገድዳል፡፡


ተዋዋይ ተቋራጮችም ይህንን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት ከማመለከቻ ጋር የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ያልተገደበ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሐገር ውስጥ ተቋራጮች ሲሆኑ በሁኔታዎች የተገደበ ዋስትና ከኢንሹራንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሚያቀርቡትም ዋስትና ከሚጠይቁት የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዋስትናው ምትክ ከመሰረታቸውና ከሚከታተላቸው ባለሰልጣን መስሪያ ቤት የሚያቀርቡት ደብዳቤ እንደ ዋስትና ተቀባይነት ይኖረዋል ሲል የመመሪያው አንቀፅ 16.20.5(ሐ) ይደነግጋል፡፡


ከዚህም በፊት ግን ተቋራጩ በግዢ ስነ-ስርዓቱ ያሸነፈውን ዉል መፈረምና የውል ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ዋስትና ያቀረበ መሆን አለበት (አዋጅ ቁ.649/2001፣ አንቀፅ 48/2/)፡፡


በአዋጁ አንቀፅ 78(3) መሰረት የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ አዋጁንና መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው መደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ [The Public Procurement Agency Standard Bidding Document: General Condition of Contracts: PPA-2011] ክሎስ 60(1) ላይ የቅድሚያ ክፍያው ለተቋራጩ መከፈል ያለበት ተቋራጩ ስራውን ለመጀመር የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን እነዲረዳው ታስቦ ሲሆን ይህም የሚከፈለው ተቋራጩ ለግንባታ ስራው የሚያገለግሉ ማሽኖችን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን መግዛቱን ወይም ማዘዙን የሚያሳይ መረጃ ሲያቀርብ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ በስራው ጊዜያትም ገንዘቡን እነዚህን ዕቃዎችና ማሽኖችን ለመግዛትና ወደ ግንባታ ቦታው ለማንቀሳቀስ/ለማዘዋወር የተጠቀመበት መሆኑን የሚያሳይ ፋክቱር/Invoices ለኢንጂነሩ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡


ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ የሚስተዋለው ችግር ቡዙ ጊዜ ተቋራጮች የቅድሚያ ክፍያውን ለታለመለት አላማ አያውሉም የሚል ሲሆን ይህም ችግር በተለይ በግንባታው ዘርፍ በተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ይህም ትልቁ ችግር መነሻው እነዚህ ተቋማት ምንም የሚያቅርቡት ዋስትና ሳይኖር ባቋቋማቸው መስሪያ ቤት ደብዳቤ ላይ ብቻ ተማምኖ ክፍያው ስለሚሰጣቸው ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ወይም በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የኢንሹራንስ ዋስትና ያቀረቡ ተቋራጮችን አሰሪው/ተዋዋዩ የመንግስት አካል አስፈላጊ ሲሆን፡ የቅድሚያ ክፍያው ገቢ የሚደረግበትና ከውሉ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ብቻ በመንግስትና በኢንተረፕራይዙ ወይም በኮንትራክተሩ ተወካዮች በጋራ ፊርማ ወጪ የሚደረግ የተለየ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ሊያዝ ይችላል፤ ገንዘቡም ለታሰበለት አላማ ብቻ እንዲውል የተለየ ስምምነት መፈራረም አለበት፡፡


ስለዚህ የቅድሚያ ክፍያ ማለት ተቋራጩ ለስራው ማስጀመሪያ የሚሆኑትን የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች መግዢያነት የሚውል በአሰሪው የመንግስት መስሪያ ቤት በቅድሚያ የሚከፈለው ገንዘብ ነው፡፡ ይህም ምንም ስራ ሳይሰራ የሚከፈል ገንዘብ ስለሆነ ለተቋራጩ ዕዳ ወይም ብድር ነው፡፡ ስለሆነም ተቋራጩ ብድሩን እንዲምልስ ይገደዳል ማለት ነው፡፡


