የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ብቃትና ተነሳሽነት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አስገነዘቡ፤
--------------------------------------------------
(ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም) ከመጪው ሐምሌ 28 ጀምሮ ከ84 ሺ በላይ ለሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገለጸ።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ የተጀመረውን የአሰልጣኞች ስልጠና ሲከፍቱ እንደገለጹት የመምህራንና የትምህርት አመራሮችን ብቃትና ተነሳሽነት ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።
መምህርነት ዜጋን በዕውቀት፣ በክህሎትና በሥነምግባር በማነጽ ተምህርት የሚያስጨብጥና ዜጎች ችግር ፈቺ ፣ተመራማሪ፣ ሀገር ተረካቢና ገንቢ እንዲሆኑ የሚቀርጽ ሙያ መሆኑን አስገንዝበዋል።
መምህርነት ቅድመ ሁኔታዎች ሳይገድቡት የወላጅነትና የባለአደራነት ሚና የሚወጣ የሙያዎች ሁሉ ቁንጮ በመሆኑ መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡና የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል የትምህርት ቤት አመራሮቾ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/15wBcpYb7M/

የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅርቦት ለማሻሻል አማራጭ የመምህራን ትምህርት ፕሮግራም በመጪው የትምህርት ዘመን እንደሚተገበር ተገለጸ።
----------------------------------------------------------
(ሐምሌ 17/2017 ዓ. ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅርቦት ለማሻሻል በ2018 ዓ.ም አማራጭ የመምህራን ትምህርት ፕሮግራም በ6 ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ ይደረጋል።
የመርሃ ግብሩ ዓላማ የመምህራንን አጠቃላይ አቅርቦት በማሻሻል ረገድ የሚስተዋሉ እጥረቶችና የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።
በአማራጭ የመምህራን የትምህርት መርሃ ግብሩ ከምሁራን ጋር የተመከረበት ፣ በየደረጃው የሚገኙ መምህራንና ሌሎችም የዘርፉ ባለድርሻዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉበትና በውይይት ከዳበረ በኋላ መጽደቁን አብራርተዋል።
አማራጭ የመምህራን ትምህርት መርሃ ግብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲተገበር ከአሁን በፊት በትምህርት ዙሪያ በትኩረት እንዲሰሩ በተለዩ 6 ዩኒቨርስቲዎችና ክልሎች መላኩን ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1B7oDqeZha/

የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ የበጎ ተግባራት መገለጫ በተለይም መተጋገዝን፣ መደጋገፍን፣ መረዳዳትንና መከባበር የበለጠ ለማላቅ እድል የሚሰጥ ነው፤ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ፤ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በጋምቤላ ክልል ተገኝተው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን አስጀምረዋል።
-----------------------------------------------------
(ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ፣ ተጠሪ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በጋምቤላ ክልል ተገኝተው አስጀምረዋል።
በክረምት የበጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ በሀገራችን ከለውጡ ወዲህ የሀገርን ገጽታ የቀየሩ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን በተለይም የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቅሰው ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተጋች ባለች ሀገር እርስ በርስ መተጋገዝና መደጋገፍ ይገባናል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/19AsKQLJco/

ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ያላትን ልምድ አካፈለች።
---------------------------------------------------
(ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም አተገባበር ያላትን ልምድና የመንግስትን ቁርጠኝነት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቅርበዋል።
የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲ ፍሬም ዎርክ በማውጣት ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ በማድረግ የአካባቢ ልማትና ግብርናን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል።
በዚህ የሀገር በቀል የት/ቤት ምገባ ፕሮግራም መንግስት 6.3 ቢሊየን ብር መመደቡንና የማህበረሰቡ ድጋፍ ደግሞ 9.8 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸው የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ ደግሞ 1.3 ቢሊየን መሆኑን አብራርተዋል።
ይህም በኢትዮጵያ ለት/ቤት ምገባ 90 በመቶ የሚደርሰው በጀት በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የሚሸፈን መሆኑን ገልጸው ተግባሩ የመንግስትንና የማህበረሰቡን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የምገባ ፕሮግራሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድረገው እንዲማሩ ከማድረጉ ባለፈ፤ ጤንነታቸው ተጠብቆ ትምህርታቸው ሳይቋረጥ እንዲማሩ ማድረግ ያስቻለ ተግባር ስለመሆኑም ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከአለም የትምህርት ቤት ምግብ ጥምረት (School Meal Coalition) እና ከአለም የምግብ ፕሮግራም ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ትምህርት ለሀገር እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ የዘርፍ ባለሙያዎች ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ፣ የተቋሙን ተልዕኮ በሚገባ የሚፈጽሙና የሚያስፈጽሙ ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳሰቡ።
============================
(ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በሚኒስቴሩ እና በሀገራችን የ2017 እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የልማት ዕቅድ እንዲሁም በተቋሙ እየተካሄዱ ባሉ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ትምህርት ለሁለንተናዊ እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ፣ዘመናዊና የተቋሙን ተልዕኮ በሚገባ የሚፈጽሙ አርኣያነት ያላቸው ሠራተኞች ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ በቅንነትና በብቃት እንዲወጡ ምቹ የሥራ አካባቢ መኖር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም ለማሳካት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/173hcvtJbe/