Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የኢትዮጵያ የትምህርት ሪፎርም ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት በትምህርት ጥራት ማሻሻያ ረገድ አርዓያ መሆን እንደሚችል ተገለጸ።

------------------------- // --------------------------

(ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም) የዩኔስኮ የአፍሪካ አቅም ግንባታ ተቋም (UNESCO-IICBA) የአቅም ግንባታ ከፍተኛ የፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ቪክቶሪያ ኪሳቼ ካኖቤ በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ያለዉ የትምህርት ሪፎርም ስራ እና የተፋጠነ የትምህርት መርሃ-ግብር (Accelerated Learning Programme) ትግበራ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑን ገለጹ።


ከተለያዩ ሀገራት ልኡካን ቡድን አባላት ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎች መሰል የፌዴራል ተቋማትን የጎበኙት ሀላፊዋ የኢትዮጵያን የትምህርት ፓሊሲና ስትራቴጂ ትግበራ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በርካታ ልምዶችን ሊቀስሙበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተለይም በተፋጠነ የትምህርት መርሃ-ግብር አተገባበር ረገድ ይዘቶችን ለአጭር ጊዜ ማስተካከል፣ መምህራንን የማነሳሳት ስራዎች እና የተማሪዎች ወሳኝ የማሰብ ችሎታን ለማጎልበት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ከፍተኛ አድናቆት የሚቸራቸው መሆኑን አመላክተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/19rueyuQZr/