በመሆኑም ተቋራጩ ይህንን ብድር እንዴት ይመልሳል የሚለው አንዳንድ ጊዜ በግንባታ ውሎች ላይ አለመግባባት ያስነሳል፡፡ በግዢ መመሪያው አንቀፅ 16.26.9 ላይ እንደተገለፀው ለተቋራጮችና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተከፈለ የቅድሚያ ክፍያ በውሉ አፈፃፀም የተለያዩ ደረጃዎች ላይ በክፍያ ሰርተፍኬት ፀድቀው ከሚከፈሏቸው እያንዳንዱ ክፍያዎች ላይ እየተቀነሰ ሙሉ የቅድሚያ ክፍያው እስኪመልስ ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ያስቅራል፡፡ ይህም ማለት ተቋራጩ የወሰደውን የቅድሚያ ክፍያ ሙሉውን ከአንድ ወይም ከሁለት ክፍያዎች ላይ የመክፈል ግዴታ የለበትም፡ አሰሪ መስሪያ ቤቱም ሙሉ ክፍያውን አንዴ ቀንሶ ማስቀረት አይችልም ማለት ነው፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዳድ ጊዜ ሙሉ ቅድሚያ ከፍያውን በአንዴ ቀንሰው በማስቀረት ከተቋራጮች ጋ እሰጣገባ ሲገጥሙ ይስተዋላል፡፡ ይህ ከህጉ አግባብ ውጭ ነው፡፡


የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ሙሉውን ሳይመለስ በተለያዩ ምክንያቶች ውሉ ቢቋረጥ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ የከፈለውን ገንዘብ ማስመለስ እንዲያስችለው ተቋራጩ የሚያቀርበው ዋስትና ክፍያው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስገዳጅነት እንደሚኖውም መመሪያው ይገልፃል፡፡ ውሉ ቢቋረጥ እንኳን ያልተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው ወዲያውኑ ካለምንመ መቃወሚያ እንዲከፍል ይገደዳል ይላል የመደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ ክሎስ 60.7፡፡


https://t.me/engineer03
Forwarded from Exam for Civil engineer's
💬The force in BF of the truss shown in given figure, is

A. 4t tension

B. 4t compression

C. 4.5t tension

D. 4.5t compression

E. zero.

For your answer and comments send here @engineersworks

Add your engineer's family
💬The cost of the earthwork in excavation for the surface drain of cross-section shown in the given figure for a total length of 5 metres @ Rs. 450% cum, is___________

A.Rs. 400

B.Rs. 425

C.Rs. 450

D.Rs. 500


For your solution, use @engineersworks
Civil Engineering
💬The cost of the earthwork in excavation for the surface drain of cross-section shown in the given figure for a total length of 5 metres @ Rs. 450% cum, is___________ A.Rs. 400 B.Rs. 425 C.Rs. 450 D.Rs. 500 For your solution, use @engineersworks
📝Solution

The length of drain = 5m.

Width of drain as per figure = 0.5m.
Depth of drain as per figure = 0.4m.

Total qty = 5 * 0.5 * 0.4 = 1 cum.

As per the question, cum excavation rate is 450%.

So the total cost required for excavation of drain is = 1 * 450 = Rs.450.

Therefore, the answer is "C."
Bonds in brick wall 🧱


ወደ ጥያቄና መልስ ቻናል ይግቡ
🔑ለሁሉም ምሃንዲስ የሚጠቅም
🔆ለተማሪዎችም ሼር ያድርጉሏቸው
👇Click on the link 👇

https://t.me/exam_room
Exam ከናፈቃችሁ ፈታ በሉበት !

@engineersworks
👉Some important facts @engineer03

🚧1. Weight of one cement bag = 50 kg

🚧2. Minimum thickness of slab = 125 mm

🚧3. Minimum lintel thickness =15 cm

🚧4. Minimum diameter of bars used in slab= 8 mm

🚧5. Minimum diameter of bars Used in column = 12 mm

🚧6. Maximum diameter of bars in slab= 1/8x(thickness of slab )

🚧7. Maximum chair spacing = 1m

🚧8. Initial setting time of cement = 30 min

🚧9. Final setting time = 10 hrs ( 600 minutes )

🚧10. DPR = Detailed Project Report

🚧11. Unit weight

▶RCC = 25 KN/ m3
▶PCC = 24 KN/ m3
▶Steel = 7850 kg/ m3

🚧12. Minimum number of bars For square column or rectangular = 4 bars & For circular column = 6 bars

🚧13. Weight of steel = D2/162.2 kg/m.

