Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ማስታወቂያ

ለ2019 ዓ/ም አዲስ ለተቋቋሙና ለነባር የፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ሙያ ተቀጥረው ለማገልገል የፅሁፍ ፈተና በመውሰድ የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ለቃለ መጠይቅ ለተመረጣችሁ መምህራን በሙሉ፣

ቃለ መጠይቁ የሚካሄደው ጳጉሜ 3/2018 ዓ. ም ማክሰኞ በኦንላይን የሚካሄደ ሲሆን በምዝገባ ወቅት በሰጣችሁት ስልክ ቁጥር ዋትስአፕ ላይ በመግባት እንዴት ኢንተር ቪውን በሞባይልና በላፕቶብ ማድረግ እንደምትችሉ የተጫነውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን!
የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች «በህብር እንደጋገፍ፤ አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንቀበል» በሚል መሪ ቃል የህብር ቀንን አከበሩ።

-------------------- // --------------------


(ጳግሜ 4/2018) የትምህርት ሚኒስቴር ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞቹ ለአዲስ አመት በዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ አደረገ።


በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት በበዓላት መደጋገፍና መተጋገዝ የቆየና ውብ የሆነ የኢትዮጵያውያን እሴት መሆኑን አብራርተዋል።


አክለውም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በተጠበቀው ልክ አድጎና ተጠናክሮ እያንዳንዱ ዜጋ ሰርቶ ራሱንና ቤተሰቡን በሙሉ አቅም መደጎም የሚችልበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ እንዲህ ያሉ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህሎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።


የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የህብር ቀን አከባበር ቴክኒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ እንደገለጹት በትምህርት ዘርፉ ስር ባሉ ልዩ ልዩ የትምህርት ተቋማት የበጎ ፈቃድና የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/14sth2kRq9P/