Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትምህርት ቤቶች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑ ተገልጸ።

……………………………………….. // -------------------------

(ጥር 15/2018 ዓ.ም) በ2018 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትምህርት ቤቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን ተገልጿል።

በተለይም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ታስቦ በመከናወን ላይ ያለውና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም አካባቢ እየተተገበረ ያለው የማጠናከሪያ ትምህርት ተስፋ ሰጪ መሆኑም ተመላክቷል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘውና ባለውፈው ዓመት በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው የመቂቾ ሚሊኒየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ፈቱዲን ኑሪ እንደገለጹት ትምህርት ቤቱ በዚህ ዓመትም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከማሟላት ባለፈ፣ የጥናት ክፍለጊዜዎች በእቅድ እንዲመሩ በማድረግ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ቆይታቸው ትኩረታቸውን በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲሆን ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1C73QcoJ59/
ማስታወቂያ

ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ባስጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ጥቂት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎችን (አሁን 9ኛ ክፍል ገብተው እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች መካከል በማወዳደር) ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ መግለጹ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የምዝገባ ጊዜው እንዲጨመር አንዳንድ ክልልሎች በጠየቁት መሰረት እስከ ጥር 20/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑነ እየገለጽን በአሉን ውስን ክፍት ቦታዎች ተመዝግባችሁ ለመማርና የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች https://sbs.moe.gov.et/apply በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በድጋሜ እንገልጻለን።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
---------------------------- //------------------------------

‎(ጥር 15/2018 ዓ.ም) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ መምህራን በስርዓተ ትምህርቱ መሠረት ስለሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል ለአቅም ማጎልበት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱንም ጠቁመዋል።

‎የትምህርት ቤቶች ግብዓቶችን ከማሟላት አንጻር በተለይም በራስ አቅም መሟላት የሚችሉ የትምህርት መርጃ ግብዓቶችን በአግባቡ ለማሟላት የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውንም አቶ ሱልጣን አስረድተዋል።

‎በከተማ አሰተዳደሩ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብርም ተጨማሪ የመምህራን ማረፊያዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተሙከራዎች፣ ቤተመጽሐፍቶች የመገንባትና የማደራጀት ስራዎች መከናወናቸውንም ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/1JrD9dEVPa/
ጥርበ2018 አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በክልሉ ሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
---------------------------- // ---------------------------
‎
‎(ጥር 19/2018 ዓ.ም) የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለጹት በክልሉ በ2017 አገር አቀፍ ፈተና የተገኘውን ውጤት የበለጠ ከፍ ለማድረግ በሁሉም የክልሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
‎
‎በክልሉ ባሉ በሁሉም የግልና የመንግስትም ትምህርት ቤቶች አደረጃጀት በመፍጠር ተማሪዎችን በስነ ልቦና የማዘጋጀትና የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጥ መደረጉን የቢሮ ኃላፊው አቶ ጌቱ ተናግረዋል።
‎
‎በአደረጃጀቱ መሠረት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የተሻለ ልምድ ባላቸው መምህራን የማጠናሪያ ትምህርቱ እንዲሰጥ መደረጉን ገልጸው፤ ከመምህራን በተጨማሪም ጠንካራ ተማሪዎች ተመርጠው የሚረዳዱበት ፕሮግራም ተቀርዖ በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመራ እንደሆነ አስታውቀዋል።
‎
ተማሪዎቹ ያላቸውን የጥናት ጊዜ በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉም ቤተ መጽሐፍቶች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከጠዋቱ 2:30 እስከ ምሽቱ 1:30 ክፍት እንዲሆኑ መደረጋቸውንም ጠቁመዋል።
በዚህም ተማሪዎች ውጤት የሚገኘው ጠንክሮ በመስራት መሆኑን በመረዳትና ለትምህርታቸው ትኩረት በመስጠት የማንበብ ባህላቸው እየደገ መጥቷልም ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/14WEDuXGZkb/
ማህበረሰቡና አጋር የልማት ድርጅቶች የተቀናጀ ድጋፍ በትምህርት ዘርፉ የሚካሄደውን የመማር ማስተማር ሂደት ውጤታማ እያደረገው መሆኑ ተገለጸ።
--------------------- // ----------------------

