የት/ቤት ምገባን በማጠናከር የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ማሳደግ ይገባል፤ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይዎት
--------------------- // ------------------
(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) በ34ኛው የትምህርት ጉባኤ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይዎት የት/ቤት ምገባን በማጠናከር የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
ፕ/ር ክንደያ አክለውም የትምህርት ማህበረሰቡ በ “ትምህርት ለትውልድ“ያሳየውን የላቀ ተሳትፎ በአዳሪ እና በሞዴል ት/ቤቶች ግንባታም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የሪፎርም ስራዎቻችንና አበይት ስራዎቻችንን በሚገባ ለይተን በዚህ የትምህርት ዘመን ውጤት ሊያመጡ በሚችል መልኩ መተግባር እንደሚገባም ተናገረዋል።

የትምህርት ስርዓቱን ከዓለም የአየር ንብረት ፣ የቴክኖሎጂ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቃኘት እንደሚገባ ተመላከተ።
34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
--------------------------- // -----------------------
(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የትምህርቱን ሥራ ከአየር ንብረት ፣ ቴክኖሎጂና ከዓለም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቃኘትና መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ይህ ጊዜ ለውጦችን በመቋቋም ወደ እድል የሚቀይሩ ፣ አገራቸውን የሚወዱና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ዜጎችን ለማፍራት በትጋት የምንሰራበት ወቅት መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።
በመሆኑም በየደረጃው ያሉ መምምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት አይነት የበቁ ሆነው በመገኘት ሙያቸውን ሊያሳድጉና ሊያስከብሩ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተቋቋሙበት አላማ ቅድሚያ በመስጠት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የአካል ጉዳተኞችን የመማር ማስተማር ከባቢ ምቹ ለማድረግ አገሪቱ ባላት አቅም ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክተዋል።
በበኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፍትሃዊና “ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪቃል የተካሄደው 34ኛው የትምህርት ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣትም ተጠናቋል።

ማስታወቂያ፤
በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ለመወዳደር የተመዘገባችሁና እና ለቃለ መጠይቅ የተመረጣችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፤
ቃለ መጠይቁ የሚደረገው እሁድ ሕዳር 07/2018 ዓ.ም ሲሆን በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ እንድትገኙ እያሳወቅን ስትመጡ፤
ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናል እና ኮፒ፣
ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የአንድ አመት ልዩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ስልጠና ሰርትፍኬት፣
የሙያ ፍቃድ እና እድሳት ሰርትፍኬት፣
በመምህርነት ተገቢነት ያለው የስራ ልምድ ማስረጃ የሚገልጽ ደብዳቤ መያዝ የሚያስፈልግ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
ለቃለ መጠይቅ የተመረጣችሁ መምህራን ስም ዝርዝር ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዟል ፡፡

ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎችና ደንብ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ በ3 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት አመራር፣ አደረጃጀት የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ ረቂቅ መመሪያ፣( ሊንክ = https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScdrHGMOV3gb_aOhiFZsxGU1JAB178bvAiDRufSIPFTIfrj_g/viewform)
2. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ረቂቅ ደንብ ፤ ( ሊንክ = https://forms.gle/LpwGdAu7mBYRUNNU6)
3. የአጠቃላይ ትምህርት የውስጥ ኢንስፔክሽን እና ሱፐርቪዥን አተገባበር ረቂቅ መመሪያ (ሊንክ = https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdoOaNWgbbPX8M2dEpqcBFOlLBefpFtzeKYyu1HOxEiycCjg/viewform?usp=sharing&ouid=111388231034755887607) አዘጋጅቷል።
በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች በመጫን፤
በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር

Google Docs
የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት አመራር፣አደረጃጀት የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ ቁጥር----/2017(ረቂቅ) ዶክመንት ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ(Link) ይጫኑ እና ያሎትን አስተያየት…
በኢትዮጵያ እና እስራኤል መካከል ያለውን የትምህርትና ስልጠና ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።
------------------ // ------------------
(ሕዳር 04/2018 ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑትን ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ ጋር ተወያይተዋል።
በዚሁ ጊዜ ሁለቱ ወገኖች በነበራቸው ውይይት ወጣቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የትምህርትና ስልጠና ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ የመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በተለይም የመምህራንና የተማሪዎች አቅምን መገንባት በሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ላይ ከእስራኤል መንግስትና ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ(ዶ/ር) በበኩላቸው በኢትዮጵያና በእስራኤል መንግስታትና ህዝብ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ ወዳጅነት መኖሩን አንስተው ይህንን አጠናክሮ በመቀጠል በሁለቱ ሀገራት መካከል በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።
በውይይቱ ላይ ዩኒስትሪም (Unistream) የተባለ የእስራኤል ድርጅት ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑም ተጠቅሷል።