🚧14. Slope of staircase = 25° -40° from horizontal.

🚧15. Size of concrete testing cube= (150x150x150)mm.

🚧16. Concrete cube is filled in 3 layers.

🚧17. Slump cone is filled in 4 layers.

🚧18. Cement should be used within three months of manufacturing.

🚧19. Minimum thickness of shear wall = 150 mm.

🚧20. Maximum thickness of shear wall = 400 mm.

🚧21. Universal testing machine is used for compression Test of concrete and tensile test of steel reinforcement.

🚧22. Minimum curing period of normal weather conditions is = 7 days

🚧23. Minimum curing period of dry and hot weather conditions is = 10 days

🚧24. Minimum percentage of steel in column = 0.8% of the cross section.

🚧25. Normal cover

➡️Footing = 50 mm
➡️Column = 25 mm
➡️Slab = 15 mm
➡️Beam = 25 mm

🚧26. Number Of Clear span stirrups in beam = Center to Center length /Total Length +1

🚧27. RCC is affected by water because of the corrosion of reinforcement bars.

🚧28. PCC is not affected by the water

🚧29. Maximum free fall of concrete = 1.5 m

🚧30. Air voids left in concrete is called as Honey Combing.

🚧31. The transverse reinforcement of column are called TIES.

🚧32. The transverse reinforcement in beams are called STIRRUPS.

🚧33. Cement ingredients are Burnt @ 1400°C temperature

🚧34. Short columns fail in Crushing.

🚧35. Long columns fail in Buckling.

🚧36. Intermediate columns can fail both in Buckling and Crushing.

🚧37. Strength of reinforcement shouldn't be less than 15 % of its designated strength.

🚧38. Compressive strength of bricks

▶️1st class bricks = 105 kg/cm2.

▶️2nd class bricks = 70 kg/cm2.

▶️3rd class bricks = 35 kg/cm2.

🚧39. PH value of water used concrete should not be less than 6.

🚧40. Riser = (150 - 200) mm.

🚧41. Tread = (250 - 300) mm.

🚧42. Height of parapet wall should be= 1m.

🚧43. TMT - Thermo mechanically treated bars.

🚧44. TMX - Thermax powered bars

🚧45. SDB - Super ductile bars.

#ConstructionNotes

@engineer03
New job see here
👉 @engineersworks


Exam @exam_room
Project Coordinator
#bulbula_construction
#engineering
#engineering_management
#coordinator
Addis Ababa
Bachelor’s degree in any major with good computer skills (Word, Excel and PowerPoint) & written English
N.B: Recent graduate (2019 and 2020 ONLY)
Minimum Years Of Experience: #0_years
Deadline: December 26, 2020
How To Apply: Send your resume via: hraddisababa@gmail.com.

Wash Technical Program Officer Assistant
#inter_aide_france
#engineering
#hydraulic_engineering
#assistant
SNNPR, Mudula
BSc in Hydraulics, Civil engineering or related fields with relevant work experience in Rural Water Supply Program
Competence:-
- Field work (community meeting, site supervision…)
- Strong social inclination (knowledge of community based approach, training of community-based associations…)
- Fluent in spoken and written English, Amharic and relevant language (Gamogna, Kambatigna, Wolaytigna)
- Basic skill on computer application software
- Motorbike driving license is a plus
Minimum Years Of Experience: #3_years
Deadline: December 7, 2020
How To Apply: Send your CV via: interaiderecruitment@gmail.com or in person to the following address: Sodo or Shinshicho office
NB: only selected candidates will be notified for further interview

Wash Gamo Zone Manager
#inter_aide_france
#engineering
#hydraulic_engineering
#manager
SNNPR, Gamo
BSc or MSc in Hydraulics or Civil engineering with strong inclination toward social and field work with relevant work experience in management of rural water supply programs
Competence:-
- Field work (community meeting, site supervision…)
- Interest in water supply schemes management, water supply network design and construction
- Fluent in spoken and written English, Amharic and relevant language (Gamogna, Kambatigna, Wolaytigna)
- Decent usage of computer application software & Motorbike driving license is a plus
Minimum Years Of Experience: #5_years
Deadline: December 7, 2020
How To Apply: Send your CV via: interaiderecruitment@gmail.com or in person to the following address: Sodo or Shinshicho office
NB: only selected candidates will be notified for further interview
@engineer03
What machine is this ?
1. Hoist
2. Telehandler
3. Mobile telescopic crane
4. Tower crane