(ጥር 20/ 2018 ዓ.ም) የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር ማህበረሰቡና የተለያዩ አጋር የልማት ድርጅቶት የሚያደርጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ፣ በትምህርት ስራው ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች ገለጹ።

በጋሞ ዞን ሠላም በር ከተማ አስተዳደር የሠላም በር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህር የሆኑት አቶ ጌታቸው በቀለ በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ከማህበረሰቡና ከልማት ማህበራት የሚገኙ ድጋፎች የመማር ማስተማር ስራው ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን ተናግረዋል።

በተለይም የማጠናከሪያ ትምህርት ለሚሰጡ መምህራን ማበረታቻ በመስጠት፣ የትምህርት ቤት መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ የቤተ-ሙከራ ቁሳቁሶችን በማሟላት ረገድ ማህበረሰቡና በትምህርት ቤቱ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ልማት ማህበራት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በስልጤ ዞን ስልጤ ወረዳ የሚገኘው አሳኖ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዳይሬክተር አቶ ኑሪ ሸኩር በበኩላቸው በትምህርት ቤቱ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ችግሮች በማህበረሰቡና በአጋር የልማት ድርጅቶች ተሳትፎ እየተፈቱ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/18LHTHBNdH/
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ኢንዲስትሪ ትስስር ጥራትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንደሚያስችል ተጠቆመ፤
------------------------------ // ------------------------
‎
‎(ጥር 23/2018 ዓ.ም) ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር አተኩረው እንዲሰሩ እየተሰራ ይገኛል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት የምርምና የማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሐንዲሶ (ዶ/ር) እንደገለጹት የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ጥራትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጻኦ ይኖረዋል።
‎
‎የትምህርት ምርምርና ስልጠና ተቋማት ጥራት መሻሻል የኢንዲስትሪዎችን ምርታማነትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነተ እንደሚያሳድገውም ዶክተር ሠራዊት ገልጸዋል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ዋነኛ አቅሞች በመሆናቸው
‎ተጽዕኗቸውን በተጨባጭ ወደተለወጠ የኢኮኖሚና እድገት ማሸጋገር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤https://www.facebook.com/share/p/1Hra2ZhcNR/
በከፍተኛ ትምህርት የሚስተዋለውን በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት ለማቃለል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
------------------------------- // -----------------------
‎
‎(ጥር 23/2018 ዓ.ም) በህንድና በኢትዮጵያ ትምህርት ተቋማት የ3ኛ ዲግሪ ስልጠና ለመስጠት በተደረሰው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
‎
‎የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በአገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ3ኛ ዲግሪ (PhD) ያለው የሰለጠነ የሰው ሀይል ከ18 በመቶ እንደማይበልጥ ተናግረዋል።
‎
‎ለአገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በሚያበረክተው የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ በአግባቡ የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን ዶክተር ኤባ ገልጸዋል።
‎
‎በኢንጂነሪንግና በቴክኖሎጂ አድቫንስድ ከሆኑ የህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች Indian Institutes of Technology በተደረሰ ስምምነት መሠረት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከ1200 የሚበልጡ መምህራንን ለማሰልጠን መታቀዱን መሪ ስራ አስፈጻሚው አመልክዋል።

‎የመምህራንና የተማሪዎች ጉዳይ ዴስክ ኃላፊ አቶ በየነ ተዘራ በበኩላቸው ከህንድ የትምህርት ተቋማት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለአምስት ዓመታት በየዓመቱ 252 የዩኒቨርስቲ መምህራን በ3ኛ ዲግሪ እንደሚሰለጥኑ አስታውቀዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1KJSsxbcXE/