Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association
5.36K subscribers
443 photos
12 videos
231 files
156 links
Tefera Gebeyehu Werku
General Manager, EPHEIA
Institutional email: info@ephetveta.com




Website : https://ephetveta.com
Download Telegram
✅ከትምህርት ሚኒስቴር የተላለፈ መልዕክት

ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

ትምህርት ሚኒስቴር የሬሜዲያል ተማሪዎች በተመለከተ አፋጣኝ ምላሽ እንድትሰጡ ስለሚፈልግ ይህን ተግባራዊ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።
⚠️ መረጃው እስከ ነገ ማለትም ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንድትሞሉ አሳስቧል።
👍5❤2
Shape the Future of African Business Schools in Addis Ababa! 🌍✨
​Join a landmark global summit at the UN ECA, Africa Hall. This is the premier academic networking bridge for Ethiopian institutions to connect with 60+ global universities and 150+ international delegates.

​📍 Location: UN ECA, Africa Hall
📅 Date: 13–15 May 2026

​🔥 High-Impact Sessions & Masterclasses:

​The Future of Work: Exclusive Masterclass on modern career shifts.
​AI in Education: Navigating the promise and pitfalls.
​Powering Youth: Skills and mindsets for a digital global economy.
​Quality & Innovation: Accreditation, ethics, and impactful research.
​Teaching for Tomorrow: Rethinking learning for the next generation.

​🎟 EXCLUSIVE LOCAL OFFER
​Special discounted rates are available for local Ethiopian universities and colleges.

Registration:https://www.aabschools.com/events/aabs-2026-connect-conference

​⚠️ URGENT: Seats for local delegates are strictly limited. Secure your institution’s on time.     
📞 +251904848586
❤1
#MoH
#የብቃት_ምዘና_ፈተና

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ - ጤና ሚኒስቴር

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ባለሙያዎች በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ስለዚህም ተፈታኞች ተቋሙ አዲስ ባለማው ሲስተም መረጃችሁን ለማስገባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (16 Digit FAN) እና ስልክ ቁጥር አስፈላጊ በመሆኑ ተመዛኞች ከሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ሊንክን በመጫን ከላይ የተገለፀውን እንዲሁም ሲስተሙ የሚጠይቃችሁን መረጃ በማሟላት ለምዝገባ ዝግጁ እንድትሆኑ ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል፡፡

በተጨማሪ ነባር ተመዛኞች ሲስተሙ የጤና ሚኒስቴር መለያ ቁጥር (Registration Number) ስለሚጠይቃችሁ ተቋሙ በይፋዊ የቴሌግራም ገፁ ከለቀቀው የተፈታኞች ዝርዝር ውስጥ ስማችሁን በመፈለግ ከስማችሁ ትይዩ ያለውን መለያ ቁጥር (Registration Number) ተጠቅማችሁ መረጃችሁን እንድታያይዙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
❤10👍4🙏1
🔔 #አስቸኳይ

የፊታችን ሰኞ መሠጠት የሚጀምረውን የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ተከታዩን ሊንክ (https://verify.ethernet.edu.et/) ከተጫኑ በኋላ Remedial Examination የሚለውን ይጫኑ፣ Start Verification የሚለውን በመጫንና የሚያስፈልገውን በመሙላት ያረጋግጡ።

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 17-20/2018 ዓ.ም እእንደሚሰጥ ይታወቃል።

verify.ethernet.edu.et
Ministry of Education
Ministry of Education | Exit Exam Verification
❤5
ማስታወቂያ

የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ።

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የምሰጥባቸው ቀናት እንደምከተለው የተሸጋሸጉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@FDRE_EAES_Official
❤6👍1
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሚ ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥራችሁ ጋር አስተሳሰራችሁ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች በሙሉ፤ ጤና ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት እየተዘጋጀ በመሆኑ ሁላችሁም ተመዛኞች ከግንቦት 20 – 26/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን FAYDA and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ  እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦  
▪ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት  የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

▪ ለብቃት ምዘና ፈተና የመፈተኛ ጣቢያ መምረጥ የምትችሉት ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ያያያዛችሁ ተመዛኞች ብቻ ይሆናል፡፡ 

▪ በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡

▪ ለበለጠ ማብራሪያ ከስር የተያያዘውን ቪዲዮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
❤5
*የሬሜዲያል ፈተና ፕሮግራም*

የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል (አቅም ማሻሻያ) ፕሮግራም ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ለአምስት ቀናት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በተጠቀሱት ቀናት በሁለት ፈረቃ በጠዋት እና በከሰዓት መርሐግብር የሚሰጠው የሪሚዲያል ፕሮግራም (የተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች) የፈተና መርሐግብር ከታች ተያይዟል።
❤3
ከጤና ሚኒስቴር የተላለፈ መልዕክት:-
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___

"ጤና ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ያያያዛችሁ ተመዛኞች የተቀመጠውን https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን የመፈተኛ ጣቢያ እየመረጣችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ የፈተና ጣቢያ መረጣ እስከ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ምርጫችሁን እንድታገባድዱ እያሳሰብን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ምዝገባው የማይራዘም መሆኑን እናሳውቃለን"፡፡
❤1
#ለሁሉም_የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት
#ባሉበት፤

በunified መሶብ አማካኝነት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ ዝርዝር ገለጻና እና ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።
ስለሆነም በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚደረገው ገለጻ እና ውይይት ላይ የተቋሙ የበላይ ኃላፊ እና ሬጅስትራር ኃላፊ አርብ፣ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ በጥብቅ እያሳወቅን ስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ሀላፊዎች ተወካይ መላክ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
❤8
4_5852527560872697556.pdf
6 MB
የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መርሐግብር (Exit Exam Schedule)

የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል
❤1
የመውጫ ፈተና #በድጋሚ ተፈታኝ የሆናችሁ (Re-sitters) የፈተና መግቢያ ትኬታችሁን https://verify.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት አውርዳችሁ ፕሪንት ማለት ይኖርባችኋል።
(ከላይ በምስል የተያያዘውን ቅደም ተከተል በመጠበቅ ያውርዱ።)
❤5
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___

ጤና ሚኒስቴር ከሰኔ 17 እስከ 19/2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ተፈታኝ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በመረጣችሁት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ወደ ፈተና ጣቢያ ስትመጡ የብሄራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print out ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ
❤4