#equipment

@engineer03
🚧የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat
with Drop or Solid Slab
.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::

@engineer03
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Soil nailing uses grouted, tension-resisting steel elements (nails) to reinforce in situ soils and creating a gravity retaining wall for permanent or temporary excavation support.

Common uses
- Stabilize slopes and landslides
- Support excavations
- Repair existing retaining walls

Process:-
Soil nail walls are generally constructed from the top down. Typically, soil is excavated in three to six feet deep stages. After each excavation stage, near-horizontal holes are drilled into the exposed face at typically three to six foot centres. Tension-resisting steel bars are inserted into the holes and grouted in place. A drainage system is installed on the exposed face, followed by the application of reinforced shotcrete wall facing.
Precast face panels can also be used. Bearing plates are then fixed to the heads of the soil nails. This installation process is repeated until the design wall depth is reached. The finished soil nails then produce a zone of reinforced ground.

#geotechnical #soilnailing
@engineer03
👉‌ጥናታዊ ጽሑፍ ለምታዘጋጁ ተመራቂ ተማሪዎች ስለምትሠሩት Proposal እና Research ትንሽ እገዛ እንስጣቹ ...
@Engineer03

▶️ በመጀመሪያ ደረጃ የሚመርጡት የጥናት ርዕስ መነሻውና መድረሻውን ሥነፍኖት በትክክል የተረዱትን መሆን ይገባዋል። ጥናታዊ ጽሑፍ መጨረሻ መታወቅ ያለበት ውጤቱ ነው እንጂ ሂደቱ መሆን የለበትም። ህደቱን ገና ከመጀመሪያው በትክክል እና በግልጽ (Accurately and clearly) መረዳትና ማወቅ ለውጤታማነት ተገቢ ነው። የጥናቱ ንድፈ ሀሳብ (Proposal) በሚገባ የሚመራ መንገድ መሆን አለበት። ጥናትን በተመለከተ ምሁራኑ የሚሉትን አንድ ታላቅ ገለፃ ላስታውሳችሁ "A research is as good as its propsal" -(የአንድ ጥናት ጥሩነት እንደ ንድፈ ሀሳቡ/ዕቅዱ/ ጥሩነት ይታወቃል) እንደማለት ነው። በመሆኑም የተወሰነ ምክረ ሃሳብ እገዛ ለማድረግ ጥቂት ነገር ላስታውሳችሁ። ልብ ሊባል የሚገባው ግን የግል ድጋፍ እንጂ የተቋም ይፋዊ format እያሳወቅሁ አለመሆኑን ነው።
.
▶️1ኛ. Title ፦ ርዕስ ለመመረጥ የመጀመሪያው ትኩረት ከሙያዎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ያስተውሉ። ከዚህ ባለፈ ሙያዎትን ተጠቅመው በአካባቢዎ ባለው ማህበረስብ ውስጥ ያለውን ችግር በመፍታት አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉበት ቢሆን ይመረጣል። ከዚህ አንጻር "ይህንን አይነት መፍትሔ ብሠራለትስ" የሚሉትን ችግር መርጠው አጭር እና ገላጭ የሆነ የጥናት ርዕስ መምረጥ ነው። ከተቋሙ አካባቢ ወጣ ያሉ ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ርዕሶች መሆንም ይችላሉ።
.
▶️2ኛ. Introduction to Your title ፦ በዚህ ርዕስ ሥር ስለ ጥናቱ ርዕስ ምንነት ገለጻ ማድረግ ነው። በዚህ ርዕስ ሥር የሚያካትቷቸው ይዘቶች defnitions, theories, materials used, tests, methods, constructions systems, types, ..... የመሳሰሉት ቢሆኑ መልካም ነው።
.
▶️3ኛ. Background to your title ፦ ይህ ደግሞ ስለሚያጠኑት ጥናት ታሪካዊ ዳራ/አመጣጥ (hisorical status) ገለጻ ማድረግ ነው። [who start investigate first, which country use, improvement (ማን ጀመርው? የት ቦታ? መቼ? በምን ተጀምሮ ወዴት ተሻሻለ all improvements፣ አሁን የት ደረሰ፣ .....) የሚሉትን የርዕሳችሁን ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስካለበት ድረስ ብቻ የምታስቀምጡበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ እርስዎ ሊጨምሩበት ወይም ሊቀይሩት ወይም ሊያስተካክሉት የሚችሉበትንም ጎን ጠቆም ማድረፍ መልካም ነው።
