Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የማጠናከሪያ ትምህር በዕቅድና በትኩረት እንዲመራ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
-------------------- // --------------------
‎(ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በአጠቃላይ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በተለይም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትን በዕቅድና በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ወላጆች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ጊዚያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል።

‎የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
‎
‎የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራትና መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ(ዶ/ር) የማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ መነሻ ስትራቴጂ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን የተያዘው ግብ እንዲሳካ ከወዲሁ የዕቅድ ክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።
‎
‎በበይነ-መረብ በተደረገው በዚሁ ውይይት ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን ፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ ጋር ተወያዩ።
-------------------------- // -------------------------

(ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጲያ የUNFPA ተወካይ Mr. Sk Kouameን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ የሆኑት Mr. Sk Kouame UNFPA በሴቶች ትምህርት በተለይም ለሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን በማቅረብ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ይህንን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለክቡር ሚኒስትሩ አብራርተውላቸዋል።

UNFPA ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሌሎች ጋር በመተባበር የሴቶችን የትምህርት ሁኔታ በማመቻቸት ረገድ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉም ገልጸውላቸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በበኩላቸው UNFPA ውስን በሆነ መልኩ ለሴት ተማሪዎች ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

አክለውም በቀጣይ ከእንዲህ ዓይነት ውስን ድጋፎች ተላቆ በራስ አቅም የሴቶችን ንጽህና መጠበቂያ በማምረት ለኢትዮጵያም ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም ሥራ መስራት እንደሚገባ ለካንትሪ ዳይሬክተሩ አብራርተውላቸዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘገጃ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

--------------------------- // -----------------

(ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘጋጃ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድና ተዛማጅ ጉዳዬች ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ባጋሩት ሀሳብ እየተቀየረ ያለውን የዓለም ጂኦፓለቲክስ ቀድሞ በመረዳት የሀገራችንን ስትራቴጂያዊ አካሄድና ብሄራዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝግጁነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ብሄራዊ ጥቅሞች ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ልዩነቶቾን በማጉላት መደነቃቀፍን የሚፈጥሩ አጀንዳዎች፣አመለካከቶችና ሌሎች ፈተናዎችን በማስወገድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

ሀገር ያለ ብሔራዊ ጥቅም ልትቀጥል እንደማትችል አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በጥልቀት መረዳት እንደሚገባም አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BhwxE7Qv9/
በኢትዮጵያና በቻይና መንግስታት መካከል በትምህርት መስክ ያለው የትብብር ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለጸ፤
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከቻይናዋ ሻንዢ ግዛት የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

---------------------------- // -------------------------

(ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ከቻይናዋ ሻንዢ ግዛት ምክትል ገዢ ዋንግ ዢአዎ የተመራ ልዑካን ቡድን ባነጋገሩበት ወቅት እንደገለጹት በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነት መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የትብብር ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ ወደ ስትራጂካው አጋርነት መሸጋገሩንም ክቡር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

የቻይና የስልጣኔ ማዕከል የሆነችው የሻንዢ ግዛት ከኢትዮጵያ ጋር በባቡር ፣ በቴክኒክና ሙያ እና በሌሎችም መስኮች የትብብር ግንኙነት እንዳላትና ትምህርት ሚኒስቴር ከግዛቲቱ ጋር ያለውን ትብብር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍም ማጠናከር እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን መከታተል ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/19SrbEu4uh/
በትምህርት ዘርፉ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የቅሬታ አፈታት ስርዓቶች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች እና የቅሬታ አፈታት ስራ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
--------------------- // ------------------------

(ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም) ውይይቱ በትምህርቱ ዘርፉ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የቅሬታ አፈታት አሰራር ስርዓቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን የተዘረጉ የአደረጃጀትና የአሠራር ስርዓቶች በትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የቀረበውን የውይይት መነሻ ሀሳብ በመንተራስ ሀሳባቸውን ያጋሩት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በየደረጃው ባለ መዋቅር የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና ቅሬታዎችን ለመፍታት የተለያዩ አደረጃጀቶችና የአሰራር ስርዓቶችን ወደ ተግባር በማስገባት ተገልጋዬችን ከዕንግልት፣ ከተጨማሪ የጊዜና ገንዘብ ወጪ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።

አሳታፊነት ከማጠናከርና ከማረጋገጥ አኳያ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በጋራ የማቀድ፣ የመከታተል፣ የመገምገምና ግብረ መልስ የመስጠት ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ክብርት ወ/ሮ አየለች አያይዘው ገልጸዋል ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1S9xnYtrzB/