Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የተፋጠነ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ለማሻሻል ያለመ አህጉራዊ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

------------------- // -------------------

(ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም) የኢትዮጵያን የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም (ALP) ተሞክሮዎች ለአፍሪካ አገራት ለማካፈል እና የትምህርት ቀውሶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ያለመ አህጉራዊ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአውደ ጥናቱ መክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉት የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዬሴፍ አበራ የትምህርት ቀውሱን ለመፍታት ከትምህርት ውጪ የሆኑ ሕፃናትን ችግር በከተማ እና በገጠር ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በተመሠረቱ የጣልቃ-ገብነት ስልቶች ማስተካከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያን የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም (ALP) ተሞክሮዎች ለሌሎች የአፍሪካ አገራት በማካፈል እና ሰፋ ያለ ልምድ ልውውጥ በማድረግ የመንግሥትን የመሪነት ሚና ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።


በተጨማሪም የትምህርት ባለሙያዎች አቅም ግንባታ እና የጥራት ማረጋገጫ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አበክረው ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1CKLgRmZWE/
ማስታወቂያ

በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ተማሪዎችን ለመቀበል በወጣው ማስታወቂያ መሠረት የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ትምህርት ቤት ቀደም ሲል በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት እንድታረጋግጡና የኦንላይን ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እየጠየቅን፤

ምዝገባችሁን ካጠናቀቃችሁ በኋላ፣ እስከ እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ተመደባችሁበት ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ እናሳስባለን።

የትምህርት ሚኒስቴር
በአማራጭ የመምህርነት ሙያ የሰለጠኑ የመጀመሪያዎቹ 693 ዕጩ መምህራን ተመረቁ።

----------------------- // -------------------------
‎
‎(ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም) በአማራጭ የመምህርነት ሙያ ሥልጠና የሰለጠኑ የመጀመሪያዎቹ 693 ዕጩ መምህራን ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ።

ትምህርት ሚኒስቴር እንደ ሀገር የሚስተዋለውን የመምህራን አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከወሰዳቸው አማራጮች መካከል በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተመርቀው ወደመምህርነት ሙያ መቀላቀል ለሚፈልጉ ምሩቃን ባመቻቸው የስልጠና እድል በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 693 እጩ መምህራንን አስመርቋል።

‎
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ተ/ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አሰገደች ምሬሳ፣ መምህርነት ለትውልድ ቀረጻ እና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ሙያ መሆኑን ገልጸው ምሩቃኑም ይህንኑ ኃላፊነት በመገንዘብ፣ በታማኝነት፣ ሙያው በሚጠይቀው ሥነ ምግባርና በቁርጠኝነት በመሥራት ለተማሪዎቻቸው አርአያ እንዲሆኑና ለሀገራቸው እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘትይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1bme24Q28J/
ማስታወቂያ

ለወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦

በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቱ የመግቢያ ቀናት ህዳር 1 እና 2/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።

በተጨማሪም፣ ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ለተማሪዎች የኦረንቴሽን መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን፣ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም ደግሞ የመማሪያ መጻሕፍት ስርጭት ይከናወናል።

ስለሆነም ሁላችሁም ነባርና አዲስ ተመዳቢ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እናሳስባለን።

መልካም የትምህርት ዘመን!

የትምህርት ሚኒስቴር