Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመጥን አሰራርና አደረጃጀት እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
------------------------------- // ------------------------
‎
‎(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) የጅማ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ጌንት የ25 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎለታል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመጥናቸው አሰራርና አደረጃጀት እንዲኖር እየተሰራ ይገኛል።
‎
‎የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች እንደሀገር እሰከ 80 በመቶ የሚደርስ የክሊኒካል አገልግሎት ጫና እንዳለባቸው የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታትም አየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
‎
‎የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ለዩኒቨርስቲው ህክምና ማዕከል የተደረገው የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ ሆስፒታሉ የተሻለ የህክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችለው ጠቅሰዋል።
‎
‎ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የጅማ ዩኒቨርስቲን ልዩ ልዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጂግጂጋ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላለፉ።
------------------------------ // ----------------------------

(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር ትልቅ ተስፋ ከተጣለባቸው የፌደራል አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የጂግጂጋ የፌዴራል አዳሪ ትምህርት ቤት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚንስቴር አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ለአጠቃላይ የት/ቤቱ ማህበረሰብ መርሃ ግብሩን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም መንግስት የትምህርት ጥራት፣ አግባብነትና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታዋ በዚህ የፌደራል አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገኛችሁ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ታሪካዊ በሆነው መርሃ ግብር የመጀመሪያዎቹ ተዋንያን በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BfF1xT1aR/
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የወደፊቱ አገር ተረካቢዎች ሁለንተናዊ ሰብዕና የሚገነባባቸው ተቋማት መሆናቸው ተመላከተ፤
የቦንጋ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
------------------------ // ----------------------
‎
‎(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) በአዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ እንደገለጹት አዳሪ ትምህርት ቤቶች የነገዎቹ አገር ተረካቢዎች ሁለንተናዊ ስብዕና የሚገነባባቸው ቦታዎች ናቸው።
‎
‎ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጥራት ያለው ትምህርት ከማቅረብ ጎን ለጎን በጥሩ ባህሪ የተገነቡ ፣ሥነምግባር የተላበሱና በሙያቸው የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ዜጎች የሚፈሩባቸው ማዕከላት መሆናቸውንም ክቡር አቶ ኮራ አስገንዝበዋል።
‎
‎የትምህርት ቤቶች ትኩረት በአብዛኛው የአካዳሚክ ዕውቀትን በማስተላለፍ ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከንድፈ ሀሳብ እውቀት ባሻገር የተማሩትን ወደ ተግባር በመለወጥ የማህበረሰቡን ችግር መፍታት የሚችሉ ዜጎችን ማፍራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግነት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BgVEuwXNA/
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቡኢ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
----------------------------- // -------------------------

(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) መርሃ ግብሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል(ዶ/ር) እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ አስጀምረውታል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ስርዓቱ የገጠመንን የሞራል ስብራት ለማስተካከል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ሀገር በፍጥነት ማደግ ከፈለግን በትምህርት ላይ ትኩረት አድርገን መሥራት አለብን፤ በዚህም ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት በሀሉም አካባቢ ለመሥጠት በኢትዮጵያ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በርካታ ሀብት በማሰባሰብ የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገናና የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1GDF3gQYaW/