ET Netsa Apps™
24K subscribers
3.27K photos
476 videos
261 files
2.64K links
ET Netsa Apps™ is the premier choice and destination for anyone seeking knowledge and information about latest airdrops technology and online courses.
CA: EQAz_XrD0hA4cqlprWkpS7TIAhCG4CknAfob1VQm-2mBf5Vl

Buy ads: https://telega.io/c/ET_Apps
Download Telegram
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael B.)
#Repost

#የማለዳ_ወግ_ከናቲ_ጋር

ትህትና...በዚች ምድር ስኬትህን ከእነእርካታው አጣጥመህ የምትጎነጭባት ሚስጥር ናት።

ብራዳ:... አንተ የምርም አራዳ ከሆንክ: የምርም ለራሴ አውቃለው ካልክ እንግዲያውስ ትኩረትን ለመሳብ ፈፅሞ እንዳታስብ። ሲተኮርብህ ሊያውም በዚህ ዘመን አይን ቢበዛብህ እንጂ እንደአባቶቻችን ደጉ ጊዜ ቱ ቱ... ብሎ የሚሸኝህ ያለ እንዳይመስልህ። ቆቅ ሁን። ዓለም ሁሌም እንደምልህ በሰጥቶ መቀበል ቀመር ላይ የተንጠለጠለች ዥዋዥዌ ነች።

ይህን ሀሳብ ላነሳ የቻልኩት ደግሞ አንተ ወንድሜ በትሬዲንጉ ተለውጠህ: ነገ ኪስህ ደልቦና አብጦ እንደማይህ ስለማምን ነው። እናማ ያኔ ኪስህ ሲሞላ: ያኔ ማማው ጫፍ ላይ የደረስክ ሲመስልህ ልብህ እንዳታብጥብህ...ያኔ ከኔ በላይ ማን የሚያስብል ባለፀግነትን ስትቀዳጅ የተነሳህበትን እንዳትረሳ አደራ ልልህ ነው።

አራዶቹ ትህትናን ከሰው አይን መውጫ: ከትዝብት መራቂያ: ከአምላክ መታረቂያ ሲያረጉት ያልገባቸው ደግሞ ልባቸውን ያደነደነችው ቁጫጭ የባንክ አካውንት ከሰው ሊለያቸው: ከሚኖሩበት ማህበረሰብ ሊያራርቃቸው የሚችል በእጃቸው የያዙት ቦምብ ያረጉታል።

ክሪፕቶ ደግሞ የእብድ ዓለም ነው። ትጋትህን ካልተውከውና እምነትህን ካፀናኸው የሆነ ቀን ዋሌትህ ጭንቅላትህን የሚያሲዝ 'ኮና' ይዞ ልታገኘው ትችላለህ። እናማ ያኔ ያልታሰበው ሀብትህ ሳታስበው ሲመጣ ሰዋዊ ስሜትህና ተፈጥሮአዊ ማንነትህ ነድተውህ "ከኔ በላይ ንፋስ" የሚል ብኩን እንዳትሆንብኝ።

እናማ አደራ ብራዳ: ትሬዲንግ ማለት ላምቦ ላየ መፈናጠጥ እንዳልሆነ አውቀኸው ግባ። ያላሰብከው ርዝቅ ሲመጣም ከቶውን እንዳትቀየር Stay Humble & Hustle Hard. አሁንም Keep Hustling till you get enough of it. እመነኝ የሚጣፍጠውም እንደዛ ነው።😉😎


💚💛❤️
❤‍🔥45👍24👌6🙏3🔥2🕊2💯1
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael B.)
#Repost

✅90 በመቶ የሚሆነው ወደትሬዲንግ የሚገባ ትሬደር ውሸት የሆነ ቅዠታዊ ትልምን ይዞ ወደ ኢንዱስትሪው ይቀላቀላል።

🚨እውቀታቸውን ሳይሆን ገዛን የሚሉትን አይፎን ፕሮ ማክሳቸውን በሚያሾፉን: ቻርቱ ምን እንደሆነ ሳይሆን ከአጠገቡ  ሰራን የሚሉትን ርዝራዥ የብር ኖቶችን በሚያስከልሙን: የትሪያንግል ፓተርኑን ከማሳየት ይልቅ በቁሳዊ ስህበቶች የራሳቸው ትሪያንግል ውስጥ ለማስገባት በሚውተረተሩ የሶሻል ሚዲያ "hustler"ሮች የተሞላ ሴክተር መሆኑን ማመንም ግድ ይላል።

