Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በጊዚያዊነት ለመቀበል እያደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ተዘዋውረው ተመለከቱ ።
-------------------------- // -------------------------

(ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚንስትሩ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን በጋምቤላ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ለመቀበል እያደረገ ያለውን ቅድመ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያስገነባቸው ባሉ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር ከመላ ሀገሪቱ አወዳድሮ የተቀበላቸውና በጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎች በጊዜያዊነት በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለማስተማር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ ተማሪዎች የመማር ማስተማር አገልግሎት ያዘጋጃቸውን የተማሪዎች ቤተ-መጽሐፍት፣ የኮምፒውተር ክፍል፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ እና የመኝታ ክፍሎች እና ሌሎችንም አይተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሚንስትሩ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙትን ስማርት እና ኮንፈረንስ ክፍሎች እንዲሁም የኬሚስትሪና የማይክሮ ባዮሎጂ ቤተ-ሙከራዎችን የጎበኙ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ጥሩ መሻሻሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርታቸው የላቁና ብቁ ተወዳሪ እንዲሁም ወደፊት የሀገር መሪ የሚሆኑ ልጆችን ለማፍራት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያስገነባ ሲሆን በአምስቱ በቅርቡ የመማር ማስተማር ሥራ የሚጀመር ይሆናል።
ትምህርት ሚኒስትሩ በጋምቤላ ክልል እየተገነባ የሚገኘውን ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበት ደረጃ ተመለከቱ።

-----------------------//---------------------------
(ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በጋምቤላ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸው ወቅት እንዳሉት የሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ግንባታው ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም የደረሰበት ደረጃ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው በዚሁ ፍጥነት ጥራቱን የጠበቀና ለተማሪዎች አመቺ ተደርጎ ሊገነባ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁሉም በሀገራችን የሚኖሩ ልጆች በተቻለ መጠን ተመጣጣኝ ትምህርት፣ እውቀትና ክህሎት ማግኘት አለባቸው ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በበኩላቸው የሞደል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ከታሰበው በላይ በፍጥነት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅም ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።


ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን እየገነባ የሚገኘው ናይል ሌችዌ ኮንስትራክሽን እና ውሃ ስራዎች ድርጅት የፕሮጀክቱ ግንባታ 42.1% እንደደረሰ ለከፍተኛ አመራሮቹ ገለጻ አድርገዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1CsqXgWrJS/
የማጠናከሪያ ትምህር በዕቅድና በትኩረት እንዲመራ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
-------------------- // --------------------
‎(ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በአጠቃላይ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በተለይም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትን በዕቅድና በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ወላጆች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ጊዚያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል።

‎የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
‎
‎የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራትና መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ(ዶ/ር) የማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ መነሻ ስትራቴጂ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን የተያዘው ግብ እንዲሳካ ከወዲሁ የዕቅድ ክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።
‎
‎በበይነ-መረብ በተደረገው በዚሁ ውይይት ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን ፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ ጋር ተወያዩ።
-------------------------- // -------------------------

(ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጲያ የUNFPA ተወካይ Mr. Sk Kouameን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ የሆኑት Mr. Sk Kouame UNFPA በሴቶች ትምህርት በተለይም ለሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን በማቅረብ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ይህንን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለክቡር ሚኒስትሩ አብራርተውላቸዋል።

UNFPA ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሌሎች ጋር በመተባበር የሴቶችን የትምህርት ሁኔታ በማመቻቸት ረገድ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉም ገልጸውላቸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በበኩላቸው UNFPA ውስን በሆነ መልኩ ለሴት ተማሪዎች ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

አክለውም በቀጣይ ከእንዲህ ዓይነት ውስን ድጋፎች ተላቆ በራስ አቅም የሴቶችን ንጽህና መጠበቂያ በማምረት ለኢትዮጵያም ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም ሥራ መስራት እንደሚገባ ለካንትሪ ዳይሬክተሩ አብራርተውላቸዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘገጃ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

--------------------------- // -----------------

(ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘጋጃ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድና ተዛማጅ ጉዳዬች ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ባጋሩት ሀሳብ እየተቀየረ ያለውን የዓለም ጂኦፓለቲክስ ቀድሞ በመረዳት የሀገራችንን ስትራቴጂያዊ አካሄድና ብሄራዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝግጁነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ብሄራዊ ጥቅሞች ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ልዩነቶቾን በማጉላት መደነቃቀፍን የሚፈጥሩ አጀንዳዎች፣አመለካከቶችና ሌሎች ፈተናዎችን በማስወገድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

ሀገር ያለ ብሔራዊ ጥቅም ልትቀጥል እንደማትችል አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በጥልቀት መረዳት እንደሚገባም አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BhwxE7Qv9/