Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹
እንደአገር ይቀረናል ስንል በምክንያት ነው። አሁንም ሰሚ ካለን መንግስት ሰፊ እና ተደራሽ ከሆኑት መሰል የማስ ሚዲያ መስኮቶቹ ጀምሮ በእያንዳንዱ ተቋሞቹ የሚሰሩ በእያንዳንዱ እርከን ላይ የሚገኙ ሰራተኞቹን በተለይ በብሎክቼይን እና ክሪፕቶከረንሲ ዙሪያ ያሉ እውቀቶችን ማደርጀት፤ ማሰልጠን እና ማብቃት አለበት።
እንደው ለመሆኑ ማንም ቦታ ሰቶ አያየውም እንጂ፤ ሊያውም ብዙ ቦታዎች ይዳረስ ዘንድ ጥቅም ላይ የሚውልን የሀሽታግ አጠቃቀም ሊያውም በመንግስት ባለቤትነት በሚተዳደር እና አገሪቷን በሚወክል ተቋም ላይ #cryptocurrency መባል ሲገባው #criptocurrency ተብሎ ለህዝብ ይፋ ሲሆን ምን ደረጃ ላይ እንደሆንን አንዱ ማሳያ ሊሆነን ይችላል። አይ ናቲ አካበድክ እንዳልባል ደግሞ ዋናው ምክንያቴ በዚህ ልክ ስለጉዳዩ በመወያየት ሂደት መጀመሪያ የምናገኘውን የእሳቤውን ስፔሊንግ በትክክል መፃፍ ካልቻልን ስለብሎክቼይን ውስብስብ እሳቤዎች ሊሰሩ የሚችሉ ዘገባዎችን ደግሞ መሳል ነው።
ሌላው ከዚሁ ጋር ተያይዞ መንግስት በአንድ በኩል በዋነኛ የመገናኛ ብዙሀን ተቋሙ በሆነው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል በስም አይጠራ እንጂ ስለብላክ ማርኬቱ በሀላል ከማውራት ጀምሮ የተለያዩ የክሪፕቶ ጥቅማጥቅሞችን ሲያቀርብልን በሌላ በኩል ደግሞ ብሄራዊ ባንኩና የመረጃ ደህንነት ድርጅቱ ያላቸው ለጊዜውም ቢሆን እያሳዩት ያሉት ፀረ ቢትኮይን/ክሪፕቶ እሳቤ ደግሞ እውቀቱ የሌለውን ብቻ ሳይሆን ያለውንም ክፍል የሚያወዛግብ አለፍ ሲልም ጠንካራ የብሬን ድሬን ችግርን ሊያመጣ የሚችል ነውና መቀላቀላችን ላይቀር በተለይ ከህግ ማእቀፍ ጋር ተያይዞ ያለውን ሁነት በተቻለ ፍጥነት አጥርቶ ቁርጣችንን ቢያሳውቀን ባይ ነኝ።
ትላንት በኢቲቪ የተላለፈውን "የክሪፕቶ ቴክኖሎጂ እና በኢትዮጵያ ያለውን እንቅስቃሴ" የሚል ርእስ ያለውን አጠር ያለ ዘጋቢ ቪዲዮ ለማየት የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የዩቲዩብ መስፈንጠሪያ ትመለከቱት ዘንድ ጋበዝኳችሁ።
https://www.youtube.com/watch?v=QOEGd2iL6Vk

❤7