Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association
5.35K subscribers
443 photos
12 videos
231 files
156 links
Tefera Gebeyehu Werku
General Manager, EPHEIA
Institutional email: info@ephetveta.com




Website : https://ephetveta.com
Download Telegram
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአገራዊ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተገለጸ!

#Fastmereja:- በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በትምህርት ተደራሽነት፣ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የስልጠና መስክበመክፈት እንዲሁም የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር አስታዉቋል።

ማህበሩ «የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አበርክቶዎች፣ ተግዳሮቶችና መፃኢ ዕድሎች» በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የግል ትምህርት ተቋማት በመንግስት ተቋማት መግባት ላልቻሉና በተለይም በራቅ ያሉ የአርብቶ አደርና አርሶ አደር አካባቢዎች ለሚገኙ ዜጎች በቀን፣ በማታና በርቀት ትምህርት የከፍተኛ ትምህርት እድል በማስፋት ረገድ የጎላ ሚና እንዳበረከቱ ገልፀዉ በርካታ ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ትልቅ እቅስቃሴ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ሆኖም ዘርፉ አሁንም ቢሆን ዘርፈ-ብዙ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም አዋጆች፣ መመሪያዎችና የዳግም ምዝገባ መስፈርቶች የአሰራርማነቆዎች በመሆን ተቋማቱን እየፈተኗቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ ማህበሩ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመከባበርና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ገንቢ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝም ነዉ የተገለፀዉ።

በሌላ በኩል ማህበሩ ለሕገ-ወጥነት ጥብቅና እንደማይቆም በመግለጽ፣ አሁን ባለው የምዝገባ ወቅት ሁሉም ተቋማት መንግስት ያስቀመጠውን የከፍተኛና ቴክኒክና ሙያ የመግቢያ መስፈርት ሳይሸራረፍ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያሳሰቡ ሲሆን አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎችና ወላጆችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

📷ዘዉዱ
❤1