የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተማሪ መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
----------------------- // --------------------
(የካቲት 03/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት በተገኘ ድጋፍ ያሳተማቸውን 23.9 ሚሊየን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍት ጅቡቲ ወደብ ደርሰው ወደ ሃገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ እየተሰራ ነው።
ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የተማሪ መጽሃፍትን በሁሉም የትምህርት እርከኖች አንድ ለአንድ ለማድረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍትን ማሟላት የክልል ትምህርት ቢሮዎች ሃላፊነት መሆኑን ያነሱት የትምህርት ሚኒስትሩ ነገር ግን እንደ ሀገር የሚታየውን የተማሪ መጽሃፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ ሀብት በማፈላለግ ከ23.9 ሚሊየን በላይ መጽሃፍትን ማሳተም መቻሉን አብራርተዋል።
እነዚህ የታተሙት መጽሃፍት ጅቡቲ ወደብ ደርሰው የተወሰኑት ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸውን ጠቅሰው በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ ተጠናቀው በመግባት ለሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተቀናጀ ሁኔታ የሚሰራጩ በመሆኑ ክልሎች በፍጥነት በመረከብ ወደ ትምህርት ቤት በማውረድ ተማሪዎቹ መጽሃፍቱን እንዲያገኙ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1E65DoVwpX/

ትምህርት ሚኒስቴር ያሳተማቸው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍት ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸው ተገለጸ።
-------------------------- // -----------------------
(የካቲት 05/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ባገኘው ድጋፍ ያሳተማቸው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍት በገላን የመጽሃፍት ክዘና ማዕከል እየተራገፉ ይገኛል።
የትምህርት ሚኒስቴር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ ከአጋር አካላት ባገኘው ድጋፍ ከ23.9 ሚሊየን በላይ መጽሃፍትን በማሳተም ከጅቡቲ ወደ ሃገር ውስጥ ማጓጓዝ መጀመሩን የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ ገልጸዋል።
በዚህም ከ30 ኮንቴነር በላይ መጽሃፍት በገላን የክዘና ማዕከል መድረሳቸውን የገለጹት ሥራ አስተፈጻሚዋ አሁን የደረሱትን መጽሐፍት ክልሎች እንዲረከቡ ከስር ከስር የማሰራጨት ሥራ ይሰራል ብለዋል። በትክክል ለተማሪዎች መሰራጨታቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
መጽሐፍቶቹም ሲታተሙ በሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ዞኖች የሚያሳይ መለያ ኪውአር ኮድ (QR CODE) የተካተተ በመሆኑ የሁሉንም ዞኖች መጽሐፍቶች በመለያ ኮዳቸው መከታተል የሚቻልበት አሰራር መኖሩንም አብራርተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍትን አንድ ለአንድ ያደረሰ ሲሆን የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ እንዲቻል ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ ረገድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
------------------ // ------------------
(የካቲት 06/2018 ዓ.ም) በቅርቡ አዲስ የተመደቡ የቦርድ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተረድተው ወደ ተግባር እንዲገቡ የሚያስችል የሥራ ትውውቅና መመሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች የተጣለባቸውን አገራዊ አደራ ለመወጣት የተመደቡበት ተቋም ተልዕኮና የሥራ ድርሻ በውል መረዳት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም አመራሩ የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት በጥልቀት አውቆና ተረድቶ መስራቱ ለተቋሙ ስኬት መሰረታዊ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆናቸው አመራሩ ግልጽ ራዕይ ይዞ መንቀሳቀሱ የተቋማዊ ለውጥ (Reform) ስራዎችን በብቃት ለመምራትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎርምና መደበኛ ስራዎችን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።
አዳዲሶቹ አመራሮች የተሰጣቸውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ወደ ስራ ሲሰማሩ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ ካለው ሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫ ጋር በማጣጣም መከወን እንደሚገባቸውም አቅጣጫ ተቀምጧል።

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ለአይነ ስውራን የተዘጋጁ የ2ኛ ደረጃ የብሬል መጽሐፍት እየተጓጓዙ ነው።
------------------------ // --------------------------
(የካቲት 09/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመጀመሪያው ዙር ለስርጭት የተዘጋጁ የብሬል መጽሀፍቱን የስርጭት ሂደት ተመልክተዋል።
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የመጽሐፍቱን ስርጭት ሂደት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ጥራት፣አግባብነት ፣ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ለማረጋጥ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል ብለዋል።
ከሪፎርም ስራዎች መካከልም የተሻሻለውን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መነሻ በማድረግ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ተግባራዊ መደረጉን ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል።
ተግባራዊ በተደረገው ሥርዓተ ትምህርት መሠረትም ተማሪዎችና መምህራን የሚገለገሉባቸውን የመማሪያና የማስተማሪያ መጽሀፍት አንድ ለአንድ ለማድረስ ሲሰራ መቆየቱንም ክብርት ወ/ሮ አየለች ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጎች የመማርና የመማሪያ ግብዓቶችን ማግኘት መብት እንዳላቸው ያስገነዘቡት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ዜጎች በሁሉም ረገድ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1LN6njN6Dp/

ሴቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርትና ምርምር በመሳብ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ቅንጅትና ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተመላከተ።
-------------------- // ----------------------
(የካቲት 09/2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሴት ተመራማሪዎች ቀን በአዲስ አበባ ተከብሯል። በበዓሉ ላይ ተገኝተው መለዕክት ያስለላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የሴት ተመራማሪዎች ቁጥር እድገት እያስመዘገበ መምጣቱን ጠቅሰው ሴቶችን በማብቃትና ወደ አመራር እንዲመጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የሴቶች በሳይንስ፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎና የአመራርነት ሚና እንዲጎለብት በቅንጅት የተጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የሴት ተመራማሪዎች ማህበር መፈጠር ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ክብርት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስገንዝበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው አንድ ተቋም ብቻውን የሴቶችን የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ አይችልም ብለዋል።
ሴቶች በሳይንስ፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ውስጥ ያላቸው ተሳትፎና አመራር እንዲጎለብት የሁሉም ተሳትፎና ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BdiAm2D7P/

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።
-------------------------- // ---------------------------
(የካቲት 10/2018 ዓ.ም) የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዬት ደምሴ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደተናገሩት በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የትምህርት ቢሮው የተማሪዎችን ውጤት ለማሳደግ ከትምህርት ሚኒስቴር በወረደው ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ንቅናቄ መሰረት የማጠናከሪያ ትምህርት (Tutorials) እየሰጠ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ለዚህም ስራ ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን አስታውቀዋል።
ይህ በጀት ከመንግስት ፣ ከልማት ማህበራት እና ከባለሀብቶች የተሰባሰበ ሲሆን የተመረጡ መምህራን እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተውጣጡ መምህራን በማጠናከሪያ ትምህርቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉን አንስተዋል።
በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ወደ 20 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮ ሃላፊው ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በትምህርት አመራሩ ላይ መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን አዳዲስ መመሪያዎችና ደንቦች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/179VmHHrT7/