.
▶️4ኛ. Statement of the problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
.
▶️5ኛ. Objectives {General and Specific}፦ ጠቅላይ/ዋና ዓላማ ከአንድ ዓረፍተ ነገር ባይበልጥ ከበዛ ደግሞ ከሁለት በላይ እንዳይሆንይመከራል። በዝርዝር ዓላማ (specific objectives) የሚቀመጡት ደግሞ በዋና ዓላማ ዉስጥ የሚገኙ በጥናቱ መከናወን የሚታወቁ የተለያዩ መልሶችን ታስቀምጣላችሁ።
.
▶️6ኛ. Scope of the Research ፦ ይህ የሚገልጸው የጥናትችሁን ስፋተ-ሜዳ ነው። ምን ምን እንደሚያጠቃልል ወይም እንደሚዳስስ፣ ምን ምንን ደግሞ እንደሚተው /እንደማያጠቃልል/ ከነምክንያቱ፣ ለምን አይነት ተግባር የሚውል እንደሆነ ... በአጠቃላይ የጥናቱን መጠነ-ስፋት ወይም ይዘት የሚያስረዳ ይሆናል።
.
▶️7ኛ. Litrature review ፦ [በርዕሱ ዙሪያ እስካሁን የተጠኑ ጽሁፎች ምን ብለዋል?] “ማን የተባለው ሰው በየትኛው መጽሐፉ/ጥናቱ የትኛው ገጽ ላይ ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ምን ብሏል?“ የሚለውን መረጃ የያዘ ነው። በ"Litrature" ሥር የሚያካትቱት የቀደሙ ህትመቶች ማስረጃ ከእርስዎ ጥናት ጋር ተያያዥ ሀሳብ ያላቸውን ብቻ ነው። እርስዎ የማይዳሡትን ነገር በዚህ ርዕስ ሥር ማስገባት ከማንዛዛት እና ትርጉም አልባነት አያልፍም፣ ይልቁንም ሥራዎትን ውጤት (value) እና ተቀባይነት (acceptance) ሊያሳጣ ይችላል። በዚህ ሥር የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች reference specification [books, quastionary, journals, published apers, recorded interviews, vedio evidences] መሆን አለባቸው እንጂ guide specification [oral speeking, internet notes, handouts, non published documents] ላይ ያገኙትን ነገር ባይጠቀሙ ይመከራል። የተጠቀሙትን ምንጭም ከነመገኛ ገፁ አብረው ዋቢ ማስቀመጥም ተገቢ እና ግዴታ ነው።
.
▶️8ኛ.METHODOLOGY ፦ ይህ ደግሞ ዋናው የጥናት ሂደት መረብ ነው። ትናቱ የሚከናወንበት አካባቢ (study area)፣ ናሙና የሚወሰድበት የናሙና አወሳሰው ሥነዘዴ - ሥነዘዴው የተመረጠበትን ማስረጃ ምክንያት ጨምሮ (sampling system)፣ ከንድፈ ሀሳብ እስከ ፍጻሜ ያለውን የሚያሳይ የጥናቱ መነሻና መድረሻ ፍሰት (research deign - ብዙ ጊዜ በ"Chart" ሊገለፅ ይችላል) መካተት አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪ ቤተሙከራዊ ጥናት (Experimental research) ከሆነ የተለያዩ የቤተሙከራ ፍተናዎች (laboratory tests) የሚሠሩበት ስለሆነ የሚሰሩት ሙከራዎች (tests) የሚያስፈልጉ መሥሪያ ነገሪች (materials), መሥሪያ መሳሪያዎች (equipments), የሙከራ ሂደቶች (procedures to be used) የሚሉት ይዘቶች በግልፅ መታወቅ አለባቸው።
ከቤተሙከራ ውጪ ከሆነ ደግሞ አንዳንዶቹ ተግባራዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ የሚጠቀሙትን ሂደት ማስቀመጥ ተአቢ ነው። (ምሳሌ ~ መኪና መሥራት፣ በፀሀይ ጉልበት የሚሰራ ባቡር መሥራት ሊሆን ይችላል)።
በሌላ በኩል Theoretical or statistical data analaysis ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ከሆኑ ደግሞ የሚጠቀሟቸው የቃለመጠይቅ ጥያቄዎች (interiview questions)፣ የሚያስሞሉት የሰነድ ጥያቄ (questionair formats for data statistics)፣ የሚጠቀሟቸው የኮምፒዉተር ፕሮግራም (softwares to be used)፣ የሚፈልጉት ስታቲካዊ መረጃ (statistic data)፣ የሚሳተፉት ባለድርሳዎች (participants /responsible bodies)፣ የጥናት ማመዛዘኛ መንገድ (analaysis statics method..) የመሳሰሉትን ማካተት ተገቢ ሲሆን ይህ "Methodology" የሚባለው ክፍል አንድ ሰው በየትኛው ሥነዘዴ እንደሠራ የክንውን ሂደቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ነው።
.
✉️NB ፦ እነዚህ ከላይ ያሉት በሙሉ በንድፈ ሀሳብ ሰነድ (proposal document) ላይ ጭምር መስፈር ኣለባቸው ሲሆኑ ቀጥሎ ያለው ተራ ቁጥር 9፣ 13፣ 14 ብቻ ግ ን ጥናቱ ከተጀመረ በኋላ የሚካተ