👀በዚህም ትሬዲንግ በነጫጭባኛው a "get-rich-quick" የሚባለ አይነት አቋራጭ መክበሪያ ዘዴ ነው የሚል እሳቤ በአብዛኛው አዲስ ትሬደር ላይ እንዲታይ ያደርጋል። አስተውሎ ለተመለከተው ጉዳዩ በተለይ ለእኛ አይነቱ ለመስኩ አዲስ ለሆነ ማህበረሰብ ሴክተሩን ከሚያቀነጭሩብን ሁነቶች አንዱ ሲሆን ለዘርፉም አንዱ ማነቆ ቫይረስ መሆኑ ልብ ይሏል።

🤷‍♂️እውነታው ግን:
ለአመታት በዘርፉ ተቆይቶም መበርታትን: updatedና ንቁ መሆንን የሚጠይቅ ስራ መሆኑን ማስታወሱ ነገሩ ቀላል ስላለመሆኑ ማሳያ ነው።

🗣እናማ ምን ልልህ ነው...

💊መጀመሪያ know how to master it by urself. Give it time to learn. የበላና የተማረ እንደሚባለው after all በጌሙ ሳትወድቅ ለመዝለቅ ከፈለክ ከብር በፊት ራስህን በእውቀት አካብት: አቋራጭነቱን አጉልተው ሊሞሉህ የሚጥሩትን ቁጫጭ ትሬደሮች ባላየ እለፋቸው: እመነኝ ካነበብክና ከጣርክ እጅህ ላይ ባለው ስልክ ብቻ አንተ እነሱን የማትሆንበት አንዳችም ምክንያት የለም። በተረፈ ጊዜ ከሰጠኸው: ፅናቱ ኖሮህ በዘላቂነት ስነልቦናህን ካበረታኸው how come አንተም ስኬታማ የማትሆነው ብራዳ?!🤔

🎊ቀኑ ቅዳሜ ነው: ወጡ በቂቤ ነው የሚሉላትን ቅዴ ተመኘሁላችሁ።✌️

💚💛❤️
🔥49👍32👌6❤‍🔥3🙏1💯1
Throw back Thursdays ... #RePost...

የማለዳ ወግ ከናቲ ጋር
📌 ጠያቂው: "ስማማ ብራዳ በክሪፕቶ አለም ብር ይሰራል ወይ?!"

እኔ: "አዎ! እንደፉርቱናህ ልኬት 1 ዶላር ወደሚሊዮኖች ሲቀየር ልታየው ትችላለህ: አረ ከዛም በላይ ጭንቅላት የሚያሲዝ ብር ሁላ ልትሰራ ትችላለህ።"

📌"ሊከሰርስ ይችላል ወይ?!"

"በአጭሩ 90 በመቶ የመክሰር ሪስክ ያለው ገበያ ነው።"🤔🙈

📌"ታዲያ እንዳልከስር ምን ላድርግ?!"

"እመነኝ በዚህ ሴክተር ውስጥ ተለውጠህ ሀብታም ስለመሆን: ላምበርጊኒ ስለመዘወር: ፎቆችን ስለመደርደር ወዘተ ከማለምህ በፊት ራስህ ላይ ኢንቨስት አድርግ። በደንብ ብላ: በስፖርት ራስህን ገንባ: ጤናህን ጠብቅ: እምነትህን አጥብቅ: ምናምን እና ከዛ ግን ከሁሉም በላይ በዚህ መስክ እውቀትህን አጎልበት። አንብብ: አሁንም አንብብ: አሁንም ድጋሚ አንብብ። የጥግረራህ: የኪሳራህ: የአንገት መድፋትህ: ተስፋ ያለመቁረጥ ትጋትህ: የመንፈሰ ጠንካራነትህ ሀምራዊ የድርጊቶች ድምር : ነገ ላምቦ እና ሮልስ ሮይሱ ላይ አንድ እጅህን ሰቅለህ በአንድ እጅህ ለመንዳትህ ከፈጣሪ ቀጥሎ ያሉ ብቸኛ ዋስትናዎችህ ናቸው። እናማ ምን ትጠብቃለህ... First you learn, then you erase the 'L' bruh."✌️🙏❤
👍32❤‍🔥3🔥2👌2💯2👏1🏆1
🕹#RePost
POV: #Bitcoin💰 እና ፀረ-ግሸበታዊ🔼 ባህሪው

