በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትረው ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
-------------------------- // ----------------------------
(ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም) የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር፣የማህበረሰብ ጉድኝትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተካሂዷል፡፡
በዚሁ ጊዜ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች ወደ ገበያ ሲገቡ commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትሪው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡
አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ፈጠራና ተቋማቱ በቅንጅትና በትብብር መሥራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የየራሳቸውን የንግድ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ማበልጸጊያ (incubation centers) ማዕከላት ያላቋቋሙ ተቋማት በአፋጣኝ አቋቁመው ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1DfgngLVJp/

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ፡፡
=======================
(ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበሰውን ብሄራዊ የሠንደቅ አላማ ቀንን አክብረዋል፡፡
በክበረ-በዓሉ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያና መሠባሠቢያ መሆኑ አንስተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሀገራችንን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ከፍታ አስጠብቀን ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ አደራ በዚህ ትውልድ ላይ የተጣለ መሆኑን አመላክተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘይ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17CNpuNiDc/

የከፍተኛ ትምህርት ድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
----------------------- // ----------------------
(ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በመሰጠት ላይ ነው።
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) የመግቢያ ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ፣ የመከላከያና የፖሊሲ ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ በ53 የፈተና ማዕከላት መሆኑን ገልጸዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ለሚገኘው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመቀጠል የተዘጋጁ 29ሺ 248 ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸውን ዶክተር ኢዶሳ ተናግረዋል፡፡ ሃላፊው አክለውም የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ጠቁመው በቀጣይም በጥር ወር ይሰጣል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ የድህረ ምረቃ ፈተና አስተባባሪዎች በበኩላቸው በዩኒቨርስቲዎቹ እየተሰጠ የሚገኘው የድህረ ምረቃ ፈተና ያለምንም ችግር በመሰጠት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CJH9ceL1W/