‌▶️9ኛ .RESULT AND
DISCUSSION ፦
.
❖RESULT [ፕሮጀክቱ የሚሰራው በTEST ከሆነ የተገኘውን ዉጤት፣ theory ከሆነ የ[intrview, questionaier, system documented data, real and visual application,...] የሚያሳዩትን ዉጤት/አኳኋን ማስቀመጥ ነው፡፡
❖DISCUSSION [ከተገኘው ውጤት አንጻር ለእያንዳንዱ ውጤት ሙያዊ ማብራሪያ እና የማሻሻያ ድጋፍ ሀሳብ ማስቀመጥ የሚጠበቅብዎት ክፍል ነው። [discuss weather the result implies good or bad accourding to proffesional point of view based on standards, laws, codes, contract agreement document, principles, softwares ... and put your proffesional solution for failures in the results]
.
▶️10ኛ. Beneficiariers of your project output {may not mandatory}፦ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጠቃሚ አካላት እነማ ናቸው። [may be scientists, teachers, students, farmers, gevornment, contractors, or all ethiopians or world.... as per your study scope]
.
▶️11ኛ. Desimination of output [i.e. how you make available your study paper for users? May be by puting at different libraries, publishing and posting on google, by training.....]
.
▶️11ኛ. የማጥኛ ጊዜ ሰሌዳ (Schedule)
▶️12ኛ. የሚያስፈልገው በጀት (Budget/cost)
.
▶️13ኛ . Conclusion
▶️14ኛ. Recommendation፦ [this should be not advice rather it is the measure to be taken for problems and organaizatinal failures based on your proffesional know how!]
.
▶️15ኛ. Reference
▶️16ኛ. Appendex .
⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።👇👇👇https://t.me/engineer03
👉በቁፋሮ ወቅት ሳይት ላይ ሊገኙ ስለሚችሉ አንዳንድ ነገሮች
ኮንስትራክሽን ኮንትራት ውል ምን ይላል???

⏩ለምሳሌ: ወርቅ ወይም ሌላ መዐድን ቢገኝ

🚧ምላሹ ከዚህ ፅሁፍ በምስል ይመልከቱ።

#ConstructionLaw

@engineer03