Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.23K photos
40 videos
6 files
642 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
Ministry of Education and Arizona State University Explore New Areas of Collaboration
---------------------------- //-----------------------
(October 9/2016) H.E. Ato Kora Tushune, State Minister for Higher Education and Development Sector at the Ministry of Education, held discussions with Dr. Kristin Lord, Vice President for Global Strategy and Engagement at Arizona State University (ASU), on strengthening collaboration and expanding innovative learning opportunities in Ethiopia’s higher education sector.
The discussion explored a range of potential areas of cooperation, including the establishment and strengthening of innovation and incubation centers, entrepreneurship development, employment-oriented initiatives through the Center for Entrepreneurship and Employment Development (CEED), and the advancement of Educational Technology (EdTech). Use this link for the detail: https://web.facebook.com/share/p/17j3cubDVp/
ማስታወቂያ
 
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ
 
ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሂደቱን እያከናወነ ይገኛል።
 
ሚኒስቴሩ በትምህርት ቤቶቹ የሚገኙ ተጨማሪ ክፍት ቦታዎችን በመጠቀም ተጨማሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ዕድል አመቻችቷል።
 
በመሆኑም በትምህርት ቤቶቹ ባሉ ክፍት ቦታዎች ተመድባችሁ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው የምዝገባ ሊንክ በመግባት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
 
የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት
የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply
                  የትምህርት ሚኒስቴር
📢 ማስታወቂያ

📌 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡
በጊዜያዊ ምደባ ሂደቱ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ ተጠናቆ ምላሽ የተሰጠ በመሆኑ፣ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ-ግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ ትምህርታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።

እንዲሁም የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሄዳቹህ በፊት በዚህ ማስፈንጠሪያ  በመግባት https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ እንድታረጋግጡ ይሁን

📌 አዲስ ተማሪዎች፡
የምደባ ቦታችሁን https://student.ethernet.edu.et/view-placement/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፦ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ) ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ
የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ማጠናከር የገጠሩንናና የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የመረጃና የትምህርት ተደራሽነት እንደሚያሳድግ ተገለጸ፤

---------------------- // -------------------

(ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም) የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ተገቢውን ማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጡበት ሁኔታ በመዲናችን አዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች የቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔትና የህትመት ሚዲያዎች ተደራሽ ባልሆኑባቸው እንዲሁም የቋንቋ ውስንነት ባላቸው የገጠርና አርብቶ አደር አካባቢዎች ዋና የመረጃ ምንጭ በመሆናቸው፣ አቅማቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል።


ዩኔስኮ ባዘጋጀው መድርክ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ከማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር ለሚተገብሩት ፕሮጀክት ውጤታማነት ከጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ለወጣቶች የሚሰጡትን ትምህርታዊ አገልግሎት ጥራት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።


በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሐፊ አቶ ዓለሙ ጌታሁን፤ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ለገጠሩና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ያላቸውን ወሳኝ ፋይዳ አብራርተዋል።
አክለውም የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ወላጆች፣ መምህራን፣ የሃይማኖትና የማህበረሰብ መሪዎች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የአካባቢው ባለሥልጣናት በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሬዲዮ ጣቢያዎቹ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18XdzZ9wRh/
📢 የማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ መወሰኑን እንገልጻለን።
📝 የፈተናው ዝርዝር መረጃ
📅 የፈተናው ቀን፦ መጪው ቅዳሜ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም
⏰ የመግቢያ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
📍 የፈተና ቦታ፦ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን (Online) በተሰጠባቸው የፈተና ማዕከላት
⚠️ ማሳሰቢያ፦
ተማሪዎች ፈተናውን አልፈው በሚመደቡባቸው የትምህርት ቤቶች ለመማር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታነት የተመደቡት አዲስ አመራሮች የስራ ርክክብ አደረጉ፤

----------------------- // -------------------

(ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታነት የተመደቡት ዶ/ር ቶላ በሪሶ እና ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ከቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታዎች የስራ ርክክብ አድርገዋል።

በዚህም የቀድሞ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አዲስ ለተመደቡት ዶ/ር ቶላ በሪሶ መልካም የስራ ዘመን በመመኘት የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፤
በተመሳሳይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ኮራ ጡሹኔ በዘርፉ አዲስ ለተመደቡት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ የስራ ርክክብ አድርገዋል።

በሥራ ርክክብ መድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፉት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች የማይቀለበሱበት ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን ገልጸው የቀድሞ አመራሮች ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። አዲስ የተመደቡት አመራሮችም ያላቸውን ሰፊ ልምድ በመጠቀም ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ስኬትና ቀጣይነት ትልቅ አቅም እንደሚሆኑ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/19FKeHEc1A/
📢 የመግቢያ ፈተና ጥሪ ማስታወቂያ


ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝጋቢዎች በሙሉ


የትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባሉት ክፍት ቦታዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ተመዝግባችሁ ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡


የመግቢያ ፈተናው ነገ ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ የሚሰጥ መሆኑን ቀደም ብለው ማሳወቃችን ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚቀርባችሁ የመፈተኛ ማዕከል በአካል በመገኘት ፈተናችሁን እንድትወስዱ እናሳስባለን።


📌 ማሳሰቢያ፦

የፈተና መስጫ ማዕከላትን በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም መረጃ ከፈለጋችሁ የየክልሎቻችሁን ትምህርት ቢሮ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