Eritrea Press Amharic (የኤርትራ ፕረስ)
2.7K subscribers
824 photos
30 videos
296 links
የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ይከታተሉ
Download Telegram
"በመከራ ጊዜ ከጎናችን የነበራችሁ የክፉ ጊዜ ወዳጃችን ነዎት" ጄኔራል አልቡርሃን ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር ዛሬ በቻይና ሲገናኙ ያካስተላለፉት የምስጋና ቃል
👍2❤1
"Ethiopian militias invade Sudanese territory, escalating violence and looting"

Armed Ethiopian militias have launched a renewed incursion into Sudanese territory, penetrating 15 kilometres deep into the Al-Fashqa border region.
Reports of escalating violence, looting, and attacks on farmers and herders in the border area have raised alarm as the militias attempt to seize control of agricultural lands.
The Sudanese military, which had retaken control of approximately 90% of Al-Fashqa since 2020, is now facing a resurgence of Ethiopian aggression. Military sources revealed that the militias have targeted Sudanese herders, killing one and stealing hundreds of cattle.
In the Quraysha locality, local livestock owner Abdallah Ahmed reported being robbed of 140 sheep by the militias at gunpoint. He warned of the dire consequences of unchecked violence, highlighting the militias’ attempts to prevent Sudanese farmers from cultivating their lands during the crucial rainy season.

Sudan Tribun
❤1👍1
#Ethiopia: Finance Ministry seeks Council of Ministers' approval for salary increases ranging from 5% to 332% for 2.4 million public servants

The Ministry of Finance has submitted a proposal to the Council of Ministers seeking approval for a salary increase for 2.4 million public servants. If approved, the adjustments, ranging from 5% to 332%, would take effect on 11 September 2024, requiring an additional 91.4 billion birr in the national budget.

The proposal follows a study highlighting the financial challenges faced by many public servants due to rising living costs. The study, reviewed by the national macroeconomic committee, underscores the need for urgent intervention, particularly for lower-income employees, to alleviate poverty and improve living standards.
👍2❤1
ግብጽ ወታደሮቿን በሶማሊያ ማስፈሯ ያለው አንድምታ ምንድን ነው?

በቅርቡ በሶማሊያ እና በግብጽ መካከል የተፈረመው ወታደራዊ ስምምነት ተግባራዊ ወደ መሆን ተሸጋግሯል።

ለዚያም ነው የግብጽ ሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የጦር ጄነራሎችን እና መሳርያዎችን ይዘው ማረፋቸው የተሰማው።

በግብጽ የሶማሊያ አምባሳደር አሊ አብዲ አዋሬ፣ ይህ የግብጽ ጦር ከጥር 2025 ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት ጥላ ሥር በመሆን የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ)ን የሚተካው አዲሱ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ከመተካቱ በፊት የሆነ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በመጪው ዓመት ጥር ወር የሚጠናቀቀው በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ)ን የሚተካው አዲሱ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በተለያዩ ጊዜያት የሚሰማሩ 10 ሺህ ወታደሮችን ግብጽ ለማሰማራት ዕቅድ ይዛለች።

የግብጽ ጦር የሶማሊያ መሬት ላይ እግሩን ማሳረፉ በኢትዮጵያ ዘንድ በበጎ አልታየም።

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት፣ ራስን እንደ ነጻ አገር ካወጀችው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ካላገኘችው ሶማሊላንድ ጋር የባህር ኃይል ጣብያ ለማግኘት ባደረገችው ስምምነት የተነሳ ከግብጽ እና ከሶማሊያ ጋር ሆድና ጀርባ ከሆነች ሰንበትበት ብሏል።

ምንም እንኳ ግብጽ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አየር ማረፍያ ስለደረሱት የጦር ጄነራሎቿ እና መሳርያዎቿ ያለችው ነገር ባይኖርም ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ግን፣ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት መንገሱን የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ መሆኑን በማንሳት ይህ ለአዲስ አበባ የተላከ መልዕክት ነው እያሉ ይገኛሉ።

ሌሎች ደግሞ ግብጽ ሶማሊያ ለጠየቀችው ድጋፍ በተለይ ደግሞ በቀይ ባሕር ላይ የራሷን ብሔራዊ ፍላጎት ለማስጠበቅ እና ለመከላከል ላቀረበችው ጥያቄ የተሰነዘረ የበጎነት እጅ የውጪ ጉዳይዋ ፖሊሲ አካል ነው ይላሉ።

ይህ የሁለቱ አገራት ጥምረት ግን ዳግም በአፍሪካ ቀንድ የውጪ አገራት ፍላጎት እና ተሳትፎ ላይ በተለይም ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ያላቸው ፍላጎት ላይ ትኩረት እንዲደረግ ያደረገ ነው።
👍5👎2❤1
👍2
የኢትዮጵያ እና የግብጽ ወታደራዊ አቅም እንዴት ይነጻጸራል?