📌የማይታበለውን ሀቅ በቁጥር ስናስደግፈው፡ በአሜሪካ አገር የሚገኙ ቤቶች አማካይ ዋጋ እኤአ ከ2016 ጀምሮ ባለው የ8 አመታት ጊዜ ውስጥ የዶላር ተመን ዋጋቸው በ50 በመቶ በመግሸብ በወቅቱ አንድ መለስተኛ የቤተሰብ ቤት ለመግዛት ከሚያስፈልገው $288,400 ዶላር ተነስቶ ዛሬ በአማካይ $434,700 ዶላር የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

💬በተቃራኒው፡ በተመሳሳይ ወቅት ቤቱን በ2016 በቢትኮይን እንግዛው ብንል ወደ 664 ቢትኮይኖች ያስፈልጉ የነበረ ሲሆን በቢትኮይን ዛሬ ላይ እንገብየው ብንል ከነበረበት የመሸጫ ዋጋ ወደ 99% ቀንሶ በ6.5 ቢትኮይኖች ብቻ የቤት ባለቤት መሆን ይቻላል።

🛍ይህን ልዩነት በአይኑ እየተመለከተ አሁንም ቢትኮይንን ለማወቅ የማይጥር፤ አሁንም ቢትኮይንን በፒራሚዳዊ ማጭበርበሪያነት የሚፈርጅ፤ አሁንም ቢትኮይን ውሸተኛ ገንዘብ እና የማረባ ህልም ነው ብሎ የሚመድብ ሰው መኖሩ ግርም ቢያሰኝም ይህን ሁነት ለመጀመሪያ ጊዜ የምታነቡ ቤተሰቦች: ስለቢትኮይንና ፊያት ገንዘብ በአንድ ፈርጅ ስለዋጋ ግሽበት ደግሞ በሌላኛው ፈርጅ የጠለቀ ምርምራችሁን ታደርጉ ዘንድ ወንድማዊ ምክራችን ሆኖ ይለፍልን ለማለት ወደድን።

CryptoTalk-ET™
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌14👍4❤‍🔥3🔥2😱2✍1👏1💯1
📣#RePost
☀️🙂የማለዳ ወግ ከናቲ ጋር - #044

እኔ ምልህ ብራዳ ትሬዲንግ ውስጥ ትልቁ ጠላትህ ማን እንደሆነ አስበኸው ታውቃለህ?!

❗️እውነት ለመናገር ወንድምአለም:  ጠላትህ አንተው ራስህ ነህ!! ለራስህ ያለህ ምልከታ ከፍታ ከሪያሊቲው አፈንግጦ ሲወጣ ራስህን በራስህ ላይ ጠላት ታረገዋለህ።

🤡እውነት ነው: በትሬዲንግ አለም እኔም: አንተም እሷም እሱም: ሁሉም ትክክል ስለመሆን ይውተረተራል።

😂በእያንዳንዱ ትሬዶቻችን ትክክል የመሆን አለመሆናችን እና የራስ-ወዳድነታችን ውቅር አፈንግጦ ይፈትነናል።

📌ይሁንና ራሳችንን የምናይበት የReality Check ላንሳልህማ...

