Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎቻቸው በአመቱ ሥራ መፍጠራቸውን ወይም መቀጠራቸውን በጥናት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ።
--------------------- // -----------------------
(መጋቢት 4/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በአካዳሚክ ጉዳዮች ሪፎርም ተግባራት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

አውደጥናቱን የከፈቱት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎቻቸው በአመቱ ሥራ መፍጠራቸውን ወይም መቀጠራቸውን በጥናት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድ የሚደረገውን ጥናት በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጡ አቅጣጫዎች መሠረት የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ለማሻሻል እና ለፖሊሲ አውጪዎች ወሳኔ ግብዓትነት በሚጠቅም መልኩ መሰነድ አንደሚገባቸውም አንስተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው ለሥራ ፈጠራ ዝግጁ የሆነ አዕምሮ እንዲኖራቸውና የሥራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሥራ ፈጠራ ሀሳብና ክህሎት ማዳበሪያ ማዕከላት ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17a1RAJPik/
በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጸ።
------------------------ // ------------------------
(መጋቢት 05/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተሰራ ያለውን ሥራ በተመለከተ ከክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም በክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች በሁሉም የክፍል ደረጃ በተለይም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በወረደው ስትራቴጂ መሰረት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ከማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎች ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ውጪ ያላቸውን ጊዜ ተጠቅመው እንዲያጠኑ እና ቤተ-መጻህፍትን እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታዎች በየትምህርት ቤቶቹ መፈጠራቸውን አንስተዋል።

በተለይም ተማሪዎችን በማዘጋጀት ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በየጊዜው በመፍታትና በቀሩት ቀናት ጉድለቶችን በማሟላትና የተማሪዎችን ዝግጅት በቅርበት በመከታተል ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለፈተናው ስኬታማነት በትኩረት እንደሚሰሩ የክልል ቢሮ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለመምህራንና ለተማሪዎች አጋዥ የሆኑ የትምህርት ይዘቶችንና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድህረ-ገጽ (Portal) ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉም ተብራርቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1TyPMiyPuw/
ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ሀገር በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ።

------------------------- // ---------------------

(መጋቢት 09/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች "50ኛ ዓመት የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በድምቀት ከክብረዋል።

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ሀገር በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማረጋገጥ በልማትና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ አይተኬ ሚና ያለው መሆኑን በማንሳት እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17MyBk6LsJ/
ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ በተዘጋጁ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
1. በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ https://forms.gle/KiRAQn6kjsZ6yymt6
2. የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ https://forms.gle/YEsQJwjE3wYUypJz6
3. በትምህርት ሚኒስቴር ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ
https://forms.gle/HLqZm83W2ANMWMLt5
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራዎቻቸውን በእውነት፣ በሐቀኝነትና በታማኝነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
----------------------- // ------------------------
‎(መጋቢት 14/2018 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በተዘጋጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ፣ የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ ደንብ ፣ ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
‎
‎የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራዎቻቸውን በእውነት፣ በሐቀኝነትና በታማኝነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
‎
‎በተቋማቱ የሚካሄዱ የሪፎርም አጀንዳዎች ዓላማ ዩኒቨርስቲዎች ካሉባቸው ተለምዷዊ የአሰራር ልምዶች በማላቀቅ አርአያነት ባለው መልኩ ተልዕኳቸውን እንዲፈጽሙ ማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት የአመራር ምልመላ የሚፈለጉ የአመራር ክህሎቶችን መሠረት ያደረገ ግልጽነትና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ፣ ከኢንዱስትሪና የውጭ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጭምር በሚጋብዝ መልኩ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CNJ5oDpJf/
ኢትዮጵያ እና ኒውዝላንድ በትምህርቱ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደርገዋል።
----------------------- // -------------------------
(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የኒውዝላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ኦውንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ አካላት በትምህርት ዘርፉ የነበራቸውን ትብብር አጠናክረው መቀጥል በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ውቅት የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ሥርዓቱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በትምህርት ዘርፉ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ተግባራትን ለአምባሳደሯ አብርራተውላቸዋል።

እነዚህን የሪፎርም ተግባራት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግም ከሀገሪቱ የመልማት ፍላጎት ጋር አብረው በሚሄዱ አዳዲስ የትምህርት መስኮች፣ በከፍተኛ ትምህርት ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ልማት፣ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ግብዓት አቅርቦትና በመሳሰሉት ላይ የአጋር አካላትን ድጋፍ እንደሚፈልጉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የኒውዝላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ኦውን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ እየተገበረቻቸው ያሉ የሪፎርም ተግባራት የሚደነቁ መሆኑን ገልጸው ኒውዝላድ በትምህርቱ ዘርፍ የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/1B8cZb1wHa/