አባይ ወንዝ ላይ ተገንብቶ እየተጠናቀቀ ባለው የሕዳሴ ግድብ ምክንያት ውዝግብ ውስጥ የቆዩት ግብጽ እና ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል።

በተፈጥሯዊ ድንበር የማይገናኙት ሁለቱ አገራት፤ የግብጽ ጦር ሶማሊያ መግባቱን ተከትሎ አዲስ አበባ እና ካይሮ ፊት ለፊት ተፋጥጠዋል።

ከሰሞኑ በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት ያየለው ግብጽ እና ሶማሊያ የደረሱትን ወታደራዊ ስምምነት ተከትሎ ጦር መሳሪያ የያዙ የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሞቃዲሾ ካረፉ በኋላ ነው።

የአውሮፕላኖቹን መምጣት ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የግብጽ ጦር በሶማሊያ እንዲሰማራ መደረጉ ለሶማሊያ እና ለአጠቃላዩ የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ደኅንነት አሳሳቢ ነው በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ መንግሥት “ቀጠናውን ለማተራመስ ከሚሹ የውጭ ኃይሎች ጋር እየሠራ ይገኛል” ማለቱ ይታወሳል።

ባለፉት ቀናት ግብጽ በበኩሏ የውሃ ድርሻዬን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ከመውሰድ ወደ ኋላ አልልም ስትል ማሳሰቢያ አዘል ደብዳቤ ለፀጥታው ምክር ቤት ልካለች።

በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለፀጥታው ምክር ቤት በተላከ ደብዳቤ ላይ “ግብጽ ሕልውናዋን ለመከላከል እና የሕዝቦቿን ጥቅም ለማስከበር በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መሠረት ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጁ ናት” ተብሏል።

በግሎባል ፋየር ፓወር አሃዝ ኢትዮጵያን ከ145 አገራት 49ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ግብጽን ደግሞ 15ኛ ላይ ትገኛለች።

ኢትዮጵያ በወታደራዊ አቅም በአህጉሪቱ ካሉ 54 አገራት የአምስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ቀዳሚዋ ደግሞ ግብጽ ናት።

የግብጽ ጦር በሠራዊት ብዛት በአየር፣ በምድር እና በባሕር ኃይል ከኢትዮጵያ ጦር ያለው ልዩነት ሰፊ ነው።

የጦር ሠራዊት ብዛት

ምንም እንኳ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ተቀራራቢ የሆነ የሕዝብ ቁጥር ቢኖራቸውም፤ በሠራዊት ብዛት ላይ ግን ልዩነታቸው ሰፋ ያለ ነው።

ኢትዮጵያ 162 ሺህ የሚሆን አጠቃላይ የሠራዊት ብዛት ያላት ሲሆን ግብጽ በአንጻሩ 440ሺህ ሠራዊት አላት።

ከዚህ በተጨማሪ ግብጽ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ተጠባባቂ ኃይል እና 300ሺህ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሲኖራት፤ ግሎባል ፋየር ፓወር ኢትዮጵያ ተጠባባቂ እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንደሌላት ያመለክታል።

አየር ኃይል፣ የምድር ኃይል እና የባሕር ኃይል

ግብጽ አጠቃላይ 1080 ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሲኖሯት ኢትዮጵያ ያሏት 91 ናቸው።

ከ1080 የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች 238 ተዋጊ ጄቶች ናቸው። ኢትዮጵያ ያላት ተዋጊ ጄቶች ደግሞ 23 ናቸው። የሄሊኮፕተር ቁጥርን ስንመለከት ግብጽ 338 ሲኖሯት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያለው የሄሊኮፕተር ብዛት 31 ነው።

በዕቃ ጫኝ የጦር አውሮፕላኖች፣ ለሥልጠና በሚውሉ እንዲሁም ልዩ ተልዕኮ በሚወጡ አውሮፕላኖች ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ የበላይነት አላት።

የምድር ኃይልን ስንመለከት ግብጽ ከ5300 በላይ ታንኮች ሲኖሯት የኢትዮጵያ የታንክ ብዛት 680 ነው።

ኢትዮጵያ ከ10ሺህ የማያንሱ ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች ሲኖሯት፤ ግብጽ ደግሞ ከ77ሺህ በላይ ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች አሏት።