✉️Ego በትሬዲንግ አለም በፍፁም ቦታ ሊሰጣቸው ከማይገቡ ጉዳዮች አንዱ ነው!!! በማንነት ስረመሰረትና ምንነት ላይ አደገኛ የሆነ የተፅእኖ ፈጣሪነት ባህሪያትም ያሉት ነው።

➡️ይህንን ሁነት ትክክለኛ የሆነ ዲሲፒሊንድ ትሬደር ያውቀዋል። የአንዷ ሙከራ አሸናፊነትህ አይደለም ቁምነገሩ።

በመጀመሪያ "ውጊያው"ን ይሁን "ጦርነቱ"ን ያሸነፍከው መለየት ቻል። ዞሮ ዞሮ ዋናው ጉዳይ ጦርነቱን የማሸነፍ ጉዳይ መሆኑንም አስታውስ። ዋናው የኪስህ ሁነት የተዛባ እና ለኦናነት ያደላ አይሁን የሚለው ብቻ ነው።


🛡በእነዚህ ሁላ ውጣውረዶች ግን: ካሉህ የትሬዲንግ ስብዕናዎች ሁሉ ዲሲፒሊንህ ቁመቱ ከሁሉም ረዝሞ ከተገኘ: ራስ ወዳድነትህ በየተወሰነ ጊዜው ግለሂሱን እየዋጠ ወደንቃተህሊናው የሚመለስ ከሆነ: ብሮስኪ በረራ ላይ ነህ: ... ኡቭታ ላይ ነህ: እመነኝ የምን ኢኮኖሚና ቢዝነስ ክላስ በራስህ የግል ጀት በራስ crew እየበረርክ ነው።

💡ዋናው ጉዳይ ልክ መሆን አለመሆንህ ወይም አሸናፊ መስለህ መታየት አይደለም። ዋናው ነገር ፍሉሱን ቀብሲስ ማረግህ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ዋናው ነገር በስተመጨረሻ በትርፍ መውጣትህ ላይ ያነጣጠረ ነው።

🔖In trading, the aim is not to be right. It's to be profitable.

CTE™ - Forex
CTE™ - Crypto
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍42🔥3👏3👌3❤‍🔥1✍1💯1
#Repost
💭የማለዳ ወግ ከናቲ ጋር

ብራዳ: ምናልባት ምናልባት ለዚህ የፋይናንስ ጡዘታዊ ዓለም አዲስ ከሆንክ የዛሬው የማለዳ ጭዌዬ ላንተ ነው።

🔖ብዙዎች የሀብት ማካበቻ ቁልፉ: በአንድ ለሊት ማማውን መርገጫ ክንፉ: በአንድ ሳምንት የላምበርጊኒ መሪ መጨበጫ መዳፉ እንደሆነ በየሶሻል ሚዲያው የሚስሉልህ የትሬዲንግም ሆነ የዲጂታል ፋይናንስ ዓለም ከሚታሰበው ሁሉ በላይ ግልባጭ ተቃራኒ መንታው ነው።

📌ይህን ስልህ በትሬዲንግ ወይም በክሪፕቶው ዓለም ብር አይሰራም ፈፅሞ ልልህ አይለደም። እዚህ ጋር ብነግርህ ላታምነኝ የምትችለውን መጠን በዓለም ዳርቻ ሁሉ በዚች ሰዓት በዚች ደቂቃ በዚህ መስክ ብዙ ሰዎች ብዙ ሚሊየኖችን እየሰሩ ነው።

📣ይልቅስ የአንተን ሰዋዊ ተፍጥሮ ስስ ጎን በመጠቀም በዚች ጡዘቷ በበዛበት ዓለም አቋራጭ ጎዳናውን የሚያሳይ ቁልፍ አለን በሚል ከአመንክዮ በራቀ ተልካሻ መሸወጃ እሳቤ በ3 ቀን ሸሚዝህን ብቻ አይደለም ህይወትህንም ቀይር የሚሉህ 'አዋቂ' ነን ባዮች ካንተ በሚቀበሏት ጨላ የራሳቸውን የተቆላለፈ ህይወት ሊከፍቱበት እንደሆነ እውቅ። ያንተን የሲግናልና የኮርስ ርዝራዥ 50 እና 100 ዶላር ለመለቃቀም ሲሉ ትርፋቱን ከመጠን በላይ አግዝፈው ሊያሾፉህ የሚጥሩትን 'ማዳመጫዬ ጥጥ ነው!' በሚለው የ90s ብሂል እለፋቸው።