በዚህ እኤአ 2024 በተሻሻለው የግሎባል ፋየር ፓወር ሪፖርት ላይ ባይጠቀስም ኢትዮጵያ ጥቂት የማይባል ቱርክ፣ ቻይና እና ኢራን ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) እንዳላት ይታመናል።

ግብጽ በበኩሏ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ የተመረቱ ወታደራዊ ዘመቻዎችን መፈጸም የሚችሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ታጥቃለች።

በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪካ ግዙፍ የባሕር ኃይል የገነባችው ግብጽ አብዛኛዎቹ የአሜሪካ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን እና የጣሊያን ስሪት የሆኑ የተለያዩ መጠን እና አገልግሎት ያላቸው 140 መርከቦች አሏት።

የባሕር በር አልባዋ የሆነችው ኢትዮጵያ ባሕር ኃይሏን መልሳ እየገነባች እነደሆነ ቢነገርም፣ በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ዘመቻን የሚወጡ ምንም አይነት የባሕር ኃይል መርከቦች የሏትም።

የሠራተኛ ኃይል፣ ፋይንስ እና ሎጂስቲክ

ለረዥም ጊዜ ቀጥሎ በሚካሄድ ጦርነት ውጤት ላይ የአንድ አገር ንቁ ተሳታፊ የሆነ ሠራተኛ ኃይል፣ ፋይናንስ እና የሎጂስቲክ አቅርቦት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

ግሎባል ፋየር ፓወር በአገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ እና በጦር ሜዳ ውሎ ግብዓት የሚሆኑ እንደ ተተኳሽ፣ የደንብ ልብስ፣ መለዋወጫዎች፣ መድኃኒት፣ ምግብ. . . እና የመሳሰሉትን የሚያመርተው ሠራተኛ ኃይል ወሳኝ ነው ይላል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ከግብጽ በ10 ሚሊዮን ሕዝብ በመብለጥ የተሻለ የሰው ኃይል አላት። በዚህ ሪፖርት ላይም ኢትዮጵያ በወታደራዊ አቅም ከግብጽ ተሽላ የተገኘችው ለግዳጅ ዝግጁ ሊሆን በሚችል የሰው ኃይል ብዛት ነው።

ግብጽ ለጦሯ የምታወጣው ወጪ በብዙ እጥፍ ከኢትዮጵያ ይበልጣል። የግብጽ ጦር ዓመታዊ በጀቱ 9.4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ በ10 እጥፍ አንሶ 888 ሚሊዮን ዶላር ነው።

አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ላላት ፍላጎቷ ትልቅ ሚና ያላት ካይሮ ከእኤአ 1980ዎቹ ወዲህ ለምጣኔ ሃብት እና ጦር መሳሪያ በሚል 50 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ድጋፍ አድርጋለች።

ይህም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ እና ግብጽ በቀጥታ ወደ ወታደራዊ ግጭት የሚገቡበት ዕድል ጠባብ ነው። በእጅ አዙር የሚደረጉ ግጭቶች ደግሞ አገራቱ ያላቸውን ወታደራዊ አቅም በሙሉ ለመጠቀም የሚያስችላላቸው አይደለም።

ከዚህ ባሻገር ግን የጎረቤት አገራትን የአየር ክልልን በማለፍ የሚፈጸሙ ድንበር ዘለል የአየር ጥቃቶች ቢኖሩ እንኳን በግሎባል ፋየር ፓወር ሪፖርት ላይ ባይጠቀስም ሁለቱም አገራት ዘመናዊ እና ጠንካራ የአየር መከላከያ ሥርዓት እንዳላቸው ይነገራል። #BBC
👍34❤11😁4
ክቡራን እና ክቡራት የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በወቅቱ በነበረው የኢንተርኔት ችግር ምክንያት ያቋረጥነውን የኤጀንሲያችንን ፕሮግራሞች በቴሌግራም፣ በዩቲዩብና በፌስቡክ በድጋሚ ማቅረብ የጀመርን መሆኑን ስናበስር በታላቅ አክብሮት ነው።
ፕሮግራማችንን ከታች በመረጣችሁት የማህበራዊ ሚዲያ ሊንክ ማለትም:-
የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ይከታተሉ
በቴሌግራም: https://t.me/eripressagencyamharic
በዩቲዩብ: https://youtube.com/@eritreanamharic?si=zQ3POUwsptGeUnYK
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/share/18rH1nemCH/

#Subscribe #Like #Share በማድረግ በቪዲዮ (በምስል) እንድትከታተሉን ስንጋብዛችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
Channel name was changed to «Eritrea Press Amharic (የኤርትራ ፕረስ)»