⚠️እናማ አውቀህም ንቃ። ነቅተህም ተማር። ተምረህም ራስህን ለውጥ። ተለውጠህም ላይህፍህን ቀውጥ።

ብሮስኪ እና ምን ልልህ መሠለህ?!  . . በዚህ የኪስ ተኩላ በሞላበት መስክ አሰፍስፈው ሊበሉህ ከሚጠባበቁ ጥርሶች ለማምለጥ መጀመሪያ ራስህን በእውቀት: በዲሲፒሊንና በስነልቦና መገንባትህን አረጋግጥ። ራስህ ላይ ስራ: ስለምትገባበት መስክ አጥና። ስትገባ ምንጭ የመሰለህ ዘርፍ ውቅያኖስ ሆኖ እንዳያሰጥምህ ስጋ . . . ይኸው ነው።

ፏ ብልጭ ያለችዋን ጁም'ዓ በያላችሁበት።
💚💛❤️

#bitcoin #crypto #forex #signal #scam #pyschology
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤21👍8🔥2🎉2
ሰላም ጋይስ እንዴት ዋላችሁ፤

የ2025 የመጀመሪያ ወር ማለቂያ እንደመሆኑ አጠቃላይ የክሪፕቶ ገበያ ምን ሁነት ላይ እንዳለ የሚዳስስ በወቅታዊ የገበያ ሁነቶች ላይ ያተኮረው ቪዲዮ ከታች ባለው የትዊተር መስፈንጠሪያ በኩል ማግኘት እንደምትችሉ ለማስታወስ ወደድኩኝ። መረጃው ተደራሽነቱ ሰፍቶ ሌሎች ኢትዮጵያዊ እህት ወንድሞቻችን ይጠቀሙበት ዘንድ፤ እንደኮሚዩኒቲ ቤተሰብነታችሁም የፖስቱን ገፅታ ለመገንባት #Like #Repost እና #Bookmark ማድረግ እንዳትረሱ ስንልም በትህትና ለመጠየቅ ወደድን። መልካም ቀን በያላችሁበት።

https:// fxtwitter.com/CryptotalkEt/status/1884583578698236114
👍6
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
እንዴት አደራችሁ ጋይስ: እቺን ፅሁፍ ከልቤ ስለፃፍኳት በድጋሚ ላጋራችሁ ወደድኩ።

#RePost
📣የማለዳ ወግ ከናቲ ጋር

🗣️እሱ: "ስማማ ብራዳ፤ እኔ ምልህ ሲግናል የሚለቁ ቻናሎች ትጠቁመኛለህ?!🙏"

🗣️እኔ: "አዎ፡ ይቻላል። ላንተ እና ላንተ ብቻ የሚጠቅምህ፤ የሚያስብልህ፤ ሪስክህን ለመቀነስ የሚታትርልህ፤ ትርፍህን ለማጋበስ ደፋ ቀና የሚልልህን ሲግናል ሰጪ ነው የምጠቁምህ።"

❓ማን እንደሆነ ታውቃለህ?
✔️አንተ ነህ!!!

🔖ትላንት እንዳልኩህ ትምህርቱ በየኢንተርኔቱ በሞላበት የቴክኖሎጂ ዘመን ፈዘዝ ማለትህን ቀነስ አርገው፡ ፍጠንና ወጣትነትህን ተጠቀምባት፤ እውቀትን ቅሰምባትና እውቀቱን ለቀሪው ህይወትህ መሰረት ጣልበት። እናማ አሳ ማስረጉን አስተምርሀለው የሚልህ እንጂ ሁሌ ጉላሹን አቀርብልሀለው የሚልህን አትስማው፤ የትሬዲንግን እሳቤ እጥብ አድርጌ አስበላሀለው  የሚልህን እንጂ ሲግናል እሰጥሀለው፤ ልጥጥም አረግሀለው የሚልህን ጆሮ ዳባ ልበስ በለው። ነገ እሱ አጠገብህ ባይኖርስ ብለህ ለአንድ አፍታ አስብ። ተምረህ ምክንያት ላይ ተመስርተህ ለራስህ የራስህ ሲግናል ሰጪ መሆንህን በተግባር አሳየው።

⚠️እናማ ዛሬም የምልህ አንብብ፤ አሁንም አንብብ፤ አሁንም ድጋሚ አንብብ ነው።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2❤